መግቢያ » ልዩ ልዩ ሁለት » ዕድሜአችሁን ሳብ ያድርገው !

የትምህርቱ ርዕስ | ዕድሜአችሁን ሳብ ያድርገው !

ዕድሜአችሁ እየገፋ ሲመጣ የምትማሩት ቁም ነገር አለ፡-

1- ሁሉም ሰው እንደ እኔ ያስብ ከሚል አዙሪት ትወጣላችሁ ።

2- ሁሉም ሰው ይወደኛል ከሚል ሞኝነት ትላቀቃላችሁ ።

3- ለመወደድ ብላችሁ የምትለፉትን ልፋት ትቀንሳላችሁ ።

4- ምቀኛ አያሳጣኝ ብላችሁ ትጸልያላችሁ ፣ ምቀኛ ራስን ያስችላልና ።

5- በማታ የተገኘ ዘመድ ንብረት ፈላጊ መሆኑን ትረዳላችሁ ።

6- ቅዱሱ ጌታ ያለው እንደማይቀር አምናችሁ መደንገጥና መሸበር ታቆማላችሁ ።

7- ሽንገላንና የቀዘቀዘ ሰላምታን ትጸየፋላችሁ ።

8- የማትወዱትን ሰው ለመውደድ ማስመሰል ታቆማላችሁ ።

9- በቁንጅናና በቁመና መማረክ ታቆማላችሁ ፣ ብዙ ጊዜ የላይ  ግንባታው ያማረ ውስጡ የፈረሰ ነውና ።

10- ከሩቅ ዘመድ የቅርብ ጎረቤት እንደሚሻል ገብቷችሁ ማኅበራዊ ኑሮን ታከብራላችሁ ።

11- በወደቀ ሰው መፍረድ ታቆማላችሁ ።

12- እፍ ያነዳል ፣ እፍ ያጠፋልና የወረት ፍቅርን ታርቃላችሁ ።

13- እያንዳንዱን ቀን እንደ መጨረሻ ቀናችሁ በማሰብ ሥራችሁን ይዋል ይደር ማለት ትጠላላችሁ ።

14- ወረቀት የያዘው ነገር ወሳኝ መሆኑን ታምናላችሁ ።

15- የሰውን አደራ ትመልሳላችሁ ።

16- በይሉኝታ ኃላፊነት ውስጥ መግባት ታቆማላችሁ ።

17- የሚወዳችሁ ጥቂት ሰው እንደ ሆነ ተረድታችሁ ለዚያ ሰው ትኖራላችሁ ።

18- ልጅም ቢሆን የሚወድደው ሲኖር መሆኑ ገብቷችሁ ማባከን ታቆማላችሁ ።

19- ስትናደዱ መናገርን ፣ ስትደሰቱ በስሜት ቃል መግባትን ትሸሻላችሁ ።

20- በማይመለከታችሁ በሰው ጉዳይ መግባት ታቆማላችሁ።

ዲያቆን አሸናፊ መኰንን

መጋቢት 8 ቀን 2017 ዓ.ም.

በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ

ተዛማጅ ትምህርቶች

የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ