“ጌታ ሁላችንም የተሳደበውና ያመነው ወንበዴ ነን ፣ ጌታ ሆይ አምናለሁ አለማመኔን እርዳው ፤
ጌታ ሆይ ከሞት ቊጥጥር ሥር ነኝ ፣ አንዳች ማድረግ የምችለው የለም ፣
ነገር ግን፡- “ጌታ ሆይ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ” እያልሁ እጮኻለሁ ።
ኢየሱስ ሆይ ፣ አሰቃቂ በሆነው ዓለም ውስጥ አንዳች አላውቅም አንዳችም አልረዳም። ነገር ግን አንተ እጅህን ፣ ልብህን ከፍተህ ወደ እኔ መጣህ ያንተ መኖር ብቻውን መንግሥተ ሰማያቴ ነው ።
ኦ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ !
በሰዎች ፍርድ የተጣለው ወንጀለኛው ወዳጅህ ለሆነው ለአንተ ክብርና ምስጋና ይሁን ።
“ጌታ ሆይ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ” እያሉ የሚጮኹትን ነጻ እያወጣህ ወደ ሲኦል ወርደሃል ።
/የራሻው ፓትርያርክ በርተሎሜዎስ/