መግቢያ » ልዩ ልዩ ሁለት » ሆድና ጀርባ

የትምህርቱ ርዕስ | ሆድና ጀርባ

ሆድና ጀርባ ከልደት እስከ ሞት ድረስ አይለያዩም ፣ ግን አይግባቡም። ሕመማቸው የጋራ ቢሆንም አንድ ቀን ተያይተው አያውቁም። ሆድ ብዙ ቢችል ፣ ጀርባም ብዙ ቢሸከም አንዳቸው አንዳቸውን አወድሰው አያውቁም። ጀርባ የሆድን መክሳትና መወፈር አይቶ አያውቅም፣ ሆድም የጀርባን መቁሰልና መፍካት አይቶ አያውቅም። ከእነርሱ ይልቅ የሚቀራረብ የለም፣ ከልደት እስከ ሞትም ከእነርሱ ይልቅ አብሮ የሚኖር የለም። ግን ሆድና ጀርባ ሳይተያዩ፣ ሳይግባቡ ይኖራሉ። ጭንቅላት መሪ ነው፣ ሆድ ከሚበላው ብዙውን ይወስዳል፣ ራስ ወዳድ ነው፣ ቶሎ ይሞታል። ላይ ሆኖ ከሆድ ቢጠቀምም ከጎረቤትሽ ከጀርባ ጋር ታረቂ ብሎ አያውቅም። ከጀርባ ብዙ መልእክት ቢቀበል፣ ማዕከላዊ ዕዝ ሆኖለት ቢኖርም ከሆድ ጋር እንዲስማማ ነገሮት አያውቅም። አንተም አብላኝ ፣ አንተም አስተንትንልኝ እያለ ይኖራል። ከልጆች ፍጭት የትልልቆች ዝምታ ይገርማል። የአቤልና የቃየልን ጠብ እንደ ዶሮ ጠብ የሚያይ ወላጅ የለም።

የአንድ አገር ልጆች፣ የአንድ መጽሐፍ ተማሪዎች፣ የአንድ እናት ልጆች ፣ የአንድ ዘመን ታሪክ ተጋሪዎች፣ የአንድ ወቅት በረከትና መርገም ተካፋዮች ለምን ሆድና ጀርባ ሆኑ?

በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ

ተዛማጅ ትምህርቶች

የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ