መግቢያ » ግጥም » የምስጋናዬ ድምፅ

የትምህርቱ ርዕስ | የምስጋናዬ ድምፅ

                                                                                            አርብ፣ መስከረም 26 2004

ይገባዋል ለርሱ የምስጋና ነዶ
አድኖኛልና ከዙፋኑ ወርዶ
እርሱ ነው ጌታዬ እርሱ ነው አምላኬ
በደሙ ተጽፎ አበራ ታሪኬ
ሲያንሰው ነው ስግደቱ ያንሰዋል እልልታ
ሞትን በሞቱ ኃይል በድንቅ ለረታ

ምስጋና በፊቱ ይደረብለታል
የእልልታ ቅኔ ዙፋኑን ይሞላል
ይጨመርለታል የአምልኮ ስግደት
ለነፍሴ መጽናናት ሆኗታል በረከት
የዝማሬው ቅኔ እንደ ውኃ ይፍሰስ
ተለውጫለሁኝ በልቤ መታደስ
አጨበጭባለሁ ነፍሴ በእርሱ ረክታ
ይደረብ ይጨመር ይብዛለት እልልታ
የምስጋና ነዶ እፊቱ ይከመር
ለነፍሴ ጽድቋ ነው ኃያሉ እግዚአብሔር
አመለኩት እርሱን ተገዛሁ በነፍሴ
ታላቅ ጥቅሜ ሆኗል ለርሱ መቀደሴ
በልጁ ደም ረጭቶ በመረቀው መንገድ
ታምኜ እጓዛለሁ በበጉ መታረድ
የወደቀው ጠላት በኔ ላይ ሀይል አጥቷል
የልጁ ደም ጋርዶኝ አርነቴ ታውቋል
ሐፍረቴ ተወስዷል ውድቀቴ ተሽሯል
በኢየሱስ ጌትነት ታሪክ ተለውጧል፡፡
እረማመዳለሁ በነጻነት መንገድ
በፍቅሩ ወላፈን ልቤ ፍሞ ይንደድ
እዘምራለሁኝ በደስታ ሲቃ
በሆነልኝ ነገር ነፍሴ ትነቃቃ
ይኸው ነው ምሥጢሩ በእርሱ የመመረጥ
አረፍኩ ተቀመጥኩኝ በጌታ ፍቅር ውስጥ
የምስጋናዬ ድምጽ ወደ ላይ ይሰማ
የበረከት ትርፉ
           የመክበሬም ትርጉም
                      ምሥጢሩ ነውና፡፡

በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ

ተዛማጅ ትምህርቶች

የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ