መግቢያ » ግጥም » ያኖራል መዓዛው

የትምህርቱ ርዕስ | ያኖራል መዓዛው

የሳሮን አበባ – ፅጌረዳም አይደል
የህብረ ቀለማት – የውበትም ፀዳል
የሚማርክ ነገር – ፍፁም የለበትም
መዓዛው ሌላ ነው – አይደል  የስሊክም
ሚሸተው ሌላ ነው – ሮማንም አይመስልም፡፡
ሽቱ አርከፍክፎ
ሱፍ ከረባት ለብሶ
ቁመቱ ቢያማልል
መልኩ ቢያነሆልል
ቃሉ ምን ቢማርክ
አንጡር ሀብት ቢኖረው
አዝማዱ ቢከበው
ይመስልሐል እንጂ …
ከኃጢአት ቤት ከቶ ምንም መልካም የለው
መዓዛው ጠረኑ ለነፍስ ርኩሰት ነው፡፡
አማናዊ ሳሮን አማናዊ ሮማን
ለቆሸሸ ኃጥዕ ለረከሰ አማኝ
ክርስቶስ ብቻ ነው ንፁህ ንዑድ ሽቶ
ከዕጣን ከስሊክ ከሁሉም በልጦ
ያኖራል መዓዛው በፍፁም ተመስጦ፡፡ 

በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ

ተዛማጅ ትምህርቶች

የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ