የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ

የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

ክቡርና ሕይወት ሰጪ ስለሆነው መስቀል/3

ቅዱስ ጎርጎርዮስ ፓላማስ እንደ ሰበከው
የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ እሑድ ሚያዝያ 25/2012 ዓ.ም.
ቃሉና ምጢሩ ከራሱ ከምልቱ አስቀድመው ስለመጡ እነርሱን አስቀድመን ልናብራራላችሁና ልንተረጉምላችሁ ይገባል ። ቅዱስ ጳውሎስ ከእኛ አስቀድሞ ተርጉሞአቸዋል ። በመስቀሉ የሚመካው ጳውሎስ ጌታ ኢየሱስ እርሱም እንደ ተሰቀለ ከዚህ ውጪ ሌላ እንዳያውቅ ቆረጠ (ከ1ኛ ቆሮ 2፥2 ጋራ ያነጻጽሩ)። ምንድር ነው ያለው ? መስቀል ማለት ሥጋን ፣ ከክፉ ምኞቱና መሻቱ ጋር መስቀል ነው (ከገላ 5፥24 ጋራ ያነጻጽሩ)። ስለ አካላዊ ደስታ ስሜቶችና ስለ ሆዳምነት ብቻ እየተናገረ ይመስላችኋልን ? እንደዚያ ቢሆንስ ለቆሮንቶሳውያን እንደዚህ ብሎ ባጻፈ ነበር ቅናትና ክርክር ስለሚገኝባችሁ ሥጋውያን መሆናችሁ አይደላችሁምን? (1ኛ ቆሮ 3፥3)። ስለዚህ ገንዘብ አልያም ክብርና ዝና የሚወ አልያም አሸናፊ ለመሆን የራሱን ፈቃድ (ሌሎች ላይ) የሚጭን ማንኛውም ሰው እንዲህ ያሉ ነገሮች የመከፋፈል ምንጭ ናቸውና ሥጋዊ ነው ኑሮውም እንደ ሰው ነው።[1]የጌታ ወንድም ያዕቆብ እንዳለው “በእናንተ ዘንድ ጦርና ጠብ ከወዴት ይመጣሉ? በብልቶቻችሁ ውስጥ ከሚዋጉ ከእነዚህ ከምቾቶቻችሁ አይደሉምን? ትመኛላችሁ ለእናንተም አይሆንም፤ ትገድላላችሁ በብርቱም ትፈልጋላችሁ፥ ልታገኙም አትችሉም፤ ትጣላላችሁ ትዋጉማላችሁ ነገር ግን አትለምኑምና ለእናንተ አይሆንም” (ያዕ 4፥12)። ሥጋን ከምኞቱና ከመሻቱ ጋር መስቀል ማለት እግዚአብሔርን ደስ የማያሰኙ ነገሮችን ሁሉ መተው ማለት ነው። ግዙፉ ሰውነታችን/ሥጋችን ቢያውከንና ተጽእኖ ቢያሳድርብንም በፍጥነት ወደ መስቀሉ ከፍታ ከፍ እናደርገው ዘንድ ይገባል። ምንድር ለማለት እየሞከርኩ ነው? ጌታ በምድር ላይ በነበረ ጊዜ የድህነት ኑሮ ነበር የኖረው። ድህነትን መኖር ብቻ ሳይሆን እንዲህ በማለትም ሰበከው እንግዲህ እንደዚሁ ማንም ከእናንተ ያለውን ሁሉ የማይተው ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም(ሉቃ 14፥33)።

ወንድሞቼና እህቶቼ ማናችሁም ብትሆኑ ንጽ በሆነ መንገድ መልካም፣ ተገቢና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ስናውጅ ስትሰሙን አትቆጡ አትበሳጩም። አልያም እነዚህ ነገሮች ፍጹም ሊደረሱ የማይችሉ በመሆናቸው አትታወኩ። በመጀመሪያ መንግተ ሰማያት የምትገፋ እንደሆነችና ግፈኞችም እንደሚናጠቋት ልብ በሉ (ማቴ 11፥12)። እንዲህ የሚለውን የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት አለቃ የሆነውን ጴጥሮስን ስሙት ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና(1ኛ ጴጥ 2፥21)። ከዚህም በመቀጠለ አንድ ሰው ምን ያል የጌታው ባለ ዳ እንደሆነ ሲያውቅና ሙሉውን መክፈል እንደማይቻለው ሲረዳ ትት በመሆን የሚችለውን ሁሉ ይሰጣል ይህንንም ነጻ ሆኖ በመምረጥ ያደርገዋል። ስለ ቀረው ዳ ራሱን በጌታ ፊት ትት ያደርጋል በትትናውም ምረቱንና ርውን በመቀበል የጎደለውን ይሞላል። አንድ ሰው ልቡናውና አእምሮው ወደ ብትና ንብረት እንደሚባዝን ከተረዳ ይህ ሥጋዊ ሳብ በውስጡ ከተሰቀለው ክርስቶስ እንደለየው ማወቅና መረዳት አለበት።
ይህንን ሳባችሁን ወደ መስቀሉ ከፍታ ከፍ ለማድረግ እንዴት መጀመርን ትችላላችሁ? ለፍጥረት ሁሉ የሚሰጠውንና ሁሉንም የሚመግበው ክርስቶስ ላይ ተስፋችሁን ጣሉ። ኢፍትዊ ከሆነ ማግኘት ራቁ። ከቅና በላባችሁ ገኛችሁት ገንዘብ ጋር እንኳን አብዝታችሁ አትቆራኙ፣ አትሳቡ አትውደዱትም። ለበጎ ምግባር አድርጉት ሆች የሚቻለውን ያል ይካፈሉ። ይህ ራስን ክዶ መስቀልን ከመሸከም ትእዛዝ ጋር ተመሳሳይ ትእዛዝ ነው። እንደ ፈቃዱ የሚኖሩ የእግዚአብሔር ሰዎች ሥጋ/ሰውነት ያላቸው ቢሆኑም ከእርሱ ጋር ብዝተው የተቆራኙ አይደሉም። በተቃራኒው አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ስተዋጽኦውን ይጠቀማሉ። (ከሥጋ) ይነጠሉ ዘንድ ሲጠሩ ያደርጉት ዘንድ ዝግጁ ናቸው ስለ ሥጋ ፍላጎትና ባርይ እንደዚህ ካደረጋችሁ ከዚህ በላይ አንዳች ማድረግ ባትችሉ እንኳን ይህ (ብቻውን) መልካምና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነው። የዝሙት ሳብ በውስጣችሁ በኃይል ሲነ ተመለከታላችሁን? (እንዲህ ከሆነ) አሁንም ራሳችሁን እንዳልሰቀላችሁ እወቁ። ይህ እንዴት ሊተገበር ይችላል? ሴቶችን በጥልቀት፣ በጉጉትና በመደነቅ ከመመልከት ሽሹ። ከእነርሱ ጋር ካለ አላስፈላጊ ከሆነ ቅርበትና አላስፈላጊ ከሆነ ንግግር ራቁ። መጠጣት፣ መስከር፣ እስክትጠግቡ ድርስ መመገብና አብዝቶ መተኛት በመተው ለዚህ ስሜት ጉልበት የሚሰጡትን ነገሮች ቀንሱ። እነዚህን ክፉ ነገሮች ከመተው በተጨማሪ ትት ልቡናን ጨምሩበት እነዚህን ስሜቶች ለመዋጋት ይረዳችሁ ዘንድ በጭምት ልብ ወደ እግዚአብሔር ተጣሩ። ከዚያ በኋላ፡- “ኃጥን ከፍ ከፍ ብሎ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ለምልሞ አየሁት። ብመለስ ግን አጣሁት ፈለግሁት ቦታውንም አላገኘሁም” (መዝ 36(37)፥3536)።
ክብርን በመውደድ ሳብ ተቸግራችኋልን? በጉባኤ አልያም በስብሰባ መል ስትሆኑ ጌታ በወንጌል ስለዚህ ጉዳይ የተናገረውን ምክር አስታውሱ። በምትናገሩበት ጊዜ ሌሎች ላይ የበላይ ለመሆን አትሞክሩ። ያላችሁን መልካም ምግባር ለእርሱ ብቻ በማሳየትና በእርሱ ብቻ በመታየት በስውር ተግብሩ። በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል (ማቴ 6፥6)። የሁሉንም ክፉ ስሜቶች ምንጭ ከቆረጣችሁ በኋላ ሳባቸው በውስጣችሁ ያናውጻችኋል። በዚህም አትፍሩ። ያስቸግራችኋል ሆኖም ግን ፈጽሞ ድል አያደርጋችሁምና ያውም አይደለምና አክሊልን ያስገኝላችኋል። መንፈሳዊ በሆነ ትግላችሁ ድል የተደረገ ሙት የሆነ እንቅስቃሴ ነው።
የመስቀሉ ቃል እንዲህ ነው (1ኛ ቆሮ 1፥19 ጋር ያነጻጽሩ)። (የመስቀሉ ቃል) ከመፈጸሙ አስቀድሞ በነቢያት ጊዜም ብቻ ሳይሆን አሁንም ከተፈጸመ በኋላም ታላቅና መለኮታዊ ምጢር ነበረ ነውም። ይህ ለምን ሆነ? በሁሉም ነገሮች ራሱን ትትና ዝቅ የሚያደርግ ራሱ ላይ ንቀትን የሚያመጣ ይመስላል። ሥጋዊ ፍላጎቶችን የሚሸሽ ማናኛውም ሰው ራሱ ላይ ብርቱ ድካምና ልፋት ብሎም ዘን የሚያመጣ ይመስላል። ያለውን ጥሪት የሚሰጥ ራሱን ድ የሚያደርግ ይመስላል። ነገር ግን በእግዚአብሔር ኃይል ይህ ድህነት፣ ዘንና መናቅ በዚህና በሚመጣው ዓለም የማያልቅ ብት፣ በቃላት የማይገለጥ ደስታና ዘላለማዊ ክብርን ይወልዳል። ጳውሎስ ይህንን የማያምኑትንና እምነታቸውን በተግባር የማይገልጡትን ከጠፉት አልያም ከግሪካውያን ጋር ይደምራቸዋል። እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን ይለናል (አይሁድ) አዳኝ የሆነውን (የክርስቶስ) መከራ ስለማያምኑ ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ  (አዛብ/ግሪኮች) የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ፈጽመው ባለማመናቸውም ምክንያት ከሁሉም በላይ ለጊዜያዊና ላፊ ለሆኑ ነገሮች ዋጋ ስለሚሰጡ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው (ካለ በኋላ) “ለተጠሩት ግን፥ . . . የእግዚአብሔር ኃይልና የእግዚአብሔር ጥበብ የሆነው ክርስቶስ ነው” ይላል (1ኛ ቆሮ 1
፥23)።
በድካም ድል ማድረግ፣ ዝቅ በማለትና በትትና ከፍ ማለት፣ በድህነት ባለ ጸጋ መሆን ይህ የእግዚአብሔር ጥበብና ኃይል ነው። መለኮታዊ የሆነው ክብር የሚያስፈልጋቸው የመስቀሉ ቃልና ምጢር ብቻ ሳይሆኑ ምልክቱም ጭምር እንጂ። ምልክቱ ቅዱስ፣ አዳኝና ክቡር ማኅተም ነው። እግዚአብሔር ለሰው ዘር በሙሉ ያደረገውን መልካም፣ ድንቅና ከቃላት በላይ ሆነውን ነገር ሁሉ መቀደስና ፍጹም ማድረግ የሚቻለው ነው። እርግማንንና ኩነኔን ማስወገድ፣ ሞትንና መበስበስን የሚያጠፋ፣ ዘላለማዊ ይወትና በረከትን የሚሰጥ ነው። ምንም እንኳን የምንፍቅና ተከታዮች በቅናት የሚከፉና ቅር የሚሰኙ ቢሆኑም መስቀል የድኅነት እንጨት[2]፣ በትረ መንግት፣ በሚታዩና በማይታዩ ጠላቶች ላይ መለኮታዊ የድል ሽልማት/አክሊል ነው። እንዲህ የሚለውን የሐዋርያውን ጸሎት አልደርሱበትም “ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ስፋቱና ርዝመቱ ከፍታውም ጥልቅነቱም ምን ያህል መሆኑን ለማስተዋል፥ ከመታወቅም የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ ትበረቱ ዘንድ (ኤፌ 3፥18)። የጌታ መስቀል በሥጋ የመምጣቱን ምጢር በሙላት እንደሚገልና የዚህን መገለ ሙሉ ምጢር እንደያዘ አልተረዱም። በሁሉም አቅጣጫዎች በመስፋት ከላይ፣ ከሥር፣ በዙያና በመካከል ያለውን ነገር ሁሉ ይይዛል። መናፍቃኑ ሰበብ በመደርደር ምክንያታዊ ቢሆኑ ከእኛ ጋር በኅብረት ሆነው ያከብሩት ዘንድ የሚገባውን የክብርን ንጉ (መዝ 23(24)፥710) ምልክት ይጠየፋሉ። ጌታም ራሱ በግልጽ መስቀሉን ሊያከብር ከፍ ማለቱና ክብሩ እንደሆነ ጠቁሟል (ዮሐ 3፥1415)። ዳግም ሲመጣና ራሱን ሲገልጥ ይህ የሰው ልጅ ምልክት በኃይልና ከታላቅ ክብር ጋር እንደሚመጣ አውጇል (ማቴ 24፥30)። 
መናፍቃኑ ክርስቶስ መስቀል ላይ ተቸንክሮ ስለ ሞተ እርሱ የሞተበትን የመስቀል ምልክት መመልከት አቅም እንደሌላቸው ይናገራሉ። ነገር ግን እኛ ባለመታዘዛችን ምክንያት አባታችን (አዳም) እጁን ወደ ዛፉ በዘረጋ ጊዜ በእኛ ላይ ተጽፎ የነበረው የዕዳችንን ጽፈት የት ነበር የተጠረቀው? [3]ወደ እግዚአብሔር በረከት እንድንመለስ አድርጎ ከመንገዳችን እንዴት ነበር የተወገደውና የተቀደደው ? ከመተላለፍ ዛፍ በኋላ ሰልጥነውብን የነበሩትን የርኩሳን መፍስትን አለቆችና ሥልጣናት ክርስቶስ መቼ ነበር የገፈፈውና ያባረረው? እኛ ነ እንወጣ ዘንድ ድል ያደረጋቸውና ያሳፈራቸው የት ነው ? በመካከል የነበረው የጥል ግድግዳ የፈረሰው ከእግዚአብሔር ጋር የነበረው ጠላትነታችንም የሞተውና የተወገደው የት ነው ? ከእግዚአብሔር ጋር በምን ዓይነት መንገድ ነበር የታረቅነው? ከእርሱም ጋር መልካሙን ዜና ወንጌልን እንዴት ነበር የሰማነው? እርግጥ ነው መስቀሉ ላይና በመስቀሉ ነበር። ይህንን የሚጠራጠሩ ሐዋርያው ለኤፌሶን ሰዎች የጻፈውን ያድምጡ “እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፥ ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው”(ኤፌ 2፥1416)። ለቆላስይስ ሰዎች ደግሞ እንዲህ ብሎ ጻፈ “እናንተም በበደላችሁና ሥጋችሁን ባለመገረዝ ሙታን በሆናችሁ ጊዜ፥ ከእርሱ ጋር ሕይወትን ሰጣችሁ። በደላችሁን ሁሉ ይቅር አላችሁ። በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው። እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል። አለቅነትንና ሥልጣናትን ገፎ፥ ድል በመንሣት በእርሱ እያዞራቸው በግልጥ አሳያቸው” (ቆላ 2፥1515)።
በእውነት ይህንን የሁሉም የሰው ልጆን ነነት መለኮታዊ ሽልማት የሆነውን (መስቀል) ልናከብረው ይገባል። መልክና ገጽታው ብቻ የክፋት አባት የሆነውን እባቡን መሸነፉንና መቀጥቀጡን በማወጅ አሸሸው፣ አሸነፈው አዋረደው። (መስቀል) ክርስቶስን ያከብረዋል ከፍ ከፍም ያደርገዋል፣ ድል ማድረጉንም ለዓለም በግልጽ ያሳያል። ክርስቶስ መከራ ሞትን በእርሱ ላይ በመቀበሉ ምክንያት መስቀልን ማቃለልና ማዋረድ የተገባ ቢሆንስ ሞቱም የሚከበርና የሚጠቅም ባልሆነ ነበር። ሐዋርያው እንዳስተማረን እንዴት ከሞቱ ጋር ንድ እንሆን ዘንድ ተጠመቅን (ሮሜ 6፥3)? ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር የተባበርን እንዴት ትንኤውን እንካፈላለን (ሮሜ 6፥5)? በሌላ መልኩ አንድ ሰው የጌታ ስም በላዩ ላይ ሳይጻፍ የመስቀሉን ምልክት ቢያከብር በትክክል ይህ ሰው የተሳሳተ ነገር እያደረገ እንደሆነ ይከሰሳል/ይወቀሳል። ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ(ፊል. 2፥10) ተብሎ ተጽፏልና መስቀል ይህንን ክቡር ስም ተሸክሟል። በክርስቶስ መስቀል ፊት ጉልበትን አለማንበርከክ እንዴት ያለ ሞኝነት ነው !
ልባችንን ወደ ሰማይ ሰቅለንና ከፍ አድርገን ከመዝሙረኛው ዳዊትና ከነቢያቱ ጋር ወደ ማደሪያዎቹ እንገባለን እግሮቹ በሚቆሙበት ስፍራ እንሰግዳለን/እናመልካለን[4] (መዝ 131(132)፥7)። ስለ እኛ ሁሉን የሚያቅፉ እጆቹ ወደ ተዘረጉበት ይወት ሰጪ የሆነውን ሥጋውም ወዳለበት (ወደ ማደሪያዎቹ እናመልከው ዘንድ እንሂድ)። መስቀሉን በእምነት ስናከብረውና ሰላም ስንለው ከእርሱ የሚመነጨውን የተትረፈረፈውን ቅድስና እንቀበል እንያዝም። ምጢርና ስውር ሆኖ ክቡር በሆነው በጌታችንና በአምላካችን በመድኒታችን ዳግም ምጽአት ሐት እናደርግና ጻሜ ወደ ሌለው ደስታ እንሻገር ዘንድ፣ በቀኙ መሆንን አግኝተን ተስፋ የተሰጠውን የደስታ ቃላትና ባርኮት በሥጋ ለእኛ ሲል ስለ ተሰቀለው የእግዚአብሔር ልጅ ክብር እንሰማ ዘንድ። 
መጀመሪያ ከሌለው አባቱ ጋርና ቅዱስ፣ መልካምና ይወት ሰጪ ከሆነው መንፈስ ቅዱስ ጋር ለእርሱ ሁሉም ክብር ይገባዋል። አሁንና ለዘላለም ለትውልደ ትውልድ አሜን! 
ተፈጸመ     
               


[1]ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለ ሆነ ሊያውቀው አይችልም። መንፈሳዊ ሰው ግን ሁሉን ይመረምራል ራሱ ግን በማንም አይመረመርም። (1ኛ ቆሮ 2፥14-15)
[2] ሐዋ 10፥39
[3] ቆላ 2፥14
[4]እዚህ ጋር የእንግሊዘኛውን የብራይስጡ ትርጉም “መስገድ” የሚለውን ሳይሆን “ማምለክ” ብሎ ነው የተጠቀመው። ስግደት የተለያየ መልክና ትርጉም ሊሰጠው የሚችል ቃልና ተግባር ሲሆን አምልክ ግን ለፈጣሪ ብቻ የሚሰጥና የመገዛታችን ማመላከቻ፣ የተፈጠርንበትም ዓላማ ነው ነው።  
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ
አዳዲስ መጻሕፍትን ይግዙ

ተዛማጅ ጽሑፎች

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ