ቅዳሜ፣ ኅዳር 9 2004
ምድሪቱ ያልተነካች የማርና ወተት
በረከቷ ብዙ የሚያጠግብ ህብስት
ተስፋው ከግንብ ይልቅ የጸና
ስሙ በጠላት ፊት ሞገስና ግርማ
የአንደበትህ ውበት የጥያቄዎች መልስ
ሊያወርስህ ያሰበው ገና ገና ብዙ
የእግዚአብሔር ህዝብ ሆይ የሚጠብቅህ ሳይዝል አይኖችህ ፈዘዙ
ገና በማለዳ ጉልበት በረሰ
ምኑንም ሳታየው ሀሞትህ ፈሰሰ
አረጀህ ሳይነጋ ጮራህ ሳይፈነጥቅ
ፀጋ በዝቶ ሳለ የመንፈስ ቅዱስ ጽድቅ
ንቃ ወገን ንቃ ወንጌሉ ሲዘራ
ወደ እግዚአብሔር መንግስት እንገባ ዘንድ አለን በብዙ መከራ