መግቢያ » ልዩ ልዩ ሁለት » የደስታ ቋጠሮ

የትምህርቱ ርዕስ | የደስታ ቋጠሮ

ኑሮህን በሌሎች ሞት ላይ አትመሥርት ። በሚታሰር አንደበትህ እውነት ተናገርበት ። ስለ ተጨነቅህ የሚቀር የለምና አትጨነቅ ፣ የቤት ሥራህን ግን ዛሬ ሥራ ። ተሳዳቢዎች አጥፍቶ ጠፊ ናቸውና አትደነቅ ። በቃየን ድንጋይ የጀመረው ጦርነት ወደ ኒውክለር አድጓልና ክፋትን በቶሎ ገስጸው ። ደቂቃዎች ቢቀሩህ የምታደርገው ምንድነው ? ሁልጊዜ ደቂቃዎች እንደ ቀሩህ ሆነህ ከኖርህ ሥራህን ትፈጽማለህ ። እንደ እማሆይ ትሬሳ “ኢየሱስ ሆይ እወድሃለሁ ፣ ኢየሱስ ሆይ እወድሃለሁ” እያልህ ለመሞት ተመኝ ። በእግዚአብሔር ሰዎችን ፣ በሰዎች እግዚአብሔርን እወቅ ። ነገ ያንተ አይደለምና ዛሬ ለፍቅር ተነሣ ።

በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ

ተዛማጅ ትምህርቶች

የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ