የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ

የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

በነቢዩ  ሕዝቅኤል ስለ ተገለጸው ራእይ ኅብረ አምሳላዊ ማብራሪያ

ቅዱሳን የሆኑ ነፍሳት የሚንቀሳቀሱትና የሚመሩት  ልጓማቸውን በሚይዘው በክርስቶስ መንፈስ ነው።”m /አባ መቃርስ/

ዋዕቱ በመጀመሪያ በካህኑ ታርዶ መሞት አለበት በመቀጠል ተቆራርጦ በጨው ከተቀመመ በኋላ በእሳት ይጠበሳል። ካህኑ በመጀመሪያ በጉን ካላረደውና ካሞተ የመዋዕቱ በግ በጨው አይቀመ ። ብሎም ብሎም እንደ መዋዕት ለአምላክ አይቀርብም ። ልክ እንደዚ ነፍስም እውነተኛ ሊቀ ካህን በሆነው በክርስቶስ መዋት (መታረድ) አለባት ። በዚህም ከራሷ የአስተሳሰብ መንገድና ክፉ ከሆነው የኃጢአት መንገድ ተለይታ መሞት ትችላለች። የመጥፎ ፍላጎት ጥርቅም የሆነው ይወት ማለፍ አለበት። ልክ ሥጋችን ነፍሳችን ተለይታት ስትወጣ እንደሚሞት፤ እንደ ቀድሞው እንደማይኖር፤ እንደማዳምጥና እንደማይራመድ ሰማያዊ ሊቀ ካህናችን ክርስቶስም በኃይሉ ጸጋ ለዚህ ዓለም ያለንን ኑሮ አርዶ ሲገድለው ከዚህ በፊት ይኖርበት ለነበረው ክፉ ሕይወት ምውት ይሆናል። ከዚህ በኋላ መስማት ማየት ወይም በጨለማ ኃጢአት ውስጥ ዜጋ አይሆንም። ምክንያቱም የይወት ጸር የነበሩት መጥፎ ስሜቶች በጋው ስለ ተወገዱ ነው ። ሐዋርያውም እንዲህ እያለ ይጮ ፡- “ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት” (ገላ.6:14)። በዚህ ዓለም በኃጢአት ጨለማ የምትኖረው ወደ ፈጣሪዋም በሞት ያልተጠቀለለችው ነፍስ ነገር ግን አሁንም በውስጧ ክፋት ማለትም የጨማው ዓለም የክፋት ስሜት በውስጧ አለ እሱም ይገዛታል። ይህም የክርስቶስ አካል አይደለም። የብርሃንም አካል አይደለም ። ነገር ግን የጨለማው አካል ነው። ነገር ግን የብርሃን ነፍስ ማለትም የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ያላቸው የብርሃን አካል ናቸው።
ነገር ግን አንድ ሰው እንዲህ ሊል ይችላል ፡- ነፍስ የተፈጠረችው ከጨለማ ሳይሆን እንዴት የጨለማ አካል ነች ይባላል? ሊል ይችላል ።ተከታተለኝ በክክልም ተረዳኝ ። አሁን የለበስከው ሹራብ ሌላ ሰው ርቶት አንተ እንደለበስከው ቤትህም ሌላ ሰው ገንብቶት አንተ እንደምትኖርበት እንዲሁ አዳም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሲተላለፍና ክፉውን እባብ ሲያዳምጥ ራሱን ለክፉው መንፈስ ሸጠ ። ክፉውም መንፈስ በእግዚአብሔር መልክ የተፈጠረችውን የአዳምን ነፍስ ክፋቱን አለበሳት። ይህንንም ሐዋርያው እንዲህ ሲል ገለ፡- “አለቅነትንና ሥልጣናትን ገፎ ፥ ድል በመንሣት በእርሱ እያዞራቸው በግልጥ አሳያቸው” (ቆላ 2፡12)። የጌታ መምጣት ዋና ዓላማም ይህ ነበር ። ይህንን ጨለማ ገፎ ማደሪያውና ቤቱ የሆነውን ሰው መመለስ ። ነፍስ ነፍስ የጨለማው ክፋት አካል ነች ያልንበት ምክንያትኃጢአት በውስጧ ስላለ ነው ።የምትኖረው በጨለማው ቁጥጥርና ለጨለማው ስለሆ ነው ። ስለዚህ ቅዱስ ጳውሎስ የኃጢአት አካል የሞት አካል ሲል እዲህ ብሎ ይጠራዋል ፡- “የኃጢአት ሥጋ ይሻር ዘንድ” “ለዚህ ሞት ከተሰጠ ሰውነት ማን ያድነኛል?” (ሮሜ 6፥6፤ ሮሜ 7፥24)። በሌላ በኩል በእግዚአብሔር ያመነች ከኃጢአትም የዳነችና ለጨለማው ዓለም የሞተች ነፍስ የመንፈስ ቅዱስን ብርሃን እንደ ይወት ተቀብላለች በዚህም መንገድ በእውነት ወደ ይወት መጥታለች ። በዚህም ይወት ለዘላለም ትኖራለች። ምክንያቱም በእግዚአብሔር ብርሃን ቁጥጥር ስር በመዋሏ ነው። ነፍስ የተፈሮ ባሕርይዋ ከእግዚአብሔር አልያም ከክፉው ጨለማ አይደለም ።ነገር ግን ተመራማሪ ውብ ታላቅና ድንቅ መጠነኛ የእግዚአብሔር መልክና አርአያ ያላት ፍጡር ነች። የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመተላለፏ ነበር የጨለማው ክፋት ወደ እርሷ የገባው
ነፍስ የእግዚአብሔብርሃን ኑሯት በዛው በብርሃን ጋ ከብርሃን ጋር አብራ ትኖራለች አልያም የኃጢአት ጨለማ ኖሯት ፍርድ ያገኛታል ። ከእግዚአብሔር ጋር በዘላለማዊ ብርሃን በእረፍት ውስጥ አብራ መኖር የምትሻ ነፍስ አስቀድመን እንደ ተናገርነው እውነተኛ ሊቀ ካህናት ወደሆነው ክርስቶስ መጥታ መታረድ (መዋት) በዚህም ለዓለምአስቀድማ ትኖርበት ለነበረው የጨለማ ክፋት ሞታ ለሌላ ማለትም መለኮታዊ ወደሆነው ይወት መቀየር አለባት ። ልክ አንድ ሰው የሆነ ከተማ ውስጥ ሲሞት በዚያ ከተማ ያሉትን ሰዎች ድምቸውንወሬአቸውን አያም የሚያወጡትን ድምአይማም ነገር ግን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ቶ ድምቅሶ ወደ ሌለበት ወደ ሌላ ክልል ተሸጋግሯል ። ለነፍስም ልክ እንደዚሁ ነው አንድ ጊዜ ከታረደች (ከተዋች) አስቀድማ ትኖርበት ለነበረው የክፋት ከተማ ስሜቶች ከሞተች የጨለማውን ድምፅ ፣ ከንቱ የሆነውንም ክርክርና ቅሶ ወይም የጨለማውን መንፈስ ግርግር አትሰማም ። ነገር ግን በጎ ነገርሰላምየእግዚአብሔርብርሃን ወደ ተሞላ ከተማ ትሸጋገራለች ። በዚያም ትኖራለችሰማለች የከተማውም ዜጋ ስለምትሆን ትናገራለችበጋራ ትኖራለች ዚያም በእግዚአብሔር ዘንድ ዋጋ ያለው መንፈሳዊ ሥራ ትራለች
ስለዚህ በእርሱ ኃይል ተውተን ለጨለማና ለክፉው ዓለም እንድንሞት ፣ የኃጢአትም መንፈስ ከውስጣችን እንዲጠፋ የሰማያዊውንም መንፈስ እንድንቀበልና እንድንለብሰውከክፉውም ጨለማ ወደ ክርስቶስ ብርሃን እንድንሸጋገር በይወትም ለዘዓለም እንድናርፍ እንልይ ። በሠረገላዎች ውድድር ላይ እንዳለው ከፊት ሆኖ የሚቀድመው የተከታዩን መንገድ እንደሚዘጋበት ወደ ፊት እንዳይጓዝ ድል እንዳይደግ መሰናክልም እንደሚሆንበት የኃጢአት ሳብም ሰውን ይይዘዋል ። የኃጢአት ሳቦች መነት ከጀመሩ  ነፍስን ወደ ፊት ተጉዛ ወደ እግዚአብሔር እንዳትጠጋ ድልንም ከእርሱ እንዳትወስድ መሰናክል በመሆን መንገዷን ይዘጉባታል ። ነገር ግን ጌታ የነገበት የነፍስንም ልጓም በእጁ የያዘበት ሁልጊዜ ድል ያደርጋል  ምክንያቱም በጥበብ እየመራና እያስተዳደረ የነፍስን ረገላ ወደ ሰማያዊና ወደ ተነቃቃ መንፈስ ስለሚወስደው ነው ። እሱ እግዚአብሔር ከክፋት ጋር አይጣላም ነገር ግን በራሱ ከፍ ያለ ሥልጣንና ኃይል ስላለው ድልን ለራሱ ያደርጋል ። ስለዚህ ኪሩቤል መሄድ ወደ ፈለጉበት ሳይሆን የሚጓዙት ረገላ ነጂው ወዳዘዛቸው ነው ። እሱ ወደ ፈቀደው ይሄዳሉ እርሱም ይረዳቸዋል ። መጽሐፉም ፡- “በእያራቱ ጐድናቸው እንደ ሰው እጅ ነበረ” (ሕዝ 1፥8)  ይላል።  ቅዱሳን የሆኑ ነፍሳት የሚንቀሳቀሱትና የሚመሩት ልጓማቸውን በሚይዘው በክርስቶስ መንፈስ ነው። ክንፍ ለአእዋፍ እንደ እግር እንደሚሆንላቸው ሰማያዊው የመንፈስ ብርሃን የነፍስን የአሳብ ክንፍ ይዞ መልካም በሚባለው ጎዳና ይመራታል
ስለዚህ እነዚህን ነገሮች ስትሰሙ በእውነት እነዚህ ነገሮች በነፍሳችእንዳሉ ራሳችሁን ተመልከቱ። እነዚህ በቃላት ብቻ የሚነገሩ ተራ ነገሮች ሳይሆኑ በነፍስ የሚሩ የእውነት ተግባሮች ና እንደ እነዚህ ያሉት በጎ መንፈሳዊ በረከቶች ከሌሉህ ለመንግተ ሰማያት ሙት ስለምትሆን ሁልጊዜ ንዴት ፣ ኀዘንና ችግር ይኖርብሃል ። ይህእውነተኛ ይወትም እንዲሰጥህ እንደ በሽተኛ ሰው ወደ ጌታ አልቅስ በእምነትም ለምን ። እግዚአብሔር የእኛ የሆነውን ይህንን አካል (ሥጋ) ሲፈጥረው ከራሱ (ሥጋ) ባርይ ወይም አካላችን በራሱ ይወት እንዲኖረው አድርጎ አልፈጠረውም ። ሰውን ሲፈጥር እርቃኑን አድርጎ  በመፈጠር ለይወት አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ሁሉ ከእርሱ ውጭ ካሉ ነገሮች (ከተፈጥሮ) እንዲያገኝ አደረገው ።  ይህም አካላችን ከራሱ ሌላ (ከተፈጥሮ) ካሉ ነገሮች ውጪ መኖር አይሆንለትም ። ማለትም ከምግብከመጠጥና ከልብስ ተለይቶ መኖር አይችልም ። ከውጪው አንዳች ሳይወስድ በራሱ ተፈጥር ብቻ መኖር ከሞከረ ይሞታል ይጠፋል ። ይህ ነገር በተመሳሳይ መልኩ ለነፍስም ይራል ። በእግዚአብሔር መልክ የተፈጠረች ብትሆንም የመለኮት ብርሃን የላትም። እሱም ከእግዚአብሔር እንጂ በራሷም ይወት እንዳይኖራት ወድዶ ስለ ጠባይዋ ወስኗል ። የእርሱ መንፈስ የእርሱ ብርሃን ለነፍስ እውነተኛ የሆነ ይወት መንፈሳዊ መጠጥመንፈሳዊ ግብሰማያዊ ልብስ በመሆን እውነተኛ ይወትን ሰጥቷታል
እስካሁን የአካላችን ይወት በራሱ እንዳልሆነ ነገር ግን ከውጭ ማለትም ከመሬት (ከተፈጥሮ) ኖ ውጫዊ ከሆኑት ነገሮች ተለይቶ ይወት እንደሌለው አይተናል ። ልክ እንደዚሁ ነፍስም “በሕያዋን ምድር” ካልተወለደች ከያዋንም ምድር መንፈሳዊውን ምግብ ተመግባ ወደ ጌታ ካላደገች ከቃላት በላይ በሆነው መለኮታዊ ውበትም ካልተዋበች ነፍስ እነዚህን ካልተመገበች በደስታና በረፍት በራሷ መኖር አትችልም ። መለኮታዊ ባርይ እንዲህ የሚሉትን የይወት እንጀራ ይዟል ። እኔ የይወት እንጀራ፣ ይወት ውነኝ (ዮሐ 6፥35፤ 4፥10) ፤ የሰውን ልብ ደስ የሚያሰኘው ወይን (መዝ 104፥15)፤ የደስታ ዘይት (መዝ 45፥7) ሁሉም የሰማያዊውም መንፈስ የምግብ ዓይነቶችንና ከእግዚአብሔር የሚመጣውን ሰማያዊ ውብ ብርሃን። በእነዚህ ምግቦች የነፍስ ዘላለማዊነት ይቀጥላል። አካል (ሥጋ) በራሱ ተፈጥሮ መደገፍ ሲጀምር ወዮለት። ነፍስም በሌላ ነር ሳይሆን በራሱ ተፈጥሮ ሲቆምመታመኑንም በራሱ ራ ላይ ሲያደርግከእግዚአብሔር መንፈስም ጋር ሕብረት ካላደረገ ከእግዚአብሔር የተሰጠውን ዘላለማዊ ይወት ሳያገኝ ይሞታልና ወዮለት ። አንድ ሰው ታሞ ምንም ዓይነት ምግብ አልወስድሲል ሰዎች በይወት ስለ መኖሩ ተስፋ ይቆርጡበታል ። ዘመዶቹና ጓደኞቹ ሁሉ በዕንባ ይሞላሉ ። በተመሳሳይ መልኩ እግዚአብሔርና መላእክቱም ነፍስ ከመንፈስ በሚገኘው ሰማያዊ ምግብ ሳትመገብ ወደማያልፈውም ይወት ሳትመጣ ስትቀር ያለቅሳሉ ። እነዚህ ነገሮች አስቀድሜ እንደ ተናገርኩት ዝም ብለው ሚነገሩ ተራ ቃላት ሳይሆኑ የመንፈሳዊ ይወት ሥራበነፍስ ላይ የተራ ትክክለና የእውነት ሥራዎች ናቸው
ከእንግዲህ የእግዚአብሔር ዙፋን ከሆንህ ፣ ሰማያዊውም መሪ ከከተመብህሙሉ ነፍስህም ዓይን ከሆነችነፍስህም ሙሉ ብርሃን ከሆነችከመንፈስ ቅዱስም ምግብ ከተመገብህ ፣ ይወት ውሃም ከጠጣህከቃላት በላይ ውብ የሆነውንም የብርሃን ልብስ ከለበስህ ፣ ውስጣዊ ማንነትህም የቆመው በእነዚህ ነገሮች ህልውና ከሆነ ይወትህ ዘላለማዊ እንደሆነ ነፍስህም በጌታ ረፍት እየኖረች እንደሆነ እወቅ ። እነዚህን ስጦታዎች ከጌታ እንደ ተቀበልካቸውና በእውነትም ከተጠቀምባቸው እውነተኛ ይወት እንደምትኖር አስተውል ። ነገር ግን እነዚህ ጸጋዎች እንደሌሉህ ካወቅላለማዊውንሰማያዊውን ስጦታ አላገኘህምና እያዘንበፀፀት አልቅስ አንተ ጎስቋላ ችግር ውስጥ ስለሆንክ ጌታን ቀን ለምነው ። ምክንያቱም አሰቃቂ በሆነው የኃጢአት ድህነት ወድቀሃልና ። ምክንያቱም አንድ በጽኑ የተቸገረ ጌታንም ሁልጊዜ የሚጠይቅና የሚፈልግ ሰው ዲያውኑ ወይም ቆየት ብሎ ቤዛነትንና ሰማያዊ ብቶችን ያገኛል ። ይህ ማለት ጌታ ስለ ክፉው ዳኛና ስለ መበለቷ ባስተማረው ትምህርት መጨረሻ ላይ እንዳለው መደምደሚያ ነው። “እግዚአብሔር እንኪያስ ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ለሚታገሣቸውም ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን? እላችኋለሁ ፥ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል” (ሉቃ 17፥7-8)። ለእርሱ ክብርና ኃይል ይሁን ለዘላለሙ  አሜን።
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ
አዳዲስ መጻሕፍትን ይግዙ

ተዛማጅ ጽሑፎች

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ