የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

አልበለጥነውም ወይ?

                                                                 ሐሙስ፣ ጥቅምት 2 2004
 

የአመፃ ጌታ ክፋት የሚያቆነጅ
ንፉግን አፍቃሪ ደግነት አሳዳጅ
ቢሆንም ቢሆንም ጠላቷ የሠላም
ለአንድ ጊዜ እንጂ
        ጌታ ክርስቶስን ዳግም አልፈተነም፡፡
የሰው ልጆች ግን፦
በእድሜ ዘመኑ ዱካውን አሽትተው
በዋለበት ውለው ባደረበት አድረው
ረበናት መሪዎች ሊቅ መባላቸውን
ለአምልኮ ተመርጠው መለየታቸውን
ዘንግተውት ሁሉን በልጠው ዲያቢሎስን
ብዙ ፈትነውት ባያርፍ ልባቸው
እስኪ ውረድ አሉት
               በመስቀል ቸንክረው፡፡
ታድያ ክርስቶስ ሆይ!
እኛ ዲያቢሎስን አልበለጥነውም ወይ?!
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ
አዳዲስ መጻሕፍትን ይግዙ

ተዛማጅ ጽሑፎች

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ