የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

እስከ መቼ አትምረንም ?

ጌታ ሆይ የምንጠብቀው የሚጠብቀን ካንተ በቀር ማነው ?

ቸር ሆይ! ያለንን ሁሉ እየተነጠቅን የሌለንን የምንናፍቀው ምስኪኖች ካንተ በቀር ሰጪአችን ማነው?

ወጋገን አየን ስንል የሚጨልምብን ፣ ከእህል ረሀብ ወደ ፍቅር ረሀብ የተሸጋገርን ካንተ በቀር ተስፋችን ማነው ?

ፍቅር ጌታ ሆይ ! የማልቀሻ ስፍራችን ፣ ሸክም የምናራግፍባት ደጀ ሰላማችን ፣ ደምን በይቅርታ ፣ በደልን በፍቅር የምንለውጥባት አንድ ዓይናችን የሆነች ቤተ ክርስቲያን ስትጎዳ ካንተ በቀር የሚያድናት ማነው ?

ገዳይም ሟችም እኛው ሁነን ፣ ፉከራም ልቅሶም ሲጠፋብን ካንተ በቀር ወደ ሕሊናችን የሚመልሰን ማነው?

አንዲት ቤተ ክርስቲያን አንድ እንድትሆን ፣ ሕመምና ልቅሶአችን ዳርቻ እንዲያገኝ እንማጸንሃለን! አማኑኤል ሆይ! በክንፍህ መዘርጋት አንተ ጋርደን ። ከልቅሶም ልቅሶ አለውና የቤተ ክርስቲያን ደጆች በምሕረት ይከፈቱልን ። እውነተኛው አዳኝ ክርስቶስ ሆይ ! አደባባይ የቆምህላት ቤተ ክርስቲያን አደባባይ ቆማለችና አንተ አስባት ! ለዘላለሙ አሜን !

ዲያቆን አሸናፊ መኮንን

በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ
አዳዲስ መጻሕፍትን ይግዙ

ተዛማጅ ጽሑፎች

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ