መግቢያ » ልዩ ልዩ ሁለት » ወደ ክርስቶስ መገስገስ

የትምህርቱ ርዕስ | ወደ ክርስቶስ መገስገስ

የማወቅ ጥማትህ እግዚአብሔርን ለማወቅ የማይፈልግ ከሆነ ከንቱ ነው ፡፡ ስለ ምድር አውቀህ ስለ ሰማይ ዝንጉ ከሆንህ ፣ ስለሚጠፋው እንቅልፍ አጥተህ ስለማይጠፋው ከደነዘዝህ በእውነት ከንቱ ነህ ፡፡ የሚያውቀህን አምላክ ትተህ የማያውቁህን ዝነኞች ስታስስ መዋል ፣ ገና ፈሳሽ ሳለህ ሳትረጋ ያወቀህን ጌታ ገሸሽ ብለህ የካዱህን ስታስብ መኖር ፣ ወላጆችህ ሳያዩህ በዓይነ ምሕረት ያየህን እግዚአብሔር አለማየት ፣ ዓለም ሳይፈጠር የመረጠህን ምርጫህ አለማድረግ በእውነት ከንቱ ነው ፡፡ ደስታ የሌለው እውቀት ፣ ዕረፍት የሌለው ጥበብ እግዚአብሔርን ማወቅ የሌለበት ነው ፡፡
የተደበቁ ነገሮችን መሰርሰር ትፈልጋለህ ፣ በአደባባይ የተሰቀለውን ጌታ ለማየት ግን ዓይንህን ትጨፍናለህ ፡፡ ትንሽ ቆይቶ ቋንጣ የሚሆነውን ዜና ተሻምተህ ትሰማለህ የዘላለሙን ምሥጢር ግን ችላ ትላለህ ፡፡ የመድኃኒት ሰዓትህን ለማስታወስ ማንቂያ ደወል ትሞላለህ ፣ ቅዳሴ ለመሄድ ግን ሲቀሰቅሱህ ትቆጣለህ ፡፡ የኤምባሲ ቀጠሮህን አትረሳም ፣ ሞትን ረስተህ ግን እንዳሻህ ትናገራለህ ፡፡ ጦም መቼ ይያዛል የሚለውን ታውቃለህ ፣ ለምን እንደሚጦም ግን አትጠይቅም ፡፡ ፋሲካ መቼ ነው ? ብለህ በግ ትገዛለህ ፣ የታረደውን በግ ክርስቶስን ግን ገሸሽ ትላለህ ፡፡ ዘመን ሲለወጥ እንኳን አደረሳችሁ ትላለህ ያደረሰህን አምላክ ግን ከልብ አታመሰግንም ፡፡ ዘመን ሲጨመርልህ ከመለወጥ ያልጨረስከውን ክፋት ለመፈጸም እንደ ገና ታስባለህ፡፡ እባክህን አንተ ተወዳጅ ሆይ እግዚአብሔርን ማወቅ ሕይወት ልዑሉንም ማስተዋል ጥበብ ነው ፡፡ እርሱን ስታውቅ በማይናወጠው መንግሥቱ ያሳርፍሃል ፡፡ በማይለወጥ ባሕርዩ ያጸናሃል ፡፡ እንኳን ዘመን ተጨመረልን ፡፡ ዘመን ተለወጠ ፣ እኛም እንለወጥ ፡፡
ወደ ክርስቶስ መገስገስ 1
ተጻፈ በአዲስ አበባ
መስከረም 1 ቀን 2011 ዓ.ም.
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ

ተዛማጅ ትምህርቶች

የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ

አዳዲስ መጻሕፍት

ትርጉሙ:- ቀይ ዕንቈ

ለምድራችንና ለአገልግሎታችን በረከት የሆነ መጽሐፍ
የመጀመሪያ እትም ጥቅምት 2016 ዓ.ም

1ኛ ጢሞቴዎስ ትርጓሜ – ክፍል አንድ

የመጀመሪያ እትም ሐምሌ 2013 ዓ.ም

ምክር አዘል መጽሐፍ

የመጀመሪያ እትም