የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ

የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

ጥቂትዕረፉ/ማር 6፡31/

ወንጌል ማለት የምሥራች፣የድኅነት ዜና ማለትነው፡፡ ወንጌል ስለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስአዳኝነት የሚናገር የነጻነትአዋጅ ነው፡፡ ወንጌልጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስበሞቱ የኃጢአትን ዋጋእንደ ከፈለ፣ በትንሣኤውጽድቃችንን እንዳረጋገጠ፣ ገነትእንደተከፈተች፣ ሕይወት እንደተመለሰ፣ ክርስቶስ በድልነሺ ዙፋኑ እንደተቀመጠ፣ ዳግመኛ ያመነውንሊያሳየን እንደሚመጣ የምትናገርሰማያዊ ዜና ናት፡፡ወንጌል ራሱ ክርስቶስነው፡፡ ስለ ሌሎችሃይማኖታዊ ነገሮች ብንናገርአስተማርን ይባላል፡፡ ወንጌልሰበክን የሚባለው ግንስለ ክርስቶስ አዳኝነትስንናገር ብቻ ነው፡፡ስለ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባበሚናገረው ክፍል ፊልጶስ፡ ስለ ኢየሱስ ወንጌልን ሰበከለት ይላል (የሐዋ. 8÷35)፡፡ወንጌል ስለ ኢየሱስየሚናገር ነው፡፡ 
ሐዋርያው ጳውሎስም፡ “… ይህምወንጌልበሥጋከዳዊትዘርስለተወለደእንደቅድስናመንፈስግንከሙታንመነሣትየተነሣበኃይልየእግዚአብሔርልጅሆኖስለተገለጠስለልጁነው፣እርሱምጌታችንኢየሱስክርስቶስነው ብሏል (ሮሜ1÷1-4)፡፡ወንጌል የሚል ስያሜየተሰጣቸውም አራቱ የአዲስኪዳን መጻሕፍት ናቸው፡፡ለምን? ወንጌል ተባሉስንል ስለ ክርስቶስከልደቱ እስከ ዕርገቱበሙሉነትና በሌጣነት ስለሚዘግቡነው፡፡ ወንጌል የክርስቶስዜና፣ የመስቀሉ ነገር፣የአዳኝነቱ ምሥጢር፣ የዘላለምሕይወት አጀንዳ፣ ብቸኛየመዳን መፍትሔ፣ የዘላለምጉዳይ፣ ዘመን የማይሽረውጥበብ፣ የማይጨረስ ሀብት፣የማይጎድል ፍቅር ነው፡፡
ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የስብከት ዘዴበተባለውና 1980 . ባሳተሙት መጽሐፍውስጥ እንዲህ ብለዋል፡
 
ምንም የስብከት ምንጩቅዱስ መጽሐፍ ቢሆንምጥቅሱም ከእርሱው ቢወጣምሐተታውና አገላለጡ ስለአዳኙ ኢየሱስ ክርስቶስመሆን አለበት፡፡ ኢየሱስንማዕከል ያላደረገ የእርሱንምአዳኝነት የማይገልጥ ስብከት፣ስብከት ሊሆን አይችልም፡፡ለምሳሌ የጥበብ መጀመሪያውእግዚአብሔርን መፍራት ነውብሎ ስለ ጥበብ፣ስለ ፈሪሃ እግዚአብሔርቢናገርም ስለ ክርስቶስየአዳኝነት ሥራ አልመሰከረምማለት ነው፡፡ እንዲሁምስለ ዐሠርቱቃላት ቢናገር፣ ይህምከቅዱስ መጽሐፉ ቢጠቀስምየኢየሱስ ክርስቶስን የሕይወትታሪክና የአዳኝነቱንም ሥራአልተመለከተም ማለት ነው፡፡ቅዱስ ጳውሎስእኛግን በክርስቶስ እናስተምራለንበተሰቀለውሲል በክርስቶስስም መስበክ መናገርምተገቢ መሆኑን ገልጦተናግሯል (1ቆሮ. 1÷23)፡፡
የኢየሱስን ስምየአዳኝነቱንም ሥራ አይናገሩምእንጂ በጠቅላላው ስለእግዚአብሔር በአይሁድ ምኩራብበእስላሞችም መስጊድ ሊነገርይችላል፡፡ ሲነገርም ይሰማል፡፡እኛ ክርስቲያኖች ግንመሪያችን መድኃኒታችን ኢየሱስክርስቶስ ስለሆነ የእርሱንየሕይወት ታሪክ የማዳኑንምተግባር መመስከር፣ መስበክ፣መናገርም አለብን፡፡ማንኛውምእውነት ነቢያት የተናገሩትትንቢት፣ የሰው ልጅድኅነት በኢየሱስ ክርስቶስመፈጸሙን የሁሉም መፈጸሚያእርሱ መሆኑን በመግለጥየሚሰበከው እውነተኛው ክርስቲያናዊስብከት ነው፡፡ ሰባኪውምእውነተኛ ሰባኪ ነው። /የስብከት ዘዴ በብፁዕአቡነ መልከ ጼዴቅ1980/
ወንጌል የሚሰበከው በምድራውያንሹማምንት ፈቃድ ሳይሆንየሰማይና የምድር ጌታበሆነው በኢየሱስ ክርስቶስሥልጣን ነው፡፡ ወንጌልለመስበክ የምናሳየው የፈቃድወረቀት፡ ሥልጣን ሁሉበሰማይናበምድርተሰጠኝ፡፡እንግዲህሂዱናአሕዛብንሁሉበአብበወልድናበመንፈስቅዱስስምእያጠመቃችኋቸው÷ ያዘዝኋችሁንም ሁሉእንዲጠብቁእያስተማራችኋቸው ደቀመዛሙርትአድርጓቸው፤እነሆም÷ እኔእስከዓለምፍጻሜድረስሁልጊዜከእናንተጋርነኝ (ማቴ. 28÷19-20) የሚለው አምላካዊቃል ነው፡፡

ጌታችን ወደ ሰማይከማረጉና ታላቁን ተልእኮከመስጠቱ በፊት ደቀመዛሙርቱን እየላከ ያለማምዳቸውነበር፡፡ ሐዋርያትም ወደ ኢየሱስ ተሰብስበው ያደረጉትንና ያስተማሩትን ሁሉነገሩት (ማር. 6÷30)፡፡ ሪፖርቱንለክርስቶስ ሲያቀርቡ ብዙጊዜ ይሰጣቸው የነበረውመልስ አስደናቂ ነው፡፡በአንድ ወቅት ርኩሳንመናፍስት ስለተገዙላቸው እጅግደስ ብሏቸው ወደጌታ ሲመጡ፡ ነገርግንመናፍስትስለተገዙላችሁበዚህደስአይበላችሁ÷ ስማችሁግንበሰማያትስለተጻፈደስይበላችሁ ብሏቸዋል (ሉቃ. 10÷20)፡፡የወደቀውን ጠላት ስለረገጣችሁሳይሆን በእኔ ቤዛነትስለዳናችሁ በእግዚአብሔር አባታችሁፊት ዕውቅና ስላገኛችሁደስ ይበላችሁ ብሏቸዋል፡፡ከጸጋ ስጦታዎች ይልቅደስ የሚያሰኘው መዳናችንነውና፡፡
በሌላ ጊዜም ደቀመዛሙርቱ ስለነበራቸው የወንጌልጉዞ ሪፖርት ሲያቀርቡለትእንዲህ ብሏቸዋል፡ እናንተራሳችሁብቻችሁንወደምድረበዳኑናጥቂትዕረፉአላቸው፤የሚመጡናየሚሄዱብዙዎችነበሩና÷ ለመብላትእንኳጊዜአጡ (ማር. 6÷31)፡፡
ጌታችን በገጣባ አህያየሚጭን ሳይሆን አህያዋንቀድሞ የሚያክም ነው፡፡እንዲሁም አገልጋዮን ከነሕመምህ አገልግለኝ የሚልሳይሆን ፈውሶ የሚልክመልካም ጌታ ነው፡፡እንደ ሻማ እያለቅንእንድናበራ አይፈልግም፣ እንደመቅረዝ ዘይቱን እየሞላንእንድናበራ ይፈልጋል፡፡ ሕፃኑየጡት ወተት የሚያገኘውእናቲቱ በትክክል ስትመገብነው፡፡ እናቲቱ ካልበላችልጁ ወተት አያገኝም፡፡ጌታ ለልጁ የሚያስበውእናቲቱን በመመገብ ነው፡፡ሞልቶን እንድንፈስ እንጂእንጥፍጣፊ እንድንሰጥ አይፈልግም፡፡እኛ ለምናገለግላቸው ብቻእያሰብን የራሳችንን መንፈሳዊምግብ እናጓድላለን፡፡ እግዚአብሔርግን ለእኛም ያስባል፡፡እየወደቁ ማንሣት የለም፣ስንቆም ብቻ የወደቁትንማንሣት እንችላለን፡፡ ይህደግነት ወይም መሥዋዕትነትአይደለም፡፡ ክርስትና ኖሮየማኖር ሥርዓት ነው፡፡መሥዋዕት የምናደርገው ምድራዊውንጥቅም እንጂ ሰማያዊውንምግብ አይደለም፡፡ ሐዋርያውጳውሎስ፡ ስለዚህ እኔያለአሳብእንደሚሮጥሁሉ< /i>እንዲሁአልሮጥም÷ ነፋስንእንደሚጎስምሁሉእንዲሁአልጋደልም።ነገርግንለሌሎችከሰበክሁበኋላራሴየተጣልሁእንዳልሆንሥጋዬንእየጐሰምሁአስገዛዋለሁ ብሏል (1ቆሮ. 9÷26-27)፡፡
የጡት ወተትና የጡጦወተት ልዩነት አለው፡፡የጡት ወተት እናቲቱለራሷ ከወሰደችው ምግብለልጁ የሚተርፈው ሲሆንየጡጦ ወተት ግንለልጁ ብቻ ተብሎየሚዘጋጅ ነው፡፡ ለልጁግን ጠቃሚነት ያለውከጡጦው ይልቅ የጡትወተት ነው፡፡ ዛሬያለው አገልግሎት የጡጦአገልግሎት ነው፡፡ ለሕዝቡተብሎ ብቻ የሚዘጋጅ፣የስብከት ሰዓት ሲደርስአገላብጦ የሚወጣበት፣ ወይምተበድሮ የሚሰበክበት ነው፡፡ስለዚህ የሚወለዱት ልጆችአቅም የለሽ፣ በፈተናየማይፀኑ ሆነዋል፡፡ ለራሳችንከበላነው፣ ካረፍንበት፣ በጸሎትሆነን ካጣጣምነው ቃልብንናገር ኖሮ ብዙዎችለነጻነት በተወለዱ ነበር፡፡ስለዚህ የምንወልዳቸው የአጋርልጆች እየሆኑ መንፈሳዊነጻነታቸውን የተገፈፉ ለኃጢአትየተማረኩ ይሆናሉ፡፡ ነጻሳይወጡ መውለድ ትውልድንለባርነት መፈልፈል ነው፡፡
ከትንሹ እስከ ትልቁያሉት አገልጋዮች የሚያስቡትለሕዝቡ ነው፡፡ ለአገልጋይየሚያስብ አገልጋይ ጠፍቷል፡፡የእረኞች አለቃ ኢየሱስግን ለአገልጋዮች መንፈሳዊደኅንነት ያስባል፡፡ ስለአገልግሎታችን ብዙ ሪፖርትስናቀርብለት፡– “እናንተ ራሳችሁብቻችሁን ወደ ምድረበዳ ኑና ጥቂትዕረፉይለናል (ማር. 6÷30)፡፡
ዐሥር ሺህ ሜትርበሩጫ ይዘለቃል፣ አንድሺህ ኪሎ ሜትርግን በሩጫ አይዘለቅም፡፡አገልግሎት ሰፊ ሩጫነው፡፡ በዛሬው ግለታችንብቻ አሸንፈን የጠላትንመንደር አፈራርሰን በጨለማየተያዙትን ነጻ አውጥተንየምናድርበት አይደለም፡፡ እያዳመጥንየምንናገርበት፣ እያረፍን የምንጓዝበትነው፡፡ አገልጋዮች በቃሉ ብቻ ሳይሆን በሥጋም ማረፍ አለባቸው፡፡ የፀጥታ ጊዜ፣ ከራሳቸው ጋር የሚሆኑበት ሰዓት፣ ነጻነት የተላበሰ ተፈጥሮ ውስጥ ማረፍ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ይህ ቅንጦት አይደለም፡፡ ሕዝባችን ለአገልጋዮች ብዙ መብልና የሚያሰክር መጠጥ ከሚያቀርብላቸው ዕረፍትን ቢያዘጋጅላቸው ተገቢ ነበር፡፡ የሱነም ሴት ያደረገችው ይህንን ነው፡፡ ለኤልሳዕ ማረፊያ ቤት፣ ማንበቢያ ጠረጴዛ፣አዘጋጀችለት (2ነገሥ. 4÷8-10)፡፡ አራስ ልጅ እንዲህ ይላል ይላሉ፡– “እናቴ ረሀቤን ስታውቅልኝ ጥማቴን አታውቅልኝምእናቲቱ ብዙ ጊዜ ሕጻኑ ምግብ እንጂ ውሃ እንደሚያስፈልገው አታውቅም፡፡ ታዲያ በዱዳ አንደበቱ፡– “እናቴ ረሀቤን ስታውቅልኝ ጥማቴን አታውቅልኝምይላል ይላሉ። መልእክቱ ለአራሱ ልጅ ውሃም ያስፈልገዋል ማለት ነው። አገልጋዮችም ዛሬ ተናገሩ ቢባሉ ከአራሱ ሕፃን ይልቅ፡– “ወገኔ ረሀቤንም ጥማቴንም አላወቀልኝምሳይሉ አይቀሩም፡፡ የአገልጋይአድናቂ ነኝ ማለት ቋንቋውም መንፈሳዊ አይደለም፡፡ ከማድነቅ መደገፍን መለማመድ ያስፈልጋል፡፡ ብዙ አገልጋዮች እየራባቸው እንደሚያድሩ አውቃለሁ፡፡ ሕዝባችንም በአብዛኛው ሐሰተኞቹን መምህራን ሲቀልብ ለእውነተኞቹ ግን ቁጥብ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡
ሩኅሩኁ ጌታ፣ ያስቀመጠውን የማይረሳ አምላክ ለደቀ መዛሙርቱ፡እናንተራሳችሁብቻችሁንወደምድረበዳኑናጥቂትዕረፉ አላቸው (ማር. 6÷30)፡፡ ጌታችን እየተናገረ ያለው የአገልጋዮች ጊዜ እንዲኖር፣ አገልጋዮች በኅብረት ሆነው እንዲያርፉ እየመከረ ነው፡፡ ብዙ አገልጋዮች አገልጋዮችን አያቀርቡም፡፡ አገልግሎታችን ሰማያዊ ጥሪያችን ከሆነ መዋደድ ግድ ነው፡፡ ገበያ ከሆነ ብንራራቅም አይደንቅም፡፡ ባለንበት ዘመን የነጋዴዎች ማኅበር፣ የፖለቲከኞች ማኅበር፣ …. እየተባለ ሁሉም ሲገናኝ የአገልጋዮች ጉባዔ ግን አለመኖሩ ያሳዝናል፡፡ ወንጌሉን ከሚሰብኩት አገልጋዮች ይልቅ ወንጌሉን የሚቃወሙት ሰዎች የተሻለ ድርጅታዊ ኅብረት አላቸው፡፡ ምንም እንኳ የአጋንንት ማኅበርተኞች ባያስቀኑም እኛ ግን ልናውቅበት ይገባል፡፡ ጌታችን፡ የዚህ ዓለም ልጆች ለትውልዳቸው ከብርሃንልጆችይልቅልባሞችናቸውና ያለውን መመከሪያችን ልናደርገው ይገባል (ሉቃ. 16÷8)፡፡
ብቻችሁን የሚለው ቃል ማራኪ ነው፡፡ አገልጋዮች ምእመናን ጣኦት ይሆኑባቸዋል፡፡ የሚኖሩት በእግዚአብሔር እጅ ሳይሆን በምእመናን ይመስላቸዋል፡፡ ምእመናኑ ቢሰጡ ቸርነት አይደለም፡፡ መንፈሳዊ ግዴታቸው ነው፡፡ የማያልቀውን ሀብት አገልጋዩ እየሰጠ የሚጠፋውን ገንዘብ ከምእመናኑ በመቀበሉ ሊሳቀቅ አይገባውም፡፡ ምእመናን በአገልጋዮች ጉባዔ ሊገኙ አይገባም፡፡ በውጭ ነገሮችን ሊያስተካክሉ ይችላሉ፡፡ አገልጋዮች ግን የራሳቸው የጽሞና ጊዜ ያስፈልጋቸዋል፡፡ መንግሥት፣ መንግሥት የሚሆነው የራሱ ምሥጢር ካለው ብቻ ነው፡፡ እንዲሁም የመንግሥቱ ሠራተኞች የሆነ አገልጋዮች የራሳቸው ምሥጢር ያስፈልጋቸዋል፡፡ በእውነት አገልጋዮች ከቸር ምእመናን ይልቅ አገልጋዩ ድካማቸውን እንደሚያውቅላቸው ሊረዱ ይገባል፡፡ ባልና ሚስት የቤቱን ምሥጢር ለልጆቹ በሙሉ አይነግሩም፡፡ ምክንያቱም ልጆቹ የመሸከም አቅማቸው አይፈቅድምና ነው፡፡ እንዲሁም ከአገልጋይ ጋር ሊነገር የሚገባው ምክክር ወደ ምእመናን መምጣት የለበትም፡፡በጫጩት ፊት ፈንግል አይወራምይባላል፡፡ ለጫጩት አቅም እንኳን በሽታው መጥቶ ድምፁም ይገድላታል።
ወደ ምድረ በዳ ኑና ጥቂት ዕረፉ
 
ምድረ በዳ እግዚአብሔር ልጆቹን የሚያሰለጥንበት ስፍራ ነው፡፡ በነቢዩ በሆሴዕ ከተነገረው ተስፋ፡ ስለዚህእነሆ÷ አባብላታለሁ÷ ወደምድረበዳምአመጣታለሁ÷ ለልብዋምእናገራለሁ የሚል ነው (ሆሴ. 2÷16)፡፡ ምድረ በዳ እግዚአብሔር ለልብ የሚናገርበት ስፍራ ነው፡፡ በከተማ በጆሮአችን ብዙ ድምፆችን እንሰማለን፡፡ በምድረ በዳ ግን የእግዚአብሔርን ድምፅ በልባችን እንሰማለን፡፡ እግዚአብሔር ለልብ የሚናገር አምላክ ነው፡፡ ወሬኞች ለጆሮአችን፣ ጠቢባን ለአእምሮአችን፣ እግዚአብሔር ግን ለልባችን ይናገራል፡፡ ታዲያ እግዚአብሔር ተናግሮ እንዲያሳርፈን ወደ ምድረ በዳ መምጣት ያስፈልጋል፡፡ ምድረ በዳ ለዓይን የሚታይ ነገር የሌለበት ማለት ነው፡፡ እንዲሁም ከቊሳዊ ዓለምና ዕይታ ወጥተን በገለልተኛ ስፍራ የጌታን ድምፅ መጠባበቅ ያስፈልገናል፡፡ ጥቂት ዕረፉ ነው ያለው፡፡ ጥቂት ማረፍ ለሁለት ሦስት ቀናት በፀጥታ መሆን ለወሩ የሚበቃ ኃይል የምንሞለበት ነው፡፡ ሂሳብ ሳንሞላ የሞባይል ስልካችንን ብንደውል የምንፈልገው አያገናኘንም፡፡ በባዶ የምንገናኘው ከዋናው ቴሌ መሥሪያ ቤት ጋር ነው፡፡ እንዲሁም መለኮታዊውን ኃይል ሳንሞላ ወገናችንን ማግኘትና ማሳረፍ አንችልም፡፡ በባዶ የምንገናኘው ከዋናው ቤታችን ከክርስቶስ ጋር ብቻ ነው፡፡
የሚመጡናየሚሄዱብዙዎችነበሩና÷ ለመብላትእንኳጊዜአጡ(ማር. 6÷31)፡፡ዛሬ ቀልብ አጥተን የምንባዝንለት ተተክሎ የሚቀር ብቻ አይደለም፡፡ አንዱ ይመጣል፣ ሌላው ይሄዳል፡፡ ሽርሽሩ ብዙ ነው፡፡ ስለዚህ ሁሉም ለመዳን አይመጣምና ጸሎትን ስለረሳንበት፣ ጽሞናን ስለተውንበት ጊዜ ንስሐ እንግባ፡፡ አስተውለን ልናርፍ ካልቻልን እግዚአብሔር የማንፈለግበትን ጊዜ አምጥቶ በግድ ያሳርፈናል፡፡ ደግሞ በነጻ እንደ መማር ቀላል አይሆንም፡፡
አገልጋይ የሚባሉት በመድረክ የሚያገለግሉ ብቻ አይደሉም፡፡ እናት በቤት ውስጥ፣ ሠራተኛ በሥራ ስፍራ አገልጋይ ነው፡፡ የኑሮን ግዴታ ለመሙላት ብዙ መባዘን ያለባቸው እንደ ማርታ ላይ ታች፣ ሽቅብ ቁልቁል የሚሉ ወገኖችም እንደ ማርያም ከጌታ እግር ሥር ቁጭ ብለው ዕረፍትን ሊጠጡ ይገባል/ሉቃ. 1042/፡፡ እንቅልፍ አጥተው ቢሮጡም ዓለም ጐዶሎ ነው፡፡ ከጌታ ጋር ስንሮጥ ግን ትንሹ ብዙ ነው፡፡ ለእግዚአብሔር ጊዜ ያጡ፣ በሩጫቸው ብቻ የሚኖሩ የመሰላቸውን እግዚአብሔር በአልጋ አስተኝቶ፣ በወኅኒ ጥሎ አግኝቷቸዋል። እግዚአብሔር ከወከባ ወጣ የምንልበት የጽሞና ሰዓት እንዲኖረን ይፈልጋል። ዕድሜ ልክ መባዘን ምንድነው?
                                     ጥቂት ዕረፉ
                                                   /ማር 631/
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ
አዳዲስ መጻሕፍትን ይግዙ

ተዛማጅ ጽሑፎች

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ