የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

ምንድን ነው መክሊት ቀበራ?

                         ሰኞ፣ መጋቢት 17 2004
ተሹመህ በብዙ ጸጋ
እንድትጠቅም እንድትረባ
አሽተህ እንድታፈራ
መንጭተህ እንድታረካ
በቃሉ መነጽርነት
አቅርበህ የሩቅ ሚስጢራት
ወደ ህይወት የእውነት  መዲና
ተቃንተህ እንድታቀና

ላኪህን ጌታ አንግሰህ

በአለቱ በእርሱ ጸንተህ
በግርማ ሆነህ በፊቱ
ታምነህ ለቃል መክሊቱ
ወደ ህያው የፅዮን ተራራ
ይገባሃል ነፍሳትን መንገድ እንድትመራ፡፡
አንድ፣ ሦስትና አምስት የእውነት አደራ
በተሰጠህ ልክ ስራ እንድትሰራ
በሰፊው ሁዳድ ዘር እንድትዘራ
አብበህ መአዛህ ሸቶ
ፅናትህ ድኩም አፅንቶ
ማረፍህ ተቅበዝባዥ ተክሎ
በልብህ ጌታ ተስሎ
ባንተ ሕይወት እርሱ ተነቦ
ለዚህ ነው ያንተ መመረጥ
ሳታረጅ ጎበዝ አትጉበጥ
ምንድን ነው መክሊት ቀበራ?
ደከመኝ ሳይሰሩ ስራ
ምንድን ነው የጥምጥም ጉዞ?
መንፈሱ ለጽድቅ ታዞ
አትናቃት አንዲቷን መክሊት
ናትና የሰማይ ፍኖት
አትሁን እንደጋን መብራት
ስበከው ጩህ በሰገነት
አትፍራ አብዝተህ ጩኸው
መክሊቱን አውጥተህ አውርደው
አሊያ ግን እንዳታስበው
ቀብሮ ለማስቀረቱ
መቃብር የማይሸሽገው ሕያው ነው የጌታ እውነቱ
በአንተ ይብስብሀል ስለት ላይ ደርሰህ ለቆምከው
መሞትን ምርጫ አድርገህ ወደ ውጭ ራስክን ለጣልከው፡፡
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ
አዳዲስ መጻሕፍትን ይግዙ

ተዛማጅ ጽሑፎች

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ