መግቢያ » ልዩ ልዩ ሁለት » የተሰቀልኸው ሆይ !

የትምህርቱ ርዕስ | የተሰቀልኸው ሆይ !

ስለ ሁላችን ሞትህ ፣ እኛ ግን ስለ ግላችን እንኖራለን ::
ስለ ኃጢአታችን ሞትህ ፣ እኛ ግን ጽድቃችንን እናወራለን ::
ሕማምህን እናስባለን ፣ ሰውን በክፋት እናሳምማለን ::
አንድ ልታደርገን ሞትህ፣ እኛ ግን ኢየሱስ የእኔ ብቻ ነው እያልን እንጣላለን ::
አንተ ግን መሐሪ ነህ ፣ እንደገና ስንሰቅልህም ትወደናለህ ።
እንኳን ሞትክልን ፣ በዚህች የተባረከች ቀን በአንድ ዓይናችን እያለቀስን በአንድ ዓይናችን እንደሰታለን ::

የተሰቀልኸው ሆይ ! ፊደላችን ነህ እንማርብሃለን ፣
መብላችን ነህ እንጠግብሃለን ፣
ሰንደቃችን ነህ እንጠራብሃለን ፣
ሽማችን ነህ እንደምቅብሃለን ::

ተመስገን!

ሚያዝያ 2 ቀን 2018 ዓ.ም

በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ

ተዛማጅ ትምህርቶች

የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ