መግቢያ » ግጥም » ብቻውን እናምልክ

የትምህርቱ ርዕስ | ብቻውን እናምልክ

                      ሰኞ፣ ጥር 28 2004 ዓ.ም.
በጸናች ክንዱ
በተዘረጋች እጁ
በድንቅ እየሠራ
ምሪት እየመራ
ያዳናቸውን ቃል የዕሪታቸውን መልስ
ኪዳኑን ሲረሱ ልባቸውም ሲረክስ
የአርባ ቀን ቆይታ ትዕግስት ነስቷቸው
ያወጣን ያዳነን ሙሴ ቀረ ብለው
የሚታዩ አማልክት ሊሰሩ መከሩ
በአመጻ ሰልጥነው ፍጹም ደነቆሩ
ሙሴ አዳነን ብለው ስህተትን ሳቱ፡፡
ቁልቁል ተንደርዳሪ የለውም መቆሚያ
ሙሴንም ጣሉና ሰገዱ ለጥጃ
ከግብጽ ባርነት ከሞት ቤት ያወጡን
እንዲያ እንድናምር ለማዕረግ ያበቁን
እኒህ ናቸው አማልክቱ
ስለደስታው ብሉ ጠጡ
ቀኑ ዛሬ ‹‹የእግዜር›› በዓል ሆኗል
ደስታ ተድላው ተትረፍርፏል
ብለው ገና ሳይጨርሱ
መጣ የአምላክ ጽኑ ፍርዱ፡፡
ከሰገነት መውረድ መቅኖ የለሽ ጉዞ
ደንቁሮ ታውሮ ተዋርዶ ደንዝዞ
ጥቂት በመታገስ ጸንተው ስላልቆሙ
ትልቁን ፈጣሪ በክፉ አማልክት ዝሙት ስላስቀኑ
ከህይወት መጽሐፍ ተደምስሰው ጠፉ፡፡
በሚከፋ ስህተት እኛም እንዳንያዝ
ሰብሮ በሚያቆስለው በሰንበሌጥ ምርኩዝ እንዳንመረኮዝ
አይናችንን ከእርሱ ከትልቁ ጌታ
ነቅለን ወደፍጡር አናድርግ ለአንድ አፍታ
አሊያ እንደ እስራኤል ነውና መዋረድ
እርሱን አንዱን ጌታ ብቻውን እናምልክ፡፡
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ

ተዛማጅ ትምህርቶች

የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ

አዳዲስ መጻሕፍት

ትርጉሙ:- ቀይ ዕንቈ

ለምድራችንና ለአገልግሎታችን በረከት የሆነ መጽሐፍ
የመጀመሪያ እትም ጥቅምት 2016 ዓ.ም

1ኛ ጢሞቴዎስ ትርጓሜ – ክፍል አንድ

የመጀመሪያ እትም ሐምሌ 2013 ዓ.ም

ምክር አዘል መጽሐፍ

የመጀመሪያ እትም