መግቢያ » መጽሐፍ ቅዱስ » አዲስ ኪዳን » 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች » የምንወድህ እናመሰግንሃለን

የትምህርቱ ርዕስ | የምንወድህ እናመሰግንሃለን

“ሥራ የሞላበት ትልቅ በር ተከፍቶልኛልና ተቃዋሚዎችም ብዙ ናቸው።” 1ቆሮ. 16፡9 ።
አንተ ከዘጋህ የሚከፍት የለም ፣ አንተ ከከፈትህም የሚዘጋ የለም ፤ አንተ ነሥተህ የሚሰጥ ፣ አንተ ሰጥተህም የሚነሣ የለም ። ዕድሜአችን ፣ ፍላጎታችን ፣ ራእያችን ሁሉ በእጅህ ነው ። ዓለም በክፋት ቢበረታም ገና በሥልጣንህ ሥር ነው ። አቅም አጥተህም የሚሸፍትብህ ግዛትና መንግሥት የለም ። የሁሉ የበላይ የመጨረሻም ዳኛ ነህ ። አንተ ይሁን ያልከው ይሆናል ። አንተ ስትረዳም ደካማው ብርቱ ነኝ ይላል ። የጠላት ብዛት አንተ ለእኛ ያለህን ዓላማ አይለውጠውም ። ጠላት በር ይዘጋል ፣ አንተ ግን ትከፍታለህ ። እንደውም በሩ መከፈቱን የሚነግሩን ተቃዋሚዎች ናቸው ። በሩ ሲከፈት የሚቃወም ይበዛል ። አንተ ስትነሣ ጠላት ይበሳጫል ። ጌታዬ ሆይ ተቃዋሚ ምልክት ነውና ደስ እንዲለን ፣ በውጊያ ውስጥም የምናስከብርህ ልጆችህ እንድንሆን እንለምንሃለን ። ያለ አንተ መሮጥ ግብ የለውም ። ያላንተ ማግኘትም ተድላ የለውም ። ያላንተ መጨረስ ለመጀመር ነው ። ያለ አንተ መውጣት ለመውረድ ነው ። አንተ ያለኸው ሰው ብቻ እርሱ የተከበረ ነው ። አንተ የተናገርኸው ይጸናል ። ያንተ ምክር የአሕዛብን ምክር ይመልሳል ። ሳይደክምህ ትሸከመናለህ ፣ ሳትሰለችም ትሰጠናለህ ። አንተን ማግኘት ሁሉን ማግኘት ነው ፣ አንተን ማጣትም ሁሉን ማጣት ነው ። ስለተዘጉ በሮች ሳይሆን በተከፈቱ በሮች ስለመሄድ አስተምረኝ ። በተከፈተው ስሄድ ያልተከፈተው ይከፈታል ። ከሁሉ በላይ አንተ የምትደሰትበት ሰው አድርገኝ ። መንግሥትህ ለልጅ ልጅ ፣ ግዛትህም መጨረሻ የለውምና እኛ የምንወድህ እናመሰግንሃለን ። ለዘላለሙ አሜን ።
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ

ተዛማጅ ትምህርቶች

የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ

አዳዲስ መጻሕፍት

ትርጉሙ:- ቀይ ዕንቈ

ለምድራችንና ለአገልግሎታችን በረከት የሆነ መጽሐፍ
የመጀመሪያ እትም ጥቅምት 2016 ዓ.ም

1ኛ ጢሞቴዎስ ትርጓሜ – ክፍል አንድ

የመጀመሪያ እትም ሐምሌ 2013 ዓ.ም

ምክር አዘል መጽሐፍ

የመጀመሪያ እትም