የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ

የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

ክቡርና ሕይወት ሰጪ ስለሆነው መስቀል

ቅዱስ ጎርጎርዮስ ፓላማስ እንደ ሰበከው

መቅድም
በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ጎርጎርዮስ በሚለው ስም የሚታወቁ ብዙ ቢኖሩም ታላላቆቹና በብዙኃኑ ዘንድ የሚታወቁት አራቱ ናቸው። የመጀመሪያው የሊቁ አርጌንስ ተማሪ የነበረው ቅዱስ ጎርጎርዮስ ገባሬ መንክራት፣ ሁለተኛው ጎርጎርዮስ ዘእንዚናንዙ፣ ሦስተኛው የቅዱስ ባስልዮስ ወንድም ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ ናቸው። አራተኛውና የእነዚህን ቅዱሳን አባቶች ፈለግ የተከተለው ጎርጎርዮስ ፓላማስ የሚባለው ቅዱስ አባት ነው። በታሪክ አሳዛኝ የሆነው የምሥራቅና ኦሪየንታል ክፍፍል ከተከሰተ በኋላ በምሥራቁ ወይም ባይዛንታይን ኦርቶዶክስ፣ የአቶስ ተራራ /Mounth Athos/ በሚባለው ገዳም በምነና ይኖርና ያገለግል የነበረ በኋላም ቆይቶ የተሰሎንቄ ሊቀ ጳጳስ የሆነ አባት ነው። የዚህን አባት ሥራዎች ተርጉመን የማቅረባችን ምክንያት ብዙ ቢሆንም ዋና የሆኑትን ሁለቱን እንጥቀስ፡- አንደኛው ይህ ስብከት ስለተሰቀለው ጌታና ስለ መስቀል በመሆኑ ምክንያት ከስብከቱ ቃል እንድንቀደስ በማሰብ ነው። ሁለተኛው ጌታ ቢፈቅድ ለወደፊቱ ይሆናል ብለን ለምናስበው የምሥራቅና የኦሪየንታል አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት መንገድ ጠራጊ ይሆን ዘንድ ነው። በሚደንቅ ሁኔታ አንባቢ ስብከቱን ሲያነብ የደራሲው ስም ባይነገር ከኦሪየንታል አባቶች አንዱ ነው ብሎ ሊናገር እንደሚችል መገመት አይከብድም። ይህ የሆነው እነዚህ ሁለት የኦርቶዶክስ ቤተሰቦች ምንም እንኳን በብዙ ምክንያቶች ተከፋፍለው ለዘመናት ቢቆዩም ሁለቱም ለጌታ ትምህርት፣ ለሐዋርያት ትውፊት፣ ለቅዱሳት መጻሕፍት ምሥጢር፣ ለአባቶችይወትና አስተምህሮ ታማኝ በመሆናቸው ምክንያት ነው። ቅዱስ ጎርጎርዮስ ፓላማስ በትምህርቱ መሐል ስለ ተሰቀለው ክርስቶስና ስለ መስቀል የሚያነሣቸውሳቦች እኛ አሁን ድረስ የምንጠብቃቸውና የምናምናቸው ሆነው ስናገኛቸው አእምሮአችን ይደነቃልልባችንም ሐሤ ያደርጋል። መልካም ንባብ!

ክቡርና ይወት ሰጪ ስለሆነው መስቀል
የክርስቶስ መስቀል ምጢራዊ  በሆነ መልኩ አስቀድሞ የተነገረ ከጥንት ዘመን ጀምሮ በምሳሌ የተገለጠ ነው። ከመስቀሉ ኃይል ውጪ አንድም ሰው ከእግዚአብሔር ጋር አልታረቀም ታርቆም አያውቅም። የመጀመሪያዎቹ አባትና እናታችን ገነት ባለው ዛፍ ምክንያት እግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ካደረጉ በኋላ ኃጢአት ወደ ይወታችን መጣ። ነገር ግን የአካላዊ ሞት /የነፍስ ከሥጋ መለየት/ ከመሞታችን አስቀድሞ ፤ የነፍስ ሞት ሞትን ። ይህም ከእግዚአብሔር መነጠልና መለየት ነው ። ከመተላለፍ በኋላ በኃጢአት ውስጥና በሥጋ ኖርንስለ ሥጋ ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነውና ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና መገዛትም ተስኖታል፤ በሥጋ ያሉትም እግዚአብሔርን ደስ ሊያሰኙት አይችሉም (ሮሜ 8፥78)።
ሐዋርያው፡- ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስም በሥጋ ላይ ይመኛልና (ገላ 5፥7) እንዲል ። ሆኖም ግን እግዚአብሔር መንፈስ ነው ። ፍጹም መልካምና ደግ (መንፈስ) ። ምንም እንኳን ኃጢአት ጥቅም የሌለው ቢያደርገውም የእኛ መንፈስም የእግዚአብሔር መልክና አርአያ ያለው ነው ። ስለዚህ አንድ ሰው  ኃጢአትና የሥጋ ይወት ካልተሻረና ድል ካልተደረገ በስተቀ  በመንፈስ መታደስና ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ የሚቻለው እንዴት ነው ? የክርስቶስ መስቀል የዚህ ኃጢአት መሻር/ድል መነት ነው። እግዚአብሔርን ከተሸከሙ /እግዚአብሔር ካደረባቸው እነሱም በእግዚአብሔር ካደሩት[1]/ አባቶች አንዱ የሆነው አባት በአንድ ኢአማኒ በተሰቀለው ክርስቶስ የእውነት ያምን እንደሆነ ተጠይቀ እርሱም “አዎ ኃጢአትን በሰቀለው በእርሱ አምናለው” ብሎ መለሰ ። እግዚአብሔር ራሱ መስቀል ከመገለጡ በፊት ፤ ከግ መሰጠት በፊት ይሁን ግ ከመሰጠቱ በኋላ ወዳጆቹ የሆኑ ብዙ ሰዎች እንደ ነበሩ መስክሯል ። ንጉና ነይ የነበረው ዳዊት በዘመኑ ከእግዚአብሔር ጋር ወዳጅ እንደነበረ እንዲህ ሲል ተናገረ አቤቱ፥ አሳቦችህ በእኔ ዘንድ እንደ ምን እጅግ የተከበሩ ናቸው! ቍጥራቸውም እንደ ምን በዛ! (መዝ 138(39)፥17)። ስለ እግዚአብሔር ፍቅር ብላችሁ አስተውላችሁ የምትሰሙኝ ከሆነ ከመስቀል በፊት ሰዎች እንዴት የእግዚአብሔር ወዳጅ ተብለው ይጠሩ እንደበረ አሳያችኋለ
የዓመ ሰው የሥርዓት አልበኝነት ልጅ (2ኛ ተሰ 2፥3) ማለት የፈለግሁት ሐሣዊሳይ መሢሑን ነው ፣ እስከ አሁን አልመጣም ። ክርስቶስ የሚወደው የነገረ መለኮት ሊቅ /theologian/ እንዲህ ይላል አሁን እንኳ ብዙዎች የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ተነሥተዋል (1ኛ ዮሐ 2፥18)። በተመሳሳይ መልኩ መስቀልም ከመፈጸሙ /ክርስቶስ በመስቀል ላይ ከመሰቀሉ/ አስቀድሞ በአባቶቻችን (በብሉይ ኪዳን) ዘመን ነበር። ታላቁ ጳውሎስ በእርግጠኛነትና ግልጽ በሆነ ቋንቋ ሐሳዊ መሢሑ አሁን ባይመጣም በመካከላችን እንዳለ እንዲህ በማለት ያስተምረናል የዓመፅ ምሥጢር አሁን ይሠራልና (2ኛ ተሰ 2፥7)። ልክ እንደዚሁ በተመሳሳይ መልኩ የክርስቶስ መስቀልም ከመገለጡ አስቀድሞ ምጢሩ በእነርሱ ዘንድ ይራ ነበርና በአባቶቻችን መካከል ነበር።
አቤልን፣ ሴትን፣ ሄኖስን፣ ኖክን፣ ኖኅንና እስከ ኖኅ ዘመን ድረስ በእነርሱ ትውልድ አብረዋቸው እግዚአብሔርን ደስ ያሰኙትን ወደ ጎን ልተው። የአዛብ /የብዙን/ አባት በተባለው፣ በሥጋ የአይሁዳውያን በእምነትም የእኛ አባት ከሆነው ከአብርሃምም ልጀምር ። የእኛ መንፈሳዊ አባት ስለነበረው ስለዚህ አባት መልካም ጅማሮና እግዚአብሔር መጀመሪያ ስለጠራው መጥራት (መናገር) ልጀምርና እግዚአብሔር መጀመሪያ የተናገረው ቃል ምንድር ነበር ? ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ (ዘፍ 12፥1)። ይህ አጠራር በውስጡ የመስቀልን ምጢር ይዟል ። ጳውሎስ መስቀልን ሲያከብር የሚለው ይህንኑ ነው ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት (ዘፍ 6፥14)። አንድ ሰው ከገሩ ወይም ከዓለም ወደ ኋላ ዘወር ሳይል ከወጣ ለዚህ ሰው በሥጋ ገሩ የሆነው ቦታ እና ዓለም ሞተዋል ህልው መሆንም አቁመዋል ይህም መስቀል ነው/ይህ ነው እንግዲህ መስቀል።
ከኑሮውና ከይወቱ ከማያምን ሰው ጋር ከመውጣቱ አስቀድሞ እግዚአብሔር አብርሃምን እንዲህ አለው ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ (ዘፍ 12፥1) ወደማሳይህ እንጂ ወደምሰጥህ አላለውም። ይህንን ያለው በዚህ ምድር ሌላ መንፈሳዊ ምድር ይታይ ዘንድ ነው። ሙሴ ከግብ ከሄደና ተራራውን ከወጣ በኋላ እግዚአብሔር የተናገረው የመጀመሪያ ቃላት ምንድር ነበሩ? ጫማህን ከእግርህ አውጣ (ዘፍ 3፥5) ይህ የመጀመሪያውን በሚገባ የሚመስል ሌላ የመስቀሉ ምጢር ነው። እግዚአብሔርን እንዲህ አለው “ከግብፅ ምድር ወጥተሃል፣ የፈርኦንን አገልግሎት ትተሃል የፈርኦል የሴት ልጅ /የልጅ ልጅ/ መባል እምቢ ብለሃል። አንተ እስከሚገባህ ድረስ ሰይጣንን የማገልገል ዓለም ፈራርሷል ተወግዷል ፈጽሞ አይኖርም ። ሆኖም ግን ከዚህ ተጨማሪ ሌላ ነገር ያስፈልግሃል።” ይህ ነገር ምን ሊሆን ይችላል? “ጫማህን ከእግርህ ታወልቅ ዘንድ፣ አንተን ቅድስት ከሆነች ምድር ነጥሎ ኃጢአት የሸፈነህና ኃጢአት የሚራበትን የሥጋን ልብስ ታስወግድ ዘንድ (ዘፍ 3፥21) እነዚህን ጫማዎች ከእግርህ አውጣ።” ይህም ማለት “ከዚህ በኋላ በሥጋና በኃጢአት አትኑር። ነገር ግን ከእግዚአብሔር ተቃራኒ የሆነው ይወት ይጥፋ ይሙትም ማለት ነው።  በሥጋ የሆነው ሳብና አስተሳሰብ (ሮሜ 8፥67)፣ በአእምሮህ ካለው ግ በተቃራኒ የሚዋጋህ በብልቶች ያለውን ግ ፣ ወደ ኃጢአት ግ ባርነት የሚመራህ (ሮሜ 7፥32-82) (ሁሉ) ምርኮ አያውርድህ፣ በአንተ ዘንድ ንቁና ያው አይሁን ይህ በእግዚአብሔር ራእይ ኃይል ድል ተነቷልና።” በእርግጥ ይህ መስቀል ነው። በጳውሎስ ቃላት መረት መስቀል ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር (ገላ 5፥24) ለመስቀል እንደሆነ ነገሮናል።   
ወደዚህ አትቅረብ አንተ የቆምህባት ስፍራ የተቀደሰች መሬት ናትና ጫማህን ከእግርህ አውጣ አለው (ዘጸ 3፥5) አለው። እነዚህ ለሙሴ የተነገሩት ቃላት ምድር ከጌታችን፣ ከአምላካችንና ከመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ በኋላ በመስቀል እንደምትቀደስ ይገልጻሉ። በዚያን ጊዜ ልክ እንደ ጤዛ የቀዘቀዘ የሚመስለውን ቁጥቋጦውን ተመለከተ። ሙሴም ለወደፊቱ ሊመጣ ያለውን የክርስቶስን መምጣት ተመለከተ። በመስቀሉ አምላክ ያለ ራእይ አስቀድሞ ከነበረው ምጢር የሚበልጥና የሚልቅ ምጢር ነው። ታላቁ ጳውሎስና ቅዱሳን አባቶቻችን ሁለት ዓይነት ምጢር/መገለጥ እንዳለ ያስተምሩናል/ይጠቁሙናል። ጳውሎስ ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት ብቻ ሳይሆን የሚለው እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ይላል (ገላ 6፥14)። አባቶች በበኩላቸው በችኮላ ሁለት የመስቀል ቃላትና ሁለት ምጢር እንዳለ አንዱን መስቀል ከሌላው እንዳናስበልጥ ያዙናል
  
የመስቀል የመጀመሪያው ምጢር በሥጋ ዘመዶቻችን የሆኑት ሰዎች ለቅድስናና ለትጋት ይወት መሰናክል የሚሆኑብን ከሆነ ከእነርሱ መለየትና ከዓለም መሸሽ ወይም መውጣትና ጳውሎስ እንደሚነግረን ሰውነትን (እግዚአብሔርን መምሰል) ማስለመድ ነው (1ኛ ጢሞ 4፥8)። በእነዚህ መንገዶች ከዓለምና ከኃጢአት አንድ ጊዜ ከተለየንና ከሸሸን ለእኛ የተሰቀሉ ይሆናሉ። በሁለተኛ የመቀል ምጢር መረት አንድ ጊዜ ከእኛ ከራቁና ከሸሹ ለዓለምና ለስሜቱ የተሰቅልን እንሆናለን። በእርግጥ እግዚአብሔርን (በፍጹም ልብ፣ ነፍስና ሳብ) ማሰብ ስለ እርሱም መመሰጥ ካልቻልን፤ (ዓለምና ስሜት) እንደሚታወቀው ሙሉ በሙሉ ፈጽመው ይተውን ዘንድና በሳቦቻችን እንዳይሩ/እንዳይንቀሳቀሱ ማድረግ የማይቻል ነው። ራሳችን የሰወርነው መለኮታዊ ስጦታ በመፈለግና በውስጣችን ያለውን መንግተ ሰማያት በማሰብ፤ በተግባር ተመስጦን ስናደርግና ውስጣዊ ሰውነታችንን ስናጎለምስ ያን ጊዜ ራሳችንን ለለምና ለሜት ሰቀልን ። እንዲህ ባለው ተመስጦ ክፉ ሳቦችን እንደ ዝንብ የሚያባርርና መንፈሳዊ ሰላምንና መጽናናትን በነፍሳችን የሚተክል አንዳች ዓይነት ሙቀት በልባችን ይወለዳል ። ለአካችንም ቅድስናን ይሰጣል ። መዝሙረኛው እንዳለው ልቤም በውስጤ ሞቀብኝ ከማሰቤም የተነሣ እሳት ነደደ (መዝ 38(39)፥3)። እግዚአብሔርን ከተሸከሙ/እግዚአብሔርን ከለበሱ አባቶቻችን አንዱ ስለዚህ ነገር እንዲህ ብሎ አስተማረን “ውስጣዊ መጋደላችሁ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንዲሆን የምትችሉትን ሁሉ አድርጉና ውጫዊውን ስሜት ድል ታደርጋላችሁ።” ታላቁ ጳውሎስም በተመሳሳይ አቅጣጫ እያሳሰበን እንዲህ ይላል በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ (ገላ 5፥16)። በሌላውም ስፍራ እንዲህ ሲል አጥብቆ ያሳስባል ይመክርማል እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ታጥቃችሁ (ኤፌ 6፥14)። (ስለ እግዚብሔር) ተመስጦ ውስጥ የሚገባው የነፍስ ክፍል በምኞት የተያዘውን (የግዙፉ አካል) ክፍል ያጠነክረዋል ያግዘውማል ሥጋዊ ምኞትንም ያስወግዳል። ታላቁ ጴጥሮስም ፍጹም በሆነ ግልጽ አነጋገር ልቡናና እውነት ምን ማለት እንደሆነ እንዲህ በማለት ይነግረናል ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን ኖራችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ (1ኛ ጴጥ 1፥13)።
በእርግጥ እግዚአብሔርን (በፍጹም ልብ፣ ነፍስና ሳብ) ማሰብ ስለ እርሱም መመሰጥ ካልቻልን፤ (ዓለምና ስሜት) እንደሚታወቀው ሙሉ በሙሉ ፈጽመው ይተውን ዘንድና በሳቦቻችን እንዳይሩ/እንዳይንቀሳቀሱ ማድረግ የማይቻል ነው። እንዲህ ያለው ተመስጦ የመስቀል ምጢር በሆነበት ልክ ለእርሱ የተገቡ የሆኑትን ለዓለም የተሰቀሉ ያደርጋቸዋል። ሙሴ በእሳት ሳትቃጠል ያያት ያቺ ቁጥቋጦ ከአብርሃም ጊዜ ከተገለጠው የሚበልጥና የተሻለ የሆነ የመስቀሉ ምጢር ነው። እንግዲህ ሙሴ የበለጠ ፍጹም ወደ ሆነው የመስቀል ምጢር የተመራ አብርሃም እንደዛ ያልሆነ ነውን? ይህስ ኢምክንያታዊ በሆነ ነበር። በእውነቱ አብርሃም ወደዚህ ምጢር የተመራው  በተጠራበት ጊዜ አልነበረም። ምንም እንኳን አሁን ሁሉንም ለመዘርዘር ጊዜ ባይኖረንም አብርሃም ከመጀመሪያው ጥሪ በኋላ  አንድ፣ ሁለት ብሎም ብዙ ጊዜ ተመራ።
የአብርሃምን ድንቅ የእግዚአብሔር ራእይ ላስታውሳችሁ። (እግዚአብሔር ሥላሴ መሆኑ) ከመታወቁ አስቀድሞ ሦስት አካላት ያሉትን አንዱን እግዚአብሔር በግልጽ ተመለከተ (ዘፍ 18፥116)። “በቀትርም ጊዜ እርሱ በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር በመምሬ የአድባር ዛፍ ተገለጠለት። ዓይኑንም አነሣና እነሆ፥ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ በሦስት ሰዎች አምሳል የተገለጠለትን አንዱን እግዚአብሔር ተመለከተ። እንዲህም ይላል እግዚአብሔር በመምሬ የአድባር ዛፍ ተገለጠለት . . . ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ።” ሆኖም ግን ሦስቱን ሰዎች ሊገናኛቸው ሮጦ እንዲህ በማለት እንደ አንድ ሰው ጠራቸው “አቤቱ፥ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደ ሆነ ባሪያህን አትለፈኝ ብዬ እለምናለሁ” (ዘፍ 18፥3)። በመቀጠል ሦስቱም እንደ አንድ ሰው ከእርሱ ጋር ተነጋገሩ “እነርሱም፦ ሚስትህ ሣራ ወዴት ናት? አሉት። . . . የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ በእውነት እመለሳለሁ ሚስትህ ሣራም ልጅን ታገኛለች አለ” (ዘፍ 18፥9-10)።[2]አሮጊቷ ራ ይህንን በሰማች ጊዜ ስትስቅ እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው። ካረጀሁ በኋላ በውኑ እወልዳለሁን? ስትል ሣራ ለምን ሳቀች? (ዘፍ 18፥13)። “እግዚአብሔርም አለ” ተብሎ ተጽፏልና አንዱ እግዚአብሔር ሦስት አካል እንዳለው፣ ሦስቱ አካላትም አንድ አምላክ እንደሆኑ እወቁ።
የመስቀሉ ምጢር በአብርሃም ዘንድ የራው በዚህ መንገድ ነው። ለይስሐቅ (ይህ ምጢር በተለየ መንገድ ነው የተገለጠው)። እርሱ ራሱ እንደ ክርስቶስ ለአባቱ እስከ ሞት ድረስ የታዘዘ ነበርና (በይወቱ) መስቀል ላይ የተሰቀለውን አስቀድሞ አሳየ። በእርሱ (በይስሐቅ) ፋንታ የታረደው በግ (ዘፍ 22፥13) ስለ እኛ ወደ መታረድ የሄደውን የእግዚአብሔር በግ አስቀድሞ አስመልክቶናል። በጉ የተያዘበት ዕፀ ሳቤቅም የመስቀልን ምልክት ምጢር ይዟል። ዕፁም “ዕፀ ሳቤቅ” የሚባል ሲሆን ትርጉሙም “የይቅርታ ዕፅ” ማለት ነው (ዘፍ 22፥13 የሰብአ ሊቃናት ትርጉም)። በይስሐቅ ልጅ በያዕቆብ ዘመንም የመስቀል ምጢርና ምልክትም በሥራ ላይ ነበር። እርሱ በጎቹን በሽመልና በው አድርጎ አበዛቸው (ዘፍ 30፥3743)። ሽመሉ የእንጨት መስቀልን፣ ውው በውስጡ የመስቀልን ምጢር የያዘ ጥምቀትን የሚያመላክት ነው። ሐዋርያውም እንዲህ አለ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ እንደ ተጠመቅን አታውቁምን? (ሮሜ 6፥3)። ክርስቶስም ምእመናኑን በእንጨትና በው አበዛ፣ ይህም ማለት በመስቀልና በጥምቀት ነው።
ያዕቆብ በይወቱ ፍጻሜ ላይ ጎምበስ ብሎ የልጅ ልጆቹን እጁን አመሳቅሎ ሲባርካቸው (ዘፍ 48፥920) የመስቀልን ምልክት እጅግ ግልጽ በማድረግ ወደ ብርሃን አወጣ (በገሃድ አሳየ)። እርሱ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ለአባቶቹ ታዛዥ ነበርና ኤሳው ከመጀመሪያው ቢጠላውም የሚወደድና የተባረከ ነበር። እርሱ ሁሉንም ፈተናዎች በጥንካሬ ተቋቋመ። የመስቀል ምጢርም በይወቱ ሙሉ በሥራ ላይ ነበር። እግዚአብሔርም ያዕቆብን ወደድሁ ኤሳውን ግን ጠላሁ (ሮሜ 9፥13፣ ከሚልክያስ 1፥23 ጋር ያነጻጽሩ) ያለው በዚህ ምክንያት ነው። በእኛም ዘንድ ወንድሞች ሆይ ተመሳሳይ ነገር ይሆናል። አንድ ሰው ምድራዊና መንፈሳዊ አባቱን ልጆች ሆይ፥ ለወላጆቻችሁ በጌታ ታዘዙ በሚለው ሐዋርያዊው ትእዛዝ መረት ሲታዘዝ በዚህ ረገድ ልክ እንደ አንድያ ልጁ በእግዚአብሔር ዘንድ ይወደዳል (ማቴ 3፥17፣ 17፥5፣ ማር 1፥11፣ 9፥17፣ ሉቃ 3፥22፣ 9፥35፣ 2ኛ ጴጥ 1፥17)። ነገር ግን የማይታዘዘው ልጅ አንድያ ልጁን ፈጽሞ አይመስልምና በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነው። ጠቢቡ ሰው ሎሞንም ይህ እውነት ለያዕቆብና ለኤሳው ብቻ ሳይሆን በሁሉም ዘመን ላሉ ሁሉም ሰዎች እንደሆነ እንዲህ በማለት ግልጽ አድርጎልናል “የሚታዘዝ ልጅ በይወት ይኖራል የማይታዘዝ ግን ይጠፋል” (ምሳሌ 13፥1 የሰብአ ሊቃናት ትርጉም)።[3]
በእርግጠኛነት የመታዘዝ ልጅ የሆነው ያዕቆብ ታላቅ ወደሆነው የመስቀል ምጢር ደረሰ። ማለት የፈለግሁት ሰው ለኃጢአት ፈጽሞ የሚሰቀልበትን ለመልካም ነገር ያው የሚሆንበት የእግዚአብሔርን ራእይ ነው። በእርግጥ እርሱ ራሱ ስለ ራእዩና ስለ ድኅነቱ ይመሰክራል። እንዲህ ብሏልና እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ፥ ነፍሴም ዳነች” (ዘፍ 32፥30 የሰብአ ሊቃናት ትርጉም)።[4]በእኛ ዘመን ከተነት ጸያፍ ነገር በመናገር ከሚቀባጥሩት መናፍቃንን የሚከተሉት ሰዎች የት አሉ?[5]ያዕቆብ የእግዚአብሔርን ፊት እንደተመለከተ ያድምጡ። እርሱም ይወቱን ያላጣ ብቻ ሳይሆን፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደተናገረው ሰው አይቶኝ አይድንምና ፊቴን ማየት አይቻልህም አለ (ዘጸ 33፥20) ያለ ቢሆንም (ያዕቆብ ግን ፊቱን አይቶ) ዳነ። በእርግጥ አንዱ ፊቱ በቅዱሳን ሊታይ የሚችል ሌላው ፊቱ ደግሞ ከራእይ/ከመገለጥ በላይ የሆኑ ሁለት እግዚአብሔሮች ሊኖሩ አይችሉም። ርኩስ የሆኑ ሳቦችን አስወግዱ! በሚገለጥበት ጊዜ ለሚገባቸው ሰዎች  የሚታየው የእግዚአብሔር ፊት የባርይው መገለጫና ጸጋው ነው ። በሌላ መልኩ የማይታየው ፊቱ አንዳንድ ጊዜ “የእግዚአብሔር ባርይ” ተብሎ የሚራውና ከሁሉም መገለጥ ወይም ራእይ በላይ የሆነው ነው። “በጌታ ባርይ ፊት ማንም ይቆም ዘንድ አይቻለውም” (ኤር 23፥18)[6]አልያም የእግዚአብሔርን ባርይ የተመለከተ ወይም የገለጠ ማን ነው። ወደ እግዚአብሔርና ቅዱስ ወደሆነው የመስቀል ምጢር የሚደረግ ተመስጦ ክፋትንና የክፋት ደራሲ የሆነውን ርኩስ መንፈስ ብቻ ከነፍስ የሚያስወግድ ሳይሆን የምንፍቅና ትምህርቶችንም የሚያርቅ ነው። እንዲህይ ያለ ሳብ ለሚያቀነቅኑ ሰዎች ሳብ መልስ የሚሰጥና ከክርስቶስ ቅድስት ቤተክርስቲያን የሚለይና የሚያስወጣ ነው። (በዚህች ቤተ ክርስቲያን ውስጥም) የመስቀልን ጸጋና የባሕርይ መገለጫ  ከክርስቶስ መሰቀል በፊት በነበሩ አባቶቻችን መካከል ለማክበርና ለማወጅ መብትና ነፃንት አለን።
ይቀጥላል


[1]አግናጥዮስ የሚለው ስም “God beerier የሚል ትርጉም እንዳለው የታወቀና የተረዳ ነው። ሆኖም ግን ጎርጎርዮስ እያለ ያለው ይህ ስም ያለውን ሰው ሳይሆን ምጢራዊ በሆነ መንገድ ይህንን እውነትና ይወት የሚጋሩ አባቶችን በጋራ ነው። ይህም “Fathers በማለቱ ይታወቃል። “እግዚአብሔርን የተሸከመ” ማለት እግዚአብሔር ያደረበት፣ ከይወቱ ተካፋይ ሆነ፣ ከሥላሴ ጋር ኅብረት ያለው ማለት ነው። “እኛም አንድ እንደ ሆንን አንድ ይሆኑ ዘንድ፤ እኔም በእነርሱ አንተም በእኔ ስትሆን፥ በአንድ ፍጹማን እንዲሆኑ፥ የሰጠኸኝን ክብር እኔ ሰጥቻቸዋለሁ፤” (ዮሐ 17፥22፥23)
[2] እዚህ ጋር ጎርጎርዮስ የተጠቀመው የሰብአ ሊቃናት ትርጉም የሆነውን መጽሐፍ ቅዱስ ነው። በዚህ ትርጉም መሰረት “እነርሱም” ሳይሆነ “እርሱም” ይላል።
[3] እኛ በምንጠቀመው መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው እንዲህ ተብሎ ነው “ባለ አእምሮ ልጅ የአባቱን ተግሣጽ ይሰማል። ፌዘኛ ግን ተግሣጽን አይሰማም” (ምሳሌ 13፥1)
[4] እኛ የምንጠቀምበት የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ላይ እንዲህ ተብሎ ተጽፏል “እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ፥ ሰውነቴም ድና ቀረች” (ዘፍ 32፥30)
[5]ይህ Hesychast controversy እየተባለ የሚጠራው በ14 ክፍለ ዘመን በባይዛንታይን ግዛት ውስጥ የተደረገ የነገረ መለኮት ክርክር ነው። የዚህ ስብከት ደራሲ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ፓላማስ በርልአም/በርላም ከተባለ ሰው ጋር ያደረጉት ክርክር ነው። የትምህርቱ ዋና ጭብጥ በጽሞናና በተመስጦ የሚኖሩ ክርስቲያኖችን የሚያነጻና የሚቀድስ የእግዚአብሔር የግብሩ መገለጫ ወይም ያልተፈጠረው ብርሃን / energies or operations of God were uncreated/ እንዳለና ይህም ከእግዚአብሔር ባህርይ /Essense or Ousia/ የተለየ መሆኑን የሚያስተምር ነው። ሰው ሊያውቅና ሊመሰጥ የሚችለው የባህርዩ መገለጫዎችን ወይም ግብሮችን ብቻ ነው። ይህ ቅዱሳንን የሚያበራና የሚያነጻ ብርሃን በታቦር ተራራ ከተገለጠው ብርሃን ጋር አንድ ነው። በርልአም በምእራቡ አለም የተማረና የምስራቅ አባቶችን ትውፊት ጠንቅቆ የማያውቅ በመሆኑ ይህ ነገር ስህተት ነው በማለቱ ክርክር ተነሳ። በ 1341 ጉባኤ ተጠርቶ በጎርጎርዮስ ድል ተነሳና ተወገዘ። ከውግዘቱ በኋላ በርልአም የካቶሊክ ጳጳስ እንደሆነ ይነገራል። ይህ ትምህርት ከጥንት ጀምሮ በኦርቶዶክስ ትውፊት የነበረና የተረዳ ነው። እነ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ሦስቱ የቀጰዶቅያ አባቶች፣ ዮሐንስ ዘሰዋስው ያስተማሩት የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ነው። ማጠንጠኛውም የእግዚአብሔር ባህርይ በዚህኛው ዓለም ይቅርና በሚመጣው ህይወት ከሰዎች የተሰወረና ፈጽሞ ሊታወቅ የማይቻል ነው የሚል ነው።
[6]እኛ በምጥቀምበት የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም እንዲህ ተብሎ ነው የተጻፈው “ቃሉን ያይና ይሰማ ዘንድ በእግዚአብሔር ምክር የቆመ ማን ነውና? ቃሉንስ ያደመጠ የሰማስ ማን ነው?” የእንግሊዘኛውም የሰብአ ሊቃናት ትርጉም ከላይ ደራሲው ከተጠቀመበት ለየት ይላል። የአማርኛውም ትርጉም ከእንግሊዘኛው ሰብአ ሊቃናት ጋር የሚመሳሰል ነው። ደራሲው ከየትኛው ትርጉም እንደተጠቀመ ለማወቅ ሌላ ጥናት ይጠይቃል። “For who has stood in the counsel of the Lord, and seen  his word? who has hearkened, and heard”
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ
አዳዲስ መጻሕፍትን ይግዙ

ተዛማጅ ጽሑፎች

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ