የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

የቅድስት ድንግል ማርያም ብሥራት /ክፍል2/

ሦስተኛው ስብከት
የሚከተለውን የሚመስል ትእዛዝ የተቀበለው ገብርኤል በስድስተኛው ወር ወደ ድንግል ተላከ ። “ሊቀ መልአክ አሁን ወደዚህ ና እና የዚህ ድንቅ የሆነው ተሰውሮም የነበረው ምጢር አገልጋይ በተአምሩም ወኪል ሁን ። እኔ የጠፋውን አዳም እመልስ ዘንድ በርዬ አዝኜ (ሰው ሆንሁ)በመልኬ ተፈጥሮ የነበረውን ኃጢአት አሳድፎታል፣ የእጄንም ራ አበላሽቶታል ፣ የራሁትንም ውበት አቆሽሾታል ። ተኩላው ልጄን በልቶታል ። የገነት መኖሪያው ባዶ ሆኗል፣ የይወት ዛፍ በሚገለባበጥ ሰይፍ ይጠበቃል ሐሤት ማድረጊያው ስፍራ ተዘግቷል ዬ በዚህ ጠላት ምክንያት ሆኗልና ይህንን ጠላት እይዘው ዘንድ እሻለው ። ላንተ ብቻ የገለጽልህን አሁንም ድረስ ከሁሉም የሰማይ ኃይላት የተሰወረውን ይህንን ምጢር እውረው ዘንድ እሻለሁ ። ስለዚህ አንተ ወደ ድንግል ማርያም ዘንድ ሂድ ። ነቢዩየእግዚአብሔር ከተማ ሆይ፥ በአንቺ የተከበረ ነገር ይባላል።/መዝ 86(87)፥3/ ብሎ ለተናገረላት ከፍ ላለው ወደዚህች ከተማ ሄድእንግዲህ ወደ ገነቴ ሂድ፣ ወደ ምራቋ ደጅ ሂድ ፣ ለቃሌ የተገባ ወደሆነው ጊዜያዊ ማረፊያዬ ሂድ ፣ በምድር ላይ ወዳለው ሁለተኛ ሰማይ ሂድ ፣ ብርህት ደመና ወደሆነው ሂድ የመምጣቴንም ዜና አብሥራት ። ለእኔ ወደተዘጋጀው ቅድተ ቅዱሳን ሂድ ፣ የሥጋዌ አዳራሽ ወደሆነቺው ሂድ ፣ በሥጋ የመወለዴ ንጽት እልፍኝ ወደሆነው ሂድ። ለእኔ የመደመጥን መንገድ ታመቻችልኝ ዘንድ ለምክንያታዊት/አእምሮአዊት/ለባዊት ታቦቴ በጆሮዋ ንገራት ነገር ግን የድንግልን ነፍስ እንዳታውክ አያም ንዳታበሳጭ። ለዚያች መቅደስ በሚመጥን መልኩ ራስህን ግለጥ አስቀድመህም በደስታ ድምሰላምታ ስጣት ። በጥፋት ውስጥ ላለው ለሔዋን ርአሳይ ዘንድ ማርያምን ‘ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ’ በሚለው ሰላምታ ሰላም በላት።”
ሊቀ መልአኩም እነዚህን ነገሮች ሰምቶ እንዲህ አለ፡- “ይህ እንግዳ ነገር ነው ። የተነገረው ነገር መረዳትንና እውቀትን የሚያልፍ ነው ። ለኪሩቤል የረድና የመንቀጥቀጣቸው ምክንያት ፣ ያ በሱራፌል ዘንድ ቀና ተብሎ የማይታየው ፣ ያ በሁሉም ሰማያውያን ኃይላት (መላእክት) የማይወሰነውና ከመረዳታቸው በላይ የሆነው በድንግል ማኅፀን ለማደር እንዴት ማረጋገጫ ሰጠን ? የራሱን መምጣት አስታወቀን ? ያ ሔዋንን የኰነነው ለልጇ እንዲህ ያለን ክብር ለመስጠት የፈጠነ ነውን ? “ለኔ የመደመጥን መንገድ ታዘጋጅልኝ ዘንድ”ሏልና ። ነገር ግን በቦታ የማይወሰነውን እርሱን ማፀን ይወስነው ዘንድ ይቻለዋልን ? በእውነት ይህ የሚያስፈራና የሚያስደነግጥ ምጢር ነው።” መልአኩ እንዲህ ባለ ሳብ ውስጥ ሳለ ጌታ እንዲህ አለው፡- “ገብርኤል ሆይ ስለ ምን እንዲህ ተጨነቅህ? ስለ ምንስ ግራ ተጋባህ ? ከዚህ ቀደም ወደ ካህኑ ዘካርያስ በእኔ አልተላክህምን? ለእርሱስ የዮሐንስን መነስ መልካም ዜና አልነገርከውምን ? ተጠራጣሪው ካህን ዲዳ ይሆን ዘንድ አልፈረድህበትምን ? ሽማግሌውን ሰው በዲዳነት አልቀጣውምን ? አንተ አዋጁን አውጀህ እኔም አላጸደቅሁትምን ? እውነታውስ/የኤልሳቤጥ መነስ የአንተን መልካም አዋጅ አልተከተለምን ? መካኗ ሴት አልነሰምን? ማኅፀኗ (ለተነገረው) ቃል ታዛአልሆነምን ? የመንነት ችግር አልራቀምን? የተፈጥሮ ግ አልተሻረምን? እርሷ/ኤልሳቤጥ አስቀድማ ንሳ የማታውቅ አሁን ወላድነትን የምታሳይ/ወላድ አይደለምን? ሁሉንም ለፈጠርለእኔ አንዳች የሚሳነኝ ነገር አለን ? ስለዚህ በመጠራጠር የምትናጠው ስለምንድን ነው?”
ለዚህ የመልአኩ መልስ ምንድን ነው ? መልአኩ እንዲህ አለ፡- “ኦ ጌታ የተፈጥሮን እንከንና ጉድለት ትፈውስ ዘንድ ፣ የይጣንን ማሰቃየት ፍጻሜ ትሰጥና ታጠፋ ዘንድ ፣ የሞቱትን ወደ ይወት ኃይል ትጠራ ዘንድ ፣ ተፈጥሮ ላይ የማስገኘትን ኃይል ትሰጥ ዘንድ የተፈጥሮን መስመር ያለፉትን ሰዎች መንነት ታጠፋ ዘንድ፣ ያረጀውንና የጠወለገውን ግንድ ወደ ለመለመ ኃያልነት ትለውጥ ዘንድ፣ ፍሬ አልባ የሆነውን አፈር በቅጽበት እልፍ ፍሬ እንዲያበቅል ትለውጠው ዘንድ ይህንን ሁሉ ማድረግ አስቀድሞ እንደነበረው ያንተን ኃይል ይፈልጋል ። ለዚህም ሣራ ምስክር ነች ። ከእርሷም በኋላ ርብቃ ፣ እንደገና ሃና ሁሉም በመንነት ፍርሃት ተገዝተው የነበረ ቢሆንም ከዚያ በኋላ ከበሽታቸው ይፈወሱና ነይወጡ ዘንድ በአንተ ዘንድ ተቸራቸው/ተሰጣ ። ነገር ግን ድንግል ከወንድ ጋር ሳትገናኝ ትወልድ ዘንድ ይህ ከሁሉም የተጥሮ ጎች በላይ ነው ። አንተ መምጣትህን ለዚያድንግል አሳውቀሃታልን ? ሰማይና ምድር ይሸከሙህ ዘንድ ያልቻሉትን አንተን እንዴት የድንግል ማፀን ይሸከምሃል?”
ጌታም እንዲህ አለ፡- “የአብርሃም ድንኳን እንዴት ቻለኝ ?” /ዘፍ 18/ መልአኩም መልሶ እንዲህ አለ፡- “እንግዳ መቀበል በእርሱ ዘንድ ነበረና ኦ ጌታ አንተ ራስህን ለአብርሃም በድንኳኑ ደጃፍ ላይ ገለጥህ። አንተም ሁሉንም እንደሚሞላ (ባርይህ) በፍጥነትም አለፍህ ። ነገር ግን ማርያም እንዴት የመለኮትህን እሳት እንዴት ቻለች ? ዙፋንህ ከድምቀቱ ብርሃን የተነይበራል ። ድንግል ሳያቃጥላት ትቀበልህ ዘንድ ይቻላታልን?”
ከዚህ በኋላ ጌታም እንዲህ አለ፡- “በእርግጥ አዎ። በበረሃ የነበረው እሳት ቊጥቋጦውን አቃጥሎት ቢሆን መምጣቴ ድንግልንም በእርግጥ ያቃጥላት ነበር ። ነገር ግን ይህ የመለኮታዊውን እሳት ከሰማይ መውረድ ምሳሌ የሆነው ያ እሳት ያን ቊጥቋጦ ሳያቃጥል ካለመለማት እንደ እሳት ነበልባል ሳይሆን እንደ ዝናብ ስለሚወርደው እውነት ምን ትላለህ ?”
ከዚህም በኋላ መልአኩ የተሰጠውን አገልግሎት ይፈጽም ዘንድ ራሱን አዘ ። ወደ ድንግልም ሄዶ እንዲህ በማለት ከፍ ባለ ድምተናገራት፡-ደስ ይበልሽ ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው ። ከዚህ በኋላ ርኩሱ መንፈስ/ሰይጣን አንቺን አይቃረንም ። በጥንት ጊዜ ያ ጠላትና ባላጋራ አቆሰለ አሁን ደግሞ ኪሙ/መድኅኑ የፈውስን ቅባት ቀባ መማችን ጎርፍ በሴት በኩል እንደመጣው በረከታችንም በሴት በኩል መነጨ ። ጸጋ የሞላሽ ሆይ ደስ ይበሽ! የመኰነናችን ምክንያት እንደሆንሽ አትፈሪ/ሃፍረት አይሰማሽ። አንቺ በአንድ ጊዜ ፈራጅና አዳኝ የሆነውን የእርሱ እናት ሆነሻልና ። የተኛው ዓለም ሙሽራ እናት የሆንው ነቀፋና ነውር የሌለብሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ! ከእናት ሔዋን የመጣውን ሞት በማፀንሽ ያሰጠምሺው ደስ ይበልሽ ! ከፍ ያልው የእግዚአብሔር መቅደስ ሆይ ደስ ይበልሽ ! የሰማይና የምድር እናት የሆንው ደስ ይበልሽ ! ወሰን የሌለው ባርይን የተሸከምሽ ደስ ይበልሽ !
ለበሽተኞች ኪም በእርሷ በኩል መጥቷል ፣ በጨለማ ለሚቀመጡ የእውነት ፀይ በእርሷ በኩል መጥቷል ፣ በማበል ለሚናጡና ለሚሰቃዩ በማበል የማይረበሸው መልህቅና ወደብ በእርሷ በኩል መጥቷል ። በማይታረቅ ጠላትነት ውስጥ ለሚኖሩ ባሪያዎች ጌታ ተወልዶላቸዋል ። የሰላም ዘመን ይሆን ዘንድ ወደ ባርነት የሄዱትም አዳኝ ፣ በጠላትነት ውስጥ ለነበሩት ሰላም ይሆን ዘንድ አንዱ በመካከላችን አደረ !
እርሱ ሰላማችን ነውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ቸርነት። ለእርሱም ምስጋና ፣ ክብርና ኃይል ይሁን ። አሁንና ለዘላለም እስከ ፍጻሜው/ለትውልደ ትውልድ ። አሜን! 
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ
አዳዲስ መጻሕፍትን ይግዙ

ተዛማጅ ጽሑፎች

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ