መግቢያ » ልዩ ልዩ አንድ » ይገርመኛል !!!

የትምህርቱ ርዕስ | ይገርመኛል !!!

•  ያልገባንን ነገር ለመናገር መቸኮላችን ፣

•  ወቅታዊ እንጂ ዘላለማዊ ርእስ አለመፈለጋችን ፣ 

•  ሞታችንን ረስተን መግደላችን ፣

•  ስለማናውቀው ሰው ከሚያውቁት በላይ ክፉ ማውራታችን ፣ 

•  እያመሰገንን ተዋውቀን እየተሳደብን መለያየታችን 

•  ደመወዝ እያለን ጉቦ መፈለጋችን ፣

•  እኔ የወደድሁትን ብቻ ውደዱ ማለታችን ፣ 

•  ሟችን ረስተን ለገዳይ ማዜማችን ፣

•  ለሬሳ ዘር ማውጣታችን ፣

•  መርጠን ማልቀሳችን ፣

•  ነግ በእኔ ይደርሳል አለማለታችን ፣ 

•  ክፋትን በክፋት ማረማችን ፣

•  የማያልቅ ብቀላ ውስጥ መግባታችን ፣

•  በአንድ ክፉ ሚሊየኖችን ክፉ ማለታችን ፣

•  መኖር እየፈለግን ሌላውን እንዳይኖር ማድረጋችን ።

ይገርመኛል !!!

ዲያቆን አሸናፊ መኰንን

ግንቦት 20 ቀን 2013 ዓ.ም.

ክፍል ሁለት

ይገርመኛል !!!

– ዝም ያለውን ሰው መቆስቆሳችን፣ ያልበደለንን መጉዳታችን፣

– የሥራ ደቦ ትተን የጠብ ደቦ መውደዳችን፣

– ሃይማኖትን በእምነት ሳይሆን በወኔ መያዛችን፣

– ስርቆትን እየተጸየፍን ነፍስ ማጥፋታችን፣

– በጽድቅ ሳይሆን በኃጢአት ዓይነት መጽናናታችን፣

– መብቱን ሰጥተነው ሳለ ከድሀ ምርቃት መጠበቃችን፣

– አገር እያፈረስን ቤት ለመሥራት መሯሯጣችን፣

– ጳጳስ እየሰደብን የእኔን ዲቁና አክብሩልኝ ማለታችን፣

– ጎሣችን እስኪመጣ ሃይማኖተኛ መምሰላችን፣

– ተገልብጠን ለመጣ ሁሉ ማዜማችን፣

– መንኩሰን ከሞትን በኋላ ጎሣ ያለን መሆናችን፣

– ዕድሜአችንን እየደበቅን ዕድሜ ስጠኝ ማለታችን፣

– መጸለይን ትተን የሰውን ኀዘኔታ መፈለጋችን፣

– ዕራቁት ተወልደን በካባ መኩራታችን፣

– ቆሻሻ ተሸክመን በሽቱ መመጻደቃችን፣

– እግዚአብሔርን እየጠራን ብቸኛ ነኝ ማለታችን።

ይገርመኛል !!!

ዲያቆን አሸናፊ መኮንን

ግንቦት 21 ቀን 2013 ዓ.ም.

የዲያቆን አሸናፊ መኰንንን ትምህርቶችና ስብከቶችን ለመከታተል

https://t.me/Nolawii

https://t.me/nolawisebketoch

https://www.facebook.com/ashenafi.mekonnen.357

YouTube player

http://ashenafimekonen.blogspot.com/

በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ

ተዛማጅ ትምህርቶች

የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ

አዳዲስ መጻሕፍት

ትርጉሙ:- ቀይ ዕንቈ

ለምድራችንና ለአገልግሎታችን በረከት የሆነ መጽሐፍ
የመጀመሪያ እትም ጥቅምት 2016 ዓ.ም

1ኛ ጢሞቴዎስ ትርጓሜ – ክፍል አንድ

የመጀመሪያ እትም ሐምሌ 2013 ዓ.ም

ምክር አዘል መጽሐፍ

የመጀመሪያ እትም