የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ

የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

የምስጋናዬ ድምፅ

                                                                                            አርብ፣ መስከረም 26 2004

ይገባዋል ለርሱ የምስጋና ነዶ
አድኖኛልና ከዙፋኑ ወርዶ
እርሱ ነው ጌታዬ እርሱ ነው አምላኬ
በደሙ ተፎ አበራ ታሪኬ
ሲያንሰው ነው ስግደቱ ያንሰዋል እልልታ
ሞትን በሞቱ ይል በድንቅ ለረታ

ምስጋና በፊቱ ይደረብለታል
የእልልታ ቅኔ ዙፋኑን ይሞላል
ይጨመርለታል የአምልኮ ስግደት
ለነፍሴ መናናት ሆኗታል በረከት
የዝማሬው ቅኔ እንደ ው ይፍሰስ
ተለውጫለሁኝ በልቤ መታደስ
አጨበጭባለሁ ነፍሴ በእርሱ ረክታ
ይደረብ ይጨመር ይብዛለት እልልታ
የምስጋና ነዶ እፊቱ ይከመር
ለነፍሴ ድቋ ነው ያሉ እግዚአብሔር
አመለኩት እርሱን ተገዛሁ በነፍሴ
ታላቅ ጥቅሜ ሆኗል ለርሱ መቀደሴ
በልጁ ደም ረጭቶ በመረቀው መንገድ
ታምኜ እጓዛለሁ በበጉ መታረድ
የወደቀው ጠላት በኔ ላይ ሀይል አጥቷል
የልጁ ደም ጋርዶኝ አርነቴ ታውቋል
ሐፍረቴ ተወስዷል ውድቀቴ ተሽሯል
በኢየሱስ ጌትነት ታሪክ ተለውጧል፡፡
እረማመዳለሁ በነጻነት መንገድ
በፍቅሩ ወላፈን ልቤ ፍሞ ይንደድ
እዘምራለሁኝ በደስታ ሲቃ
በሆነልኝ ነገር ነፍሴ ትነቃቃ
ይኸው ነው በእርሱ የመመረጥ
አረፍኩ ተቀመጥኩኝ በጌታ ፍቅር ውስጥ
የምስጋናዬ ድምጽ ወደ ላይ ይሰማ
የበረከት ትርፉ
           የመክበሬም ትርጉም
                      ሩ ነውና፡፡

በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ
አዳዲስ መጻሕፍትን ይግዙ

ተዛማጅ ጽሑፎች

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ