የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

እረኞች ዘመሩ

                         እሁድ፣ ታኅሣሥ 29 2004
ጠቢባን ፍጻሜ ጥበባቸው
ሊቃውንት የመደምደሚያ ቃላቸው
የነቢያት ትንቢት ዖሜጋ
የመዳን ጥንተ መሠረት አልፋ
ለሩቅ ምሥራቅ ሰዎች ምሥራቃቸው
እውነት የሚያበራ መሪ ኮከባቸው
የዘመናት ጥማት ሕልም ናፍቆታቸው
ላመኑ ተስፋውን የእንጀራ ቤታቸው

ተወለደ ንጉሥ የዓለም መድኃኒት
ከዳዊት ከአብርሃም ከቦዔዝ ከሩት ቤት
ከድቅድቅ ጨለማ ዳክረው ለባዘኑ
በመረረ ልቅሶ በቊስል ላዘኑ
እረኛ አልባ ሆነው ለተቅበዘበዙ
ለሕይወት ተፈጥረው በሞት ለፈረሱ
በስሉ ኃጢአታቸው ጸጋ ክብራቸውን ቆርጠው ለበጠሱ
በዳዊት ኤፍራታ ተወለደ ጌታ
ድንቅ መካር ኃያል የሰላም አለቃ
ሕልም ተከተተ ራእይ ተፈፀመ
የቀዳማይ ምጽአት ትንቢት አከተመ
ጠቢባን አረፉ ሊቃውንት ዝም አሉ
እረኞች ዘመሩ ለፍጻሜ ቃሉ፡፡   
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ
አዳዲስ መጻሕፍትን ይግዙ

ተዛማጅ ጽሑፎች

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ