የልብ አውቃው የኢየሱስ እናት ማርያም ሆይ እንወድሻለን!
የደስታ ጥጉ የፋሲካው የኢየሱስ እናት ማርያም ሆይ እንወድሻለን!
ሸሽጎ የሚያጎርሰው የሰጪው የኢየሱስ እናት ማርያም ሆይ እንወድሻለን!
የፍሬው የኢየሱስ እናት አበባ ማርያም ሆይ እንወድሻለን!
ሁሉን ሳይዘነጋ የሚያስበው የመልካሙ የኢየሱስ እናት ማርያም ሆይ እንወድሻለን !
የድሆች ወዳጅ የተባለው የኢየሱስ እናት ማርያም ሆይ እንወድሻለን !
ልማዱ ሰውን ማፍቀር የሆነው የኢየሱስ እናት ማርያም ሆይ እንወድሻለን !
ላመኑበት የማይጠልቀው ፀሐይ የኢየሱስ እናት ማርያም ሆይ እንወድሻለን !
ከማለዳ ይልቅ የተዋበው የኢየሱስ እናት ማርያም ሆይ እንወድሻለን!
የረሀብ መድኃኒት የሆነው የኢየሱስ እናት ማርያም ሆይ እንወድሻለን!
የክፉ ዘመን መጠጊያ የሆነው የኢየሱስ እናት ማርያም ሆይ እንወድሻለን!
አንቺን የወደደ አንዱ አብ ቡሩክ ነው፣ ለእናትነት የመረጠሽ አንዱ ወልድ ቡሩክ ነው ፣ ያጸናሽ አንዱ መንፈስ ቅዱስ ቡሩክ ነው።