የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ

የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

የኑሮ መድኀን – መቅድም

የዲ/ን አሸናፊ መኰንን ገጽ……. ማክሰኞ ነሐሴ ፳፱/ ፳፻፬ ዓ/ም
የምትበላው መኖር ስላለብህ፣ የምትለብሰው አበደ እንዳይሉህ፣ የምፈቅረው ስለሚያሳዝኑህ፣ የምትረዳው ሕሊና ፀጥ እንዲልልህ ሊሆን ይችላል፡፡ እንደ ማሽላ እያረሩ መሳቅ ውስጥህንጎድቶት ይሆናል፡፡ ምስጥ እንደ በላው እንጨት ላይህ ገዝፎ ትንሽ ሲነኩህ የምትወድቅ ሆነህ ይሆናል፡፡ ስለገባው ገቢ እንጂ ስለወጣው የማያወቁ ምቀኛ ጎረቤቶች ያበሳጩህ፣ ሁሉም ነገር አልጥም ብሎህ በግድ የምትኖር ሰው ሆነህ ይሆናል፡፡ እንዲህ የምሆነው የመረጥኩትና የሰለጠንኩበት ትምህርቴ አሊያም በቀደመ አስተሳሰቤ ያገባኋት ሚስቴ ትክክለኛ ምርጫዬ ስላልሆኑ ነው እያልክ ትታመስ ይሆናል፡፡ ዛሬ ስታገኝ የድህነት ሚስትህና ጓደኞችህ ያን ክፉ ቀን መስለውህ ይሆናል፡፡ በምትኩ ደግሞ በሽንገላ ፍቅር አብደህ ይሆናል፡፡ ሲገባ ሰፊ ሲወጣ ጠባብ በሆነው፣ ማላመጥ እንጂ መዋጥ በሌለበት ፖለቲካ ውስጥ ገብተህ በሩ ጠፍቶህ እየተቍለጨለጭክ ይሆናል፡፡

          አርፍበለሁ ብለህ የገነባኸው ቤትህ ነገር የተጣደበት ምድጃ ሆኖብህ አሊያም የምትወደው ልጅህ በሕመም የሚንገላታበት ሆኖ ወደ ቤትህ የሚወስደውን ጎዳና ስትጀምር እግርህ እያጠረብህ ተቸግረህ ይሆናል፡፡ የሞቀው ትዳርህን ስብ ከመሐል አንዳችን ብንቀነስ ልጆቹ ምን ይሆናሉ? የሚል ፍርሃት እየወዘወዘህ ሊሆን ይችላል፡፡ ብር ካለ በሰማይ መንገድ አለ በሚል ፈሊጥ ተይዘህ ገንዘብ የሁሉም ነገር መልስ መስሎህ ፍቅርን እየገፋህ ገንዘብከማች ይሆናል፡፡ የአገሬ ሰው የሚያከብረው ሲወፍሩ ነው ብለህ ጭንቀትህን በምግብ እየተወጣኸው ይሆናል፡፡ ገንዘብ ሲመጣ ሰላሜ በየትኛው በር እንደ ወጣ አላውቅም እያልክ ይሆናል፡፡
          ብዙ ሕዝብ እየወደደህ ይህ ሁሉ ተከ ቢከዳኝስ እያልክ ተጨንቀህ ይሆን? ወይስ አመስግና በምትራገመው ዓለም ተራው ደርሶህ ያመሰገነህ ሁሉ ሰድቦ እስኪጨርስ ወረፋው ረዝሞብህ ይሆን? ከክብርህና ከሥልጣንህ የተነሣ እንኳን ጠላቶችህን ወዳጆችህን ማመን ተስኖህ ጥላህን እየፈራህ የምትኖር ሆነሃል?
          በማያስተማምን ፖለቲካ ቤት ሠርቶ ከባድ ማሽን ተክሎ መኖር እያስጨነቀህ ያላረፈ ልብ ይዘህ ሊሆን ይችላል፡፡ ወይም መብራት ጠፍቶ፣ ጉንዳን ገብቶ፣ እርሱሞ፣ ሚስቱ ምጥ እንደ መጣባት ሰው ሆነሃል? ለነገ የሚሆን በጎተራህ ስለ ሌለ ዕረፍት አጥተህ ይሆን? ብቻህን ለምወራው፣ ጭር ባሉ መንገዶች ለምታለቅስ፣ በሰው ልቅሶ ለራስህ ኑሮ ለምላዝን፣ በወዳጅና በትዳር መካከል ብቸኝነት ለፈጀህ፣ ቋንቋህ ሰሚ ላጣው፣ ከዚህ ሁሉ በላይ በነገ ፍርሃት ለተያዝከው ወገን የኑሮ መድንህ ማን ነው?
          በሰለጠነው ምድር ኢንሹራንስ ያልተገባለት ማንኛውም ተንቀሳቃሽ ንብረት መንቀሳቀስ አይችልም፡፡ የጤናና የሕይወት ዋስትና ያልገቡ ሰዎችን መቅጠርም ባለ ሀብቶች ይፈራሉ፡፡ በከፍተኛ በጀት የሚንቀሳቀሱ የዋስትና ተቋማትም መኪና ለወደመበት ያንኑ የሚያህል መኪና፣ ቤት ለተቃጠለበት ተካካይ ቤት ይሰጣሉ፡፡ ምንም እንኳ የሕይወት ኢንሹራንስ ቢያስገቡም ሕይወት ላጣ ሕይወትን ሰጥተው አያውቁም፡፡ በለማ ከተማ ፍርሃት ለሚንጠው፣ የውስጥ ጥያቄ ለወጠረው፣ ጣራ ሲቆጥር ለሚያድረው እንቅልፍ ብርቁ፣ ትዳሩ አክሲዮን ለሆነበት፣ ሀብቱ እርካታ ለነሣው፣ በጦርነት ቀጠና ለሚኖረው፣ የፍቅር ረሀብ ላጠወለገው፣ ወዳጅ ሁሉ የተልባ ስፍር ለሆነበት፣ ነገ ጨለማ ሆኖ ለሚየው ዋስትና የሚሰጥ የኢንሹራንስ ተቋም የለም፡፡ እንዲህ ያለውን ዋስትና ሰጪ  ቢያገኙ የኢንሹራንስ ተቋሙ ባለቤትም ይፈልጉት ነበር፡፡ዲያ የኑሮ መድ ማን ነው?

          ይህን ሁሉ ሕመማችሁን የነካካሁት እየቆነጠጡ ማስለቀስ እንደሚወዱ ሰዎች ሆኜ አይደለም፡፡ ስለ ኑሮ ሳነሣም ጆሮን ለመማረክ ብዬም አይደለም፡፡ ለእናንተ እንደምናገር ባስብ ኖሮ ብዕሬን አስቀምጥ ነበር፡፡ ከድካሜና ከሩጫዬ በኋላ እፎይ የምልበት ቃል ለራሴ እያዘጋጀሁ እንደ ሆነ ግን አውቃለሁ፡፡ ይህን የምጽፈው ቃለ መጠይቅ አድርጌ ሳይሆን ራሴን አይቼ ነው፡፡
          እኔም ለእኔ ያለሁት እኔ ብቻ እየመሰለኝ የባዘንኩበትን ዘመን አውቃለሁ፡፡ ሰዎች በሕይወቴ ወሳኝ የሆኑ እየመሰለኝ ሲወዱኝ የምኖር፣ ሲጠሉኝ የምጠፋ ይመስለኝ ነበር፡፡ የትልልቅ ሰዎችን ስልክ መያዝ እንደ ቡዳና መጋኛ መድኒት የኪሴ መሣሪያ ይመስለኝ ነበር፡፡ የእግዚአብሔርን ሳይሆን የሰውን ፊት እያየሁ ያገለገልኩበት ዘመን ብዙ ነው፡፡ ጊዜዬን እንጂ ሕይወቴንና ክብሬን አስቀምጬ  ማገልገል ባለ መቻሌ ሩጫዬ ሁሉ የብቻ ሩጫ እንደ ነበር ተገንዝቤአለሁ፡፡ ስህተትን በስህተት ለማጥራት በመሞከር አእምሮዬን ለብዙ ዘመን እንዳቆሰልኩ እግዚአብሔር በሰጠኝ የፀጥታ ጊዜዎች አውቄአለሁ፡፡
          ምድር ለተሸከመችኝ እነርሱ ከብዷቸው ብዙ ያሉኝ ወገኖች አሉ፡፡ ለመወደድም ለመጠላትም ጊዜ አለውና ሁለቱንም አይቼ ሕይወት እንዲህ ነው? ያልኩበት ጊዜ ብዙ ነው፡፡ መርዝ የተቀላቀለበት ሰላም  ብዙ ጊዜ ተቀብዬአለሁ፡፡ «እየወጉ ይማርህ» የሚሉ የከበቡኝ ጊዜ ጥቂት አይደለም፡፡ ስለ ከዱኝ ባልንጀሮቼ ሰዎች ሲጠይቁኝ ውስጤ እያረረ ደህና ናቸው ስል መልሰው «አቤት የእናንተ ፍቅር» ሲሉኝ ደግሞ ራሴን ጠይቄአለሁ፡፡ በዚህ ሁሉ ወጀብ ውስጥ ግን የተረዳኹት እግዚአብሔር ቁም ሳይል ሕይወትን የሚያቆማት እንደ ሌለ ነው፡፡ በርግጥም የኑሮ መድኅን እግዚአብሔር ነው፡፡
መግቢያ
ችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚስቡ ቃሎች ብቻ ሳይሆን የሚስብ ፍቅርም ነበረው፡፡ በረሃው ዓለም ላቃጠለው ቃሎቹ ጥም ቆራጭ ፍቅሩም ማረፊያ ጥላ ነበር፡፡ የተናገራቸው ቃሎች ፊደል ሳይሆኑ ሕይወት፣ ፍልስፍና ሳይሆኑ መንፈስ ነበሩ (ዮሐ.6፡63)፡፡ ከተናገራቸው ሕይወት አድን ቃሎች በማቴዎስ 1128 ያለው ቃል ልብን የሚገዛ ቃል ነው፡«እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፣ ወደ እኔ ኑ፣ እኔም አሳርፋችኋለሁ፡፡»
 ሁላችንም ወደ እግዚአብሔር ለመምጣት እንፈልጋለን፡፡ ነገር ግን ይህን ሱስ፣ ይህንጢአት ስተው፣ ንጹሕ ስሆን ነው የምመጣው እንላለን፡፡ ነገር ግን ራሳችንን አጽድተን መምጣት ብንችል ኖሮ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ መሞት ባላስፈለገው ነበር፡፡ እርሱ የሞተው ሰው ራሱን ጢአት ማዳን ስላልቻለ ነው፡፡ በምድር ላይ የሚገኙት ሃይማኖቶች ሰው ወደ እግዚአብሔር መምጣት ያለበትጥቦናጥኖ፣ ፀድቶና ተለውጦ ነው ይላሉ፡፡ ክርስትናው ግን የምንፀዳውና የምንለወጠው ወደ ክርስቶስ ስንመጣ እንደሆነ ይነግረል፡፡ ሰው ራሱን ለማዳን አምላክነት ያስፈልገዋል፡፡
ንስሐን በሚመለከት በሃይማኖቶች ሁሉ ያልተቋጨ ክርክር አለ፡፡ አንደኛው ወገን ሰው ወደ ክርስቶስ መምጣት ያለበት አስቀድሞ ንስሐ ገብቶ ነው ሲል ሌላው ወገን ደግሞ ንስሐ የሚገባው ወደ ክርስቶስ ሲመጣ ነው ይላል፡፡ጢአተኛው ንስሐ ለመግባትጢአቱን በንጹሕ መስወት ማየት፣ ተጸጽቶ ለመወሰን እርሱን አፍቅሮ የሞተለትን ጌታ መመልከት ያስፈልገዋል፡፡ በክርስቶስ የቅድስና ብርሃን ፊት ካልቆመጢአቱ ሊታየው፣ በቀራንዮ ፍቅር ፊት ካልቆመ የበደሉ ክብደት ሊታየው በፍጹም አይችልም፡፡ ስለዚህጢአተኛው አስቀድሞ ወደ ክርስቶስ ይመጣል፡፡ ከዚያም ልቡ ለንስሐ ይዘጋጃል፡፡ ለኃጢአተኞች የበደልን ፍርድ ከመንገራችን በፊት የበደላቸው ስርየት የሆነውንላቁን ፍቅር ልንነግራቸው ይገባል፡፡ ለዚህ ነው «እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፣ ወደ እኔ ኑ፣ እኔም አሳርፋችኋለሁ» ያለው፡፡
ብዙ ክርስቲያኖች የበደል ሸክም ተጭኗቸው ቀድሞ ወደ ክርስትና ሲመጡ የነበራቸው ደስታ ርቋቸዋል፡፡ ሌሎችም እግዚአብሔርን እየበደልኩት እንዴት በቤቱ እኖራለሁ? በማለት በአጉል ትሕትና ተይዘው ወደ ዓለም ኮብልለዋል፡፡ እንደ እነርሱ አሳብጢአትን ለማድረግ በሚቻልበት ቦታ ሆነው ኃጢአቸውን እየፈጸሙት ነው፡፡ጢአትን ሳይጨርሱት ንስሐ መግባት ግድ ነው፡፡ የተቀሩትም በድፍረትጢአት ተይዘው ብከፋ ብከፋ ከእነ እገሌ አልከፋም እያሉ በመሻል መስፈርት ተረጋግተው ተቀምጠዋል፡፡ የሚበዙትም «የሃይማኖት አባቶች ይህን እያደረጉ በእኛማ ምን ይፈረዳል?» እያሉ ከንስሐ ርቀው ይኖራሉ፡፡ ነገር ግን እነዚህ ሰዎች አንድ የሃይማኖት አባት ምን ማድረግ እንዳለበት የሚያውቁ ከሆነ እውቀታቸው ከሃይማኖት አባቶች በላይ በመሆኑ ይበልጥ ይፈረድባቸዋል፡፡
ብቻ ደካማነችን ከተሰማን ጥሪው ይመለከተናልና ወደ ጌታችን ቀርበን «ጌታ ሆይ፣ በጎ የመሆን ፍላጎት እንጂ አቅም የለኝም፡፡ ሙከራዎቼ ሁሉ ሊለውጡኝ አልቻሉም፡፡ አንተ ብቻ ትለውጠኛለህና እንደ ቃልህ አሳርፈኝ» ብለን መጸለይ አለብን፡፡
ከበደል ባሻገር የኑሮ ሸክም የተጫናቸው ብዙ ወገኖች አሉ፡፡ እንደ አገልጋይነችንም ያሳዝኑናል፡፡ የሚያሳዝኑን በችግር ውስጥ ስላሉ ብቻ ሳይሆን ሊረዳቸው የተዘረጋውን የእግዚአብሔርን እጅ ማየት ባለመቻላቸውም ነው፡፡ እንደ ሳማ በሚለበልብ ትዳር ውስጥ የሚኖሩ፣ ምግባረ ብልሹ ልጆችን የተሸከሙ፣ ጣዕም በሌለው ባለጠግነት የሚዋኙ፣ ሰላም በራቀው ቤተሰብ የሚኖሩ፣ ጉድለት በሚፈራረቅበት ኑሮ የሚንገላቱ፣ ሥር በሰደደ በሽታ
የተያዙ፣ የስህተታቸውን ዋጋ ከፍለው መጨረስ ያቃቸው፣ ዝም ብለው በአሳብና በጭንቀት ማዕበል የሚንገላቱ፣ በፍቅር እጦት ምክንያት የብቸኝነት ብርድ የሚያንዘፈዝፋቸውሰዎች በዙሪያችን አሉ፡፡ ይህን ጽሑፍ ለመጻፍ በተነሣው በመጀመሪያው ቀን እንኳ በስልኮቼ አሰቃቂ የሆኑ ልቅሶዎችን ሰምቻለሁ፡፡ እነዚህ አልቃሾች ይህን ጽሑፍ እንድገፋበት ረድተውኛል፡፡
በዚህ ሁሉ የሰቀቀን ድምፅ ውስጥ «እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፣ ወደ እኔ ኑ፣ እኔም አሳርፋችኋለሁ» የሚለው ድምጽ የኑሮ መድ ነው፡፡
የተሸከምነውን ሸክም እንደ ተሸከምን ለመጓዝ ካልቻልንክሲ እንጠብቃለን፡፡ክሲው ሲመጣ ሸክማችንን ለታክሲው አሸክመን በታክሲው ምቾት ተዝናንተን እንጓዛለን፡፡ የመንገዱንም ጉዳይ ለሾፌሩ ስለጣልነው ዓይናችንን ጨፍነን እናዜማለን፡፡ እንዲሁም
በእምነት ወደ ክርስቶስ ስንመጣ የሚከብደንን ሸክም ሁሉ ለእርሱ ትተን በዕረፍቱ አርፈን መጓዝ ይገባናል፡፡ ሸክም ያለ ቦታው አያርፍም፡፡ የሚያንገደግድ ሸክም ተሸክሞ ላቡ እንደ ውሀ እየጎረፈ የሚጓዘው ሰው ለምን አይጥለውም? ብንል ሸክም ያለ ቦታው ስለማያርፍ ነው፡፡ እንዲሁም የሕይወትና የኑሮ ሸክማችንን  ከክርስቶስ በቀር የሚያሳርፍልን ማንም የለም፡፡
በዛሬው ዘመን ሰዎች ሁሉ ሲገናኙ የሚለዋወጡት የእግዚአብሔርን ሰላም ሳይሆን ፍርሃታቸውን ነው፡፡ የአንዱ ፍርሃት ከሌላው ይለያል፡፡ የተቃጠለ አየር ስለሚለዋወጡ ጥቂት እንደ ቆዩ ነፍሳቸው በፍርሃት ፈናለች፡፡ ይልቁንም በአንደበታችን የሽንፈት ቃሎች ስንናገር የእግዚአብሔርይል እየራቀን ይመጣል፡፡ እንደ ዋዛ የምንናገራቸው «እግዚአብሔር ቢኖርማ እንዲህ ይሆን ነበር? የእኔ ዕድል ጠማማ ነው፡፡ አልፎ አወራው ይሆን? . . .» የሚሉት ንግግሮች የተለመዱ ስለሆኑ ምንም አይመስሉንም እንጂ የጭንቀትን ዘመን የሚያራዝሙብን ናቸው፡፡ ሰይጣን መረጃ የሚያገኘው ከአንደበታችን በመሆኑ የሽንፈት ቃሎች ስንናገር አሁንስ ደክሞታል ብሎ ጦር ያስከትትብናል፡፡ ይህን ስንል ልባችን ወድቆ በአንደበታችን እናስመስል ማለት አይደለም፡፡ ከእግዚአብሔር አቅም በላይ የሆነ ፈተና አልገጠመንምና ልባችንም አንደበችንም ሊፀና ይገባዋል፡፡ ድካማችንንም በጸሎት ለእግዚአብሔር መንገር ያስፈልገናል፡፡
በሰለጠነው ዘመንና ዓለም ሁሉም ነገር ዋስትና ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ሰዉ፣ መኪናው፣ ቤቱዋስትና አለው፡፡ የዋስትና ተቋማትም በታማኝነት መኪና ሲጠፋ መኪና ይተካሉ፡፡ ዋስትናችንን አሳድገናል በማለትም ሰዎች የሕይወት ዋስትና እንዲገቡ ያባብላሉ፡፡ ነገር ግን ለጠፋ ሕይወት ገንዘብ እንጂ ራሱን ሕይወት ሲተኩይተው አያውቁም፡፡ ስለዚህ ዋስትናቸው ከቁሳቁስ አያልፍም፡፡ ላዘመሙ ትዳሮች፣ መረን ለሆኑ ልጆች፣ ለታወከች ነፍስ
መፍትሔ የላቸውም፡፡
የምንኖርበት ዓለም ጥፋትና ክስረት የሚፈራረቅበት በመሆኑና ዘወትርም በልዩ ልዩ አደጋዎች ውስጥ ስለምናልፍ ዋስትና እንፈልጋለን፡፡ እኛ የምንፈልገውን ዋስትና የታወቁ የኢንሹራንስ ድርጅቶች ሊያሟሉት አይችሉም፡፡ እኛ ራሳችንን አልተቀበልነውም፣ ሰላማችን እንደ ባሕር የሚነዋወጽ ነው፣ በትዳር ምርጫችን ደስተኞች አይደለንም፡፡ዲያ የኑሮ መድ ናችን ማን ነው? ብለን መጠየቃችን አይቀርም፡፡ የዚህ መጽሐፍ ዓላማ በማዕበልና በፍርሃት ለሚንገላቱ ወገኖቻችን የነፍሳቸውን መልሕቅ ለመወርወር ነው፡፡ መጽሐፉ ያሳያል እንጂ አንባቢውን ተክቶ አይደርስም፡፡ እውነቱን ይናገራል እንጂ ለአንባቢው አያምንለትም፡፡
የመጽሐፉ ፍሰት ከብሉይ ኪዳን እስከ አዲስ ኪዳን እግዚአብሔር ለእኛ ሕይወት ያለውን ዕቅድ ያሳያል፡፡ የዓለምን ከንቱነትና የእግዚአብሔርን ቋሚነት ለማሳየት ይጨነቃል፡፡ እያንዳንዱን ምዕራፍ አንባቢው ሲጨርስ የጽሞና ጊዜ በመጠየቅ ከአንባቢው ጋር ይደራደራል፡፡ የአንባቢው እሺታ በራሱ ኃይል የለውምና ወደ ጸሎት ያልፋል፡፡ መጽሐፉ አንባቢው ከአምላኩ ጋር እየተገናኘ በጸሎት መንፈስ ሆኖ እንዲያነበው የተዘጋጀ ነው፡፡ ብዙ ሀዘንተኞች የጽሑፉን ጅምር አይተው እንድፈጽመው ከዓመት በላይ ወትውተውኛል፡፡ እናንተም እንደምትበረቱበት ጸሎቴም እምነቴም ነው።
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ
አዳዲስ መጻሕፍትን ይግዙ

ተዛማጅ ጽሑፎች

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ