13- እሺ እያሉህ የማይፈጽሙ ሰዎች በሕይወትህ ላይ እያለመጡ ነውና ውሳኔ አድርግ ።
14- ልግመኛ ሰዎች ጤናህን ያቃውሳሉና መክረህ ካልሆነ በጊዜ አርቃቸው ።
15- ሰዎች ምክርን እስካልፈለጉ ምሥጢራቸውን ለማወቅና ምክር ለመስጠት አትድፈር ።
16- ሰዎችን ሳታውቀው እንዳታስከፋ ጎሣና ሃይማኖትን የሚነካ ቀልድ አትናገር ።
17- የሳቀልህን አክብረው ፣ ነገር ግን ቋሚ ወዳጅህ ላይሆን ይችላል ።
18- ወደ ቤተ ክርስቲያን መሄድን እንደ ቀላል አትቍጠረው ።
19- መንፈሳዊ አማካሪ ይኑርህ ።
20- ውስጥህንና አሁን የተሰማህን ለሁሉ ሰው አትግለጥ ፣ ሰዎች በቀላሉ የሚያውቁህ ከሆነ ትናቃለህ ።
21- ከወዳጆችህ ጋር ካልሆነ ንግግርህ መጠን ይኑረው ።
22- ባለህ ነገር ለመደሰት ሞክር ።
23- ሊያስከፉህ ለሚፈልጉ መድኃኒቱ አለመከፋት ነው ።
24- ጸጸት የስህተት ካሣ አይሆንምና ራስህን ባለፈው ነገር አትቅጣ ።
25- ስላለፈው ከመቆጨት ስለ ነገ አስብ ።
26- ጀግና የሚሞተው በፈሪ ነውና ደካማ አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች ከመንገድህ እንዳያወጡህ ራስህን ግዛ ።
27- ማንንም ሰው ስትቀርብ ምን እሰጣለሁ ? እንጂ ምን አተርፋለሁ ? ብለህ አይሁን ።
28- ዕድሜህ እየገፋ ሲመጣ ወዳጅ ያንሳልና ያሉህን ወዳጆች አጥብቀህ ያዝ ።
29- ልቡናህ ከደፈረሰ የሚታይህ ሁሉ ጨለማ ይሆናልና ቂምን አርቅ ።
30- ወዳጅ የትም አይሄድም ብለህ አታቃልለው ። በግ ከበረረ ፣ ወዳጅ ካመረረ አይገኝም ።
ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ !