ስለ ሁላችን ሞትህ ፣ እኛ ግን ስለ ግላችን እንኖራለን ::
ስለ ኃጢአታችን ሞትህ ፣ እኛ ግን ጽድቃችንን እናወራለን ::
ሕማምህን እናስባለን ፣ ሰውን በክፋት እናሳምማለን ::
አንድ ልታደርገን ሞትህ፣ እኛ ግን ኢየሱስ የእኔ ብቻ ነው እያልን እንጣላለን ::
አንተ ግን መሐሪ ነህ ፣ እንደገና ስንሰቅልህም ትወደናለህ ።
እንኳን ሞትክልን ፣ በዚህች የተባረከች ቀን በአንድ ዓይናችን እያለቀስን በአንድ ዓይናችን እንደሰታለን ::
የተሰቀልኸው ሆይ ! ፊደላችን ነህ እንማርብሃለን ፣
መብላችን ነህ እንጠግብሃለን ፣
ሰንደቃችን ነህ እንጠራብሃለን ፣
ሽማችን ነህ እንደምቅብሃለን ::
ተመስገን!
ሚያዝያ 2 ቀን 2018 ዓ.ም