የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

የእውነት ፈርጦች

ካህኑ አባ ኢሳይያስ እንዲህ አለ ፡- “ከአባቶች አንዱ ፣ አንድ ሰው ከሁሉም ነገር በፊት እግዚአብሔርን ማመን ፣ ሳያቋርጥ እግዚአብሔርን መናፈቅ ፣ የህነት ፣ ክፉን በክፉ አለመቃወም ፣ ትናና ራስን ማዋረድ ፣ ንጽሕና ፣ ርና ለሁሉም የሆነ ፍቅር ፣ መዛት ፣ እርጋታ ፣ ትትና ቻይነት ፣ እግዚአብሔርን መፈለግ ፣ ዘወትር በተሰበረ ልብና እውነተኛ በሆነ ፍቅር እግዚአብሔርን መጥራት ፣ ያለፈው ነገር ላይ ትኩረት ባለማድረግ የሚመጣውን መጠበቅ ፣ በራስ መልካም ሥራዎችና አገልግሎቶች አለመታመን ፣ በየቀኑ ለሚገጥሙት ነገሮች ሳያቋርእግዚአብሔርን መለመን አለበት” ይል ነበር ። (አባ ኢሳይያስ ፣ የምነና ንግግሮች ፣ 23)
ይህ ታላቅ አባት አንድ ክርስቲያን ስለሚያጠልቀው የጽድቅ ልብስ ፣ ስለሚጎናጸፈው ቀጸላ ፣ ስለሚደርበው ካባ ፣ ስለሚደረድረው ኒሻን እየተናገረ ነው “በውኑ ቆንጆ ጌጥዋን ወይስ ሙሽራ ዝርግፍ ጌጥዋን ትረሳለችን ? ሕዝቤ ግን የማይቈጠር ወራት ረስቶኛል” ይላል ኤር. 2፡32 እግዚአብሔርን መታዘዝና ማምለክ ከቆንጆ ጌጥ ፣ ከሙሽራም ዝርግፍ ጌጥ ጋር ተመሳስሏል የእግዚአብሔር ሕዝብ እግዚአብሔርን ማሰብ አለበት አሊያ ማልዶ እንደ ተነሣ ራሱንም እንዳላጸዳ ሰው ውበት የራቀው ይሆናል ሰዎች ሳያርቁት ራሱን ያርቃል ፣ “አልታጠብኩም ሰላም አልላችሁም” ይላል ርቆ ከመሄድ ፣ ክብር ካለው ስፍራና ሰዎች ከመገናኘት ራሱን ያግዳል ይህ አባትም የምእመንን ጌጥ እየነገረን ነው ጌጥ ውበትን ማውጫና ያልረኩበትን ቁንጅና መሸፈኛ ነው የምእመኑ ጌጦችም የሃይማኖትን ውበት የሚያወጡ ፣ ያለፈውን ዘመን ጉድለቶች የሚክሱ ናቸው እነዚህም፡-
1-  እግዚአብሔርን ማመን፡- የሰው ልጅ ከማመን ነጻ አይደለምና እግዚአብሔርን ካላመነ ራሱንና ሰዎችን ወይም አጋንንትን ያምናል ራስን ስለ መካድ ወንጌል ሲናገር ራስን ማመን እንዳለ እያሳየ ነው እግዚአብሔርን ማመን ማለት ቢያንስ ሦስት ነገሮች አሉት፡- ከእግዚአብሔር አሳብ ጋር መስማማት ፣ በእግዚአብሔር መተማመንና በእግዚአብሔር ማረፍ ወይም እፎይ ማለት ነው
2-  ሳያቋርጥ እግዚአብሔርን መናፈቅ ፡- ነቢዩ ዳዊት፡- “ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ፥ አቤቱ፥ እንዲሁ ነፍሴ ወደ አንተ ትናፍቃለች” ይላል ዋላ ውኃ ከመውደዷ የተነሣ ከውኃ ዳር አትለይም ውኃው የሚናፍቃት አጠገቧ እያለ ነው እግዚአብሔርንም በማያቋርጥ ናፍቆት መናፈቅ ይገባል አሁንም ዝማሬ ፣ አሁንም ጸሎት ፣ አሁንም ምስክርነት ስለ እርሱ ማቅረብ ይገባል ይልቁንም ቤተ ክርስቲያን ላለፉት ሁለት ሺህ ዓመታት አጠገቧ ያለውን ጌታ “አሜን፥ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ና” ትለዋለች ራእ. 22፡20 ሙሽሪት ናትና ሙሽራዋን ትናፍቃለች ሙሽራዋን የማትናፍቅ ምእመን ሌላ ሙሽራ አበጅታለች ማለት ነው
3-  የዋህነት፡- እውቀት ያለበት ትሕትናና ፍቅር እርሱ የዋህነት ይባላል እያወቁ መብትን መተዉ ፣ እንደ ሞኝ እየተቆጠሩ ማፍቀር መቻል እርሱ የዋህነት ነው የዋህነት የእውቀት ዳርቻ ነው የዋህነት የእውቀትም ዓላማው ነው የዋህነት የሰውን ልጅ ሁሉ መውደድ ፣ የዋህነት ለሁሉ መራራትና አክሞ መስማት ነው የዋህ የሚያጠፋ ሰው ቀድሞ የጠፋ ሰው መሆኑን በመገንዘብ ይራራል የዋህነትና ሞኝነት የተለያዩ ናቸውና ልናምታታቸው አይገባም
4-  ክፉውን በክፉ አለመቃወም፡- የአንድ ወገን ተኩስ ጦርነት አይባልም ፤ ጦርነት የሚባለው የሁለት ወገን ተኩስ ነው ክፉውን በክፉ መቃወም ሰዎች ስሜንና ጥቅሜን ነኩት ብሎ ሰብእናን መጣል ነው ክፉውን በክፉ የሚቃወም ሰዎች ከሚነሡት ራሱ የሚጥለው ይበዛል ክፉዎች ይጉዱህ እንጂ መልካም ጠባይህን ሊወስዱብህ አይገባም
5-  ትሕትናና ራስን መዋረድ፡- ከፊት ለፊት ለሚመጣው ሰው ዝቅ ስንል አይገባም ብሎ ከፍ ያደርገናል ትልቅ ሰው ከፍ እንዲያደርገን አስቀድመን ራሳችንን ዝቅ ማድረግ አለብን ኃይለኛው እግዚአብሔርም ከፍ እንዲያደርገን በትሕትና መዋረድ ይገባናል ትሕትና ለአንዳንድ ሰዎች የምናደርገው የሥራ ልብስ ሳይሆን ሁልጊዜ ሊገኝብን የሚገባ የኑሮ ዘይቤ ነው እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይበቀላል
6-  ንጽሕና፡- የእግዚአብሔር ሕዝብ በሥጋም በነፍስም ንጹሕ መሆን ይገባዋል ኅሊናን ከከንቱ ምኞት ፣ አንደበትን ከሽንገላ ፣ ተግባርን ከግፍ ሥራ ማንጻት ይገባል
7-  ና ለሁሉም የሆነ ፍቅር፡- ፍቅር እውነተኛ የሚሆነው ሲራራ ነው ፍቅር ሰው ሁሉ ድጋፍ እንደሚያስፈልገው ያስባል ፍቅር “ወንድሜ ከየት ያመጣል ?” ይላል እንጂ “ይኖረዋል ደብቆ ነው” አይልም ፍቅር “ወንድሜ እርቦት ይሆናል” ይላል እንጂ “በልቶ መጥቶ ይሆናል” አይልም ፍቅርና ርኅራኄ ለሁሉም የሰው ልጅ ፣ ለተፈጥሮም መስጠት ይገባናል
8-  ዛት፡- ለእውነት ፣ ለበላዮች ፣ ከሁሉ በላይ ለእግዚአብሔር መገዛት ያስፈልጋል ነጻነት ማለት ነጻ ሰው ማለት አይደለም ሰው ከበላይ የሚያከብረው ከሌለው ሕይወቱ ውድቀት ያጠላበት ይሆናል
9-  እርጋታ፡- በአነጋገር ፣ በእርምጃ ፣ በውሳኔ ፣ በፍቅር ፣ በፍርድ ፣ በአመራር ፣ በቃል መግባት እርጋታ ያስፈልጋል ሁሉም ነገር በታቀደለት መርሐ ግብር እየሄደ ነውና የሰው ችኮላ የትም አይደርስም
10-         ትና ቻይነት፡- ትዕግሥት እያረሩ መሳቅ ሳይሆን ነገሮች ይለወጣሉ በሚል ተስፋ መደሰት ነው ትዕግሥት እያነሰ ሲመጣ የበሉትን አላምጦ ለመዋጥም መፈተን ይመጣል
11-         እግዚአብሔርን መፈለግ፡- በእያንዳንዱ እርምጃ እነ እገሌ ከእኔ ጋር አሉ ወይ ? ሳይሆን እግዚአብሔር ከእኔ ጋር አለ ወይ ? ማለት ይገባል እግዚአብሔርን የማናይበት ጅምርም ሆነ የተገባደደ ነገር ጥቅም የለውም
12-         ዘወትር በተሰበረ ልብና እውነተኛ በሆነ ፍቅር እግዚአብሔርን መጥራት፡- እግዚአብሔር የሚለመነው ለተሰበረ ልብና ለእውነተኛ ፍቅር ነው አምልኮም ልምምድ ብቻ ሳይሆን ፍቅርም ሊሆን ይገባዋል
13-         ያለፈው ነገር ላይ ትኩረት ባለማድረግ የሚመጣውን መጠበቅ፡- ያለፈው ስህተት ላይ ብቻ ሳይሆን ደግነት ላይም መቆየት ዛሬን እንዳንራመድ ያደርገናል ከትላንት ይልቅ ነገ ለሰው ልጅ ቅርብ ናት
14-         በራስ መልካም ሥራዎችና አገልግሎቶች አለመታመን፡- ትምክሕት በገደል አፋፍ ላይ እንደ መጫወት ነው ትዕቢት በቦምብ ቀለበት እንደ መቀለድ ነው
15-         በየቀኑ ለሚገጥሙት ነገሮች ሳያቋር እግዚአብሔርን መለመን፡- የዚህን ዓለም ሸለቆ የሚወጡት ሰዎች አብዝተው አቤት ፣ አቤት የሚሉ ናቸው የዚህ ቅዱስ አባት ምክር ብዙ የእውነት ፈርጦችን ይዟል
በብዙ ክብር በልዕልና ያለኸው ፣ ደካሞችን በመርዳትህ የምትደሰተው ፣ የጽድቅ ራስ ፣ የሕይወትም ምሥጢር እግዚአብሔር ሆይ ፣ የማልረሳቸው ብዙ ነገሮች አሉኝ ዛሬ ግን አንተን በመርሳት ከመፈተን ጠብቀኝ የሰውነትና የዓለማዊነት ልብሴን ትቼ የመንፈሳዊ ቀሚሴን ለብሼ ለአገልግሎት መሰየም ይሁንልኝ አንድ ጊዜ ተናግረኸኝ ሠላሳ ፣ ስድሳ የማፈራ ልጅህ አድርገኝ በቅዱሱ ስምህ ለዘላለሙ አሜን
የበረሃ ጥላ 2
መስከረም 2 ቀን 2012 ዓ.ም.
ዲአመ
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ
አዳዲስ መጻሕፍትን ይግዙ

ተዛማጅ ጽሑፎች

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ