የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ አዲስ ዓመት ከሰበከው /2/

እንኳን ከዘመነ ማርቆስ 2010 ዓ.ም. ወደ ዘመነ ሉቃስ 2011 ዓ.ም. በሰላምና በጤና አሸጋገራችሁ !!
በእግዚአብሔር ዘንድ ክብር ያለውን ሰው ጸጋዎች ከዘረዘረ በኋላ አንድ ሰው በቅዱሱ ድንኳን ለመኖር ምን ዓይነት ሰው መሆን እንዳለበት ይናገራል ። ይህም ነቀፋ የሌለበት ፣ ጽድቅን የሚራ ፣ ከክፋት የራቀ ይልና ይህን ይጨምራል፡- “በአንደበቱ የማይሸነግል ፥ በባልንጀራው ላይ ክፋትን የማያደርግ ፥ ዘመዶቹንም የማይሰድብ ።” (መዝ 14 (15)፥3) በመቀጠልም “ኃጢአተኛ በፊቱ የተናቀ ፥ እግዚአብሔርንም የሚፈሩትን የሚያከብር ፥ ለባልንጀራው የሚምል የማይከዳም ።” (መዝ 15 (16)፥3) ይላል ። ይህ ማለትም ክፋትን መናቅ ፣ መልካም የሆነውንም ማመስገን ከፍጽምና ተግባራት አንዱ መሆኑን ያመላክት ነው ። በሌላም ቦታ እንደገና ይህን ነገር ግልጽ ያደርጋል
እግዚአብሔር ያከበረውን አትንቀፉ ። ምንም እንኳ ድቢሆንም እግዚአብሔር በጽድቅ የሚኖረውን ያከብራል ። እርሱ ምንም ባለ ጸጋ ቢሆኑም ክፋት ውስጥ በሚኖሩት ላይ ፊቱን ያዞራልና እግዚአብሔር የተወውን አታክብሩ ። ነገር ግን የምታመሰግኑ ቢሆን ወይም የምትገስጹ ሁሉንም እግዚአብሔር በፈቀደበት መንገድ አድርጉ
ለእግዚአብሔር ክብር መክሰስ ይቻላል ። ይህ እንዴት ይሆናል ? በተደጋጋሚ በራተኞቻችን እንበሳጫለን ። ይህ ከሆነ ታያ እንዴት ነው ስለ እግዚአብሔር ብሎ መክሰስ የሚኖረው ? አንድ ሰው ሰክሮ አያም ሲሰርቅ ካያችሁ ይህም ሰው ራተኛ ይሁን ወዳጅ አያም ከሚቀርቧችሁ ሰዎች አንዳቸው ወደ ትያትር እየሄዱ አያም ለነፍሳቸው አንዳች ሳይጨነቁ ወይም እየማሉ አያም በሐሰት እየማሉ ፣ እየዋሹ (ካያችሁ) ተቆጡ ፣ ቅጧቸው መልሷቸው ፣ አርሟቸውም ይህ ለእግዚአብሔር ክብር የተደረገ ይሆናል ። አንድ ሰው እናንተ ላይ ኃጢአት ሲያደርግሲበድላችሁ ብትመለከቱ ፣ (ወይም ደግሞ) ሊያደርጉላችሁ የሚገባውንም ነገር ሳያደርጉ ብታዩ ይቅር በሏቸው ። ይህን ካደረጋችሁ ለእግዚአብሔር ብላችሁ ይቅር አላችሁ ማለት ነው ። ነገር ግን አሁን ብዙዎች ወዳጆቻቸው ላይ አያም ራተኞቻቸው ላይ የሚያደርጉት ከዚህ በተቃራኒ ነው ። ሲበድሏቸው መራራና ይቅር የማይል ዳኛ ይሆኑባቸዋል ። ነገር ግን እግዚአብሔርን ሲሳደቡ ነፍሳቸውንም ሲያጠፉ አንዳች አይሏቸውም
አሁንም ወዳጅ ማበጀት የግድ አስፈላጊ ነውን ? ስለ እግዚአብሔር ብላችሁ (ወዳጅ) አድርጓቸው ። ጠላት ማበጀት የግድ አስፈላጊ ነውን ? ስለ እግዚአብሔር ብላችሁ ጠላት አድርጓቸው ። አንድ ሰው (ሌሎችን) ወዳጅ አያም ጠላት የሚያደገው እንዴት ነው ? ይህ የሚሆነው ሰዎች ወዳጅ የምናደገው ገንዘብ ስላላቸው ፣ ማዕድ ስለሚያካፍሉን ፣ ሰዋዊ ድጋፍ ስላደረጉልን ሳይሆን ወዳጅ ማድረግ ያለብን ሁልጊዜ ነፍሳችንን ርዓት የሚያይዙ ፣ አስፈላጊ ነገሮችን የሚያማክሩ ፣ ኃጢአተኞችን የሚገሥጹ ፣ ተላላፊዎችን በግልጥ የሚመክሩ ፣ የወደቁትን የሚያረጋጉ ፣ ወደ እግዚአብሔርም ለመምራት በጸሎትና በምክር የሚያግዙትን ነው ። እንደገና ስለ እግዚአብሔር ብሎ ጠላትን ማፍራት ይቻላል ። አንድ ርዓት የሌለው ፣ ፀያፍ ነገር የሚያደርግ ፣ በክፋት የተሞላ ፣ ስህተት በሆኑ ትምህርቶች የተዘፈቀ ሰው ከተመለከታችሁ ክርስቶስ “ቀኝ ዓይንህም ብታሰናክልህ አውጥተህ ከአንተ ጣላት” (ማቴ 5፥29) ብሎ እንዳዘዘው ከዚህ ሰው ተለዩ ራቁትም ። በዓይን ልክ የሚወደዱ ጓደኞቻችንንና በቀን ተቀን ይወታችን አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች እንኳ ከነፍስ ድኅነት አንጻር የሚጎዱ ከሆ
መቁረጥና መጣል እንዳለብን ሲነግረን ነው
በስብሰባቸው ከተገኛችሁ ንግግራችሁንም ካስረዘማችሁ ይህንንም ቢሆን ለእግዚአብሔር ብላችሁ አድርጉ ። ዝም ካላችሁም ለእግዚአብሔር ብላችሁ ዝም በሉ ። ስለ እግዚአብሔር ብሎ በስብሰባ መሳተፍ ምን ማለት ነው? ከአንድ ሰው ጋር ከተቀመጥህ ስለ ጊዜአዊ ጉዳዮች ፣ ከንቱ ስለሆኑ ካንተ ጋርም አንዳች የሚያገናኝ ነገር ስለሌላቸው ነገሮች አትነጋገር ። ነገር ግን ስለ ክርስትና አስተምህሮአችን ፣ ስለ ሲዖል ፣ ስለ መንግተ ሰማያት ተናገር እንጂ  “ልጣን ማን ያዘ?” “ስልጣን ማን አጣ?” “እሌ በምን ምክንያት ነው ገንዘቡን የከሰረው?” “እሌትርፍ አግኝቶ ባለ ጸጋ የሆነው መቼ ነው?” “እገሌ ከአልጋ ወራሾቹ እንዴት አንዱ አልሆነም?” እና የመሳሰሉ ብዙ ስለሚያሳፍሩና ስማይጠቅሙ ነገሮች አይሁን ። እንዲህ ስላሉ ነገሮች አንወያይ ያም ሌሎች ሲወያዩ አንታገቸው ነገር ግን ምን ዓይነት ንግግር ወይም እንዴት ያለ ተግባር እግዚአብሔርን ደስ እንደሚያሰኝ እናስብ። ተበድላችሁ ፣ ተንገላትታችሁ ፣ ተሰድባችሁ ፣ ተጎሳቁላችሁ ፣ ብዙ ክፉ በሆኑ ነገሮች ተሰቃይታችሁ በእርጋታ ከተቋቋማችሁት ይህያደረሰባችሁ ሰው ላይም አንዳች የስድብ ቃልን ካልተናገራችሁ ስለ እግዚአብሔር ብላችሁ ዝም ብላችኋል ማለት ነው ። ማመስገንና መገጽ ብቻ ፣ አያም ቤመቀመጥና መውጣት ወይም ደግሞ ቃል
ን መናገርና ዝም ማለት ሳይሆን ማልቀስና ማዘን መደሰትና
ሐሤት ማድረግም ለእግዚአብሔር ክብር መሆን አለበት
ወንድማችሁ ኃጢአት ሲያደርግ ስትመለከቱ አያም እናንተ ራሳችሁ በኃጢአት ብትወድቁ ማቃሰትና ማልቀስ ይገባችኋል ። ጳውሎስ እንዳለው “እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ኀዘን ጸጸት የሌለበትን ፥ ወደ መዳንም የሚያደርሰውን ንስሐ ያደርጋልና ፤ የዓለም ኀዘን ግን ሞትን ያመጣል።” (2ኛ ቆሮ 7፥10) በዘናችሁም የማያጸጽት ድኅነትን ታገኛላችሁ ። ሌላ ሰው ታላቅ የሆነ ክብርን ሲያገኝ ከተመለከታችሁ አታንኳሱት ነገር ግን ለእናንተ እንደሆነ መልካም ነገር በመቊጠር ወንድማችሁን ዝነኛ/ገናና ያደረገውን እግዚአብሔርን አመስግኑ ። ከዚህም ደስታ ታላቅ ሽልማትን ትቀበላላችሁ
እስኪ ንገሩኝ ከቅናት በላይ ምን የሚያሳዝን ነገር አለ ? በደስታ ሐሤት ማድረግና ጥቅም ማግኘት የተፈቀደ ሆኖ ሳለ ሌላው ሰው የሚያገኘው ጥቅም ላይ ይናደዳሉ ። በንዴታቸውም ከእግዚአብሔር ቅጣትን ለራሳቸው ያመጣሉመራራ የሆነ ቅጣት ። ስለ እግዚአብሔር ብለን ካደረግናቸው ትንሽ ከሚባለው ነገር ትልቅ ጥቅም የሚገኝ ከሆነ ስለ ምስጋና እና ወቀሳ ፣ ስለ ስቃይና ደስታ ማውራቱ ምን ጥቅም አለው ?
“እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትሆኑ ወይም ማናቸውን ነገር ብታደርጉ ሁሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት ።” (1ኛ ቆሮ 10፥33)። ከጸለይንከጾምን ፣ ከከሰስንይቅር ካልን ፣ ካመሰገንንከገጽን ፣ ከገባንከወጣን ፣ ከሸጥንከገዛን ፣ ዝም ካልንና ከተናገርን ከዚህም የተለየ  ምንም ዓይነት ነገር ብናደግ ሁሉንም ለእግዚአብሔር ክብር እናድርግ ። ምንም ዓይነት ነገር ለእግዚአብሔር ክብር የማይደረግ ከሆነ በእኛ ዘንድ አይደረግ ያም አይነገር። ነገር ግን ትልቅ የሆነ ጉዳይ ይዘን ቢሆን ፣ የጦር መሪያቢሆን ወታደርነት ፣ የማይነገር ብት አያም የትኛውም ቦታ ብንሆን ይህንን ቃል በመረዳታችን አትመን ተሸክመን እንዙር ። ስለዚህ ስንራ ሆነ ስንናገር ሁሉንም ነገር ለእግዚአብሔር ክብር እናደርጋለን። በዚህም በአሁኑ ዓለም ሳለን በሚመጣውም ይወት ከእርሱ የሆነውን ክብር እንቀበላለን። እንዲህ ይላልና፡- “ያከበሩኝን አከብራለሁና፥ የናቁኝም ይናቃሉና ” (1ኛ ሳሙ 2፥30) ። ስለዚህ በቃላት ብቻ ሳይሆን በተግባርም እርሱን (አብን) ዘወትር ከአምላካችን ከክርስቶስ ጋር እናመስግነው ። ምክንያቱም ሁሉም ምስጋና ለእርሱ ይገባዋልና ክብርና አምልኮ ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለም ዓለም አሜን
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ
አዳዲስ መጻሕፍትን ይግዙ

ተዛማጅ ጽሑፎች

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ