መግቢያ » ልዩ ልዩ ሁለት » መድኃኔ ዓለም !

የትምህርቱ ርዕስ | መድኃኔ ዓለም !

አንተ የነፍስ መልሕቅ ማዕበሉን አሳለፍከው !

አንተ ጽኑ መርከብ ከወደቡ አደረስከን !

አንተ ትጉህ እረኛ ከአውሬ ተናጠቅኸን !

አንተ የእውነት ፀሐይ ነጻ አወጣኸን !

አንተ የደናግል መመኪያ መጠሪያ ስም ሆንከን!

አንተ የካህን ካባ በአደባባይ አከበርከን !

አንተ የነፍስ ማረፊያ ልባችንን ደገፍክልን !

አንተ የቤታችን ራስ ጉድለትን ሞላህልን !

አንተ ሠራተኛ ተራራውን ደለደልክልን !

አንተ የድሀ አባት ሸለቆውን ሞላህልን !

አንተ የፍቅር ሀገር ሰው አዘጋጀህልን !

አንተ ብርሃን ሰባክያንን ላክልን!

አንተ ታሪክ አዳሽ እንደገና ፈጠርከን!

አንተ ታዳጊ ከምኞታችን አዳንከን!

አንተ ጥሩ ምንጭ ከመዛል አተረፍከን !

አንተ ነጭ ልብስ ከመራቆት አዳንከን !

አንተ የትኩዝ መጽናኛ በቃልህ ጠገንከን !

መድኃኔ ዓለም ሆይ!

አንተን የሚጠላ ያልታደለ ፣ ምስጋናህን የሚቃወም ቤቱ ወደ ሞት ያዘነበለ፤ ደምህን የሚያቃልል ዘላለሙን የበደለ ነው!

መድኃኔ ዓለም የሕይወት ሽታ ከዓይነ ሞት ሰወርከን !

ይህንንም ዘመን ሸፍነህ አሻግረን !

ተመስገን!

 

ሰኞ ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም.

በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ

ተዛማጅ ትምህርቶች

የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ