• ያልገባንን ነገር ለመናገር መቸኮላችን ፣
• ወቅታዊ እንጂ ዘላለማዊ ርእስ አለመፈለጋችን ፣
• ሞታችንን ረስተን መግደላችን ፣
• ስለማናውቀው ሰው ከሚያውቁት በላይ ክፉ ማውራታችን ፣
• እያመሰገንን ተዋውቀን እየተሳደብን መለያየታችን
• ደመወዝ እያለን ጉቦ መፈለጋችን ፣
• እኔ የወደድሁትን ብቻ ውደዱ ማለታችን ፣
• ሟችን ረስተን ለገዳይ ማዜማችን ፣
• ለሬሳ ዘር ማውጣታችን ፣
• መርጠን ማልቀሳችን ፣
• ነግ በእኔ ይደርሳል አለማለታችን ፣
• ክፋትን በክፋት ማረማችን ፣
• የማያልቅ ብቀላ ውስጥ መግባታችን ፣
• በአንድ ክፉ ሚሊየኖችን ክፉ ማለታችን ፣
• መኖር እየፈለግን ሌላውን እንዳይኖር ማድረጋችን ።
ይገርመኛል !!!
ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
ግንቦት 20 ቀን 2013 ዓ.ም.
ክፍል ሁለት
ይገርመኛል !!!
– ዝም ያለውን ሰው መቆስቆሳችን፣ ያልበደለንን መጉዳታችን፣
– የሥራ ደቦ ትተን የጠብ ደቦ መውደዳችን፣
– ሃይማኖትን በእምነት ሳይሆን በወኔ መያዛችን፣
– ስርቆትን እየተጸየፍን ነፍስ ማጥፋታችን፣
– በጽድቅ ሳይሆን በኃጢአት ዓይነት መጽናናታችን፣
– መብቱን ሰጥተነው ሳለ ከድሀ ምርቃት መጠበቃችን፣
– አገር እያፈረስን ቤት ለመሥራት መሯሯጣችን፣
– ጳጳስ እየሰደብን የእኔን ዲቁና አክብሩልኝ ማለታችን፣
– ጎሣችን እስኪመጣ ሃይማኖተኛ መምሰላችን፣
– ተገልብጠን ለመጣ ሁሉ ማዜማችን፣
– መንኩሰን ከሞትን በኋላ ጎሣ ያለን መሆናችን፣
– ዕድሜአችንን እየደበቅን ዕድሜ ስጠኝ ማለታችን፣
– መጸለይን ትተን የሰውን ኀዘኔታ መፈለጋችን፣
– ዕራቁት ተወልደን በካባ መኩራታችን፣
– ቆሻሻ ተሸክመን በሽቱ መመጻደቃችን፣
– እግዚአብሔርን እየጠራን ብቸኛ ነኝ ማለታችን።
ይገርመኛል !!!
ዲያቆን አሸናፊ መኮንን
ግንቦት 21 ቀን 2013 ዓ.ም.
የዲያቆን አሸናፊ መኰንንን ትምህርቶችና ስብከቶችን ለመከታተል
https://t.me/Nolawii
https://t.me/nolawisebketoch
https://www.facebook.com/ashenafi.mekonnen.357

http://ashenafimekonen.blogspot.com/