የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ

የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

ስብከት አራት

ክርስያኖች ሰማያዊውን ስጦታ ከእግዚአብሔርና ከመላእክት እንዲቀበሉ በዚህ ዓለም ያላቸውን ሩጫ በማስተዋልና በጥንቃቄ መሮጥ እንዳለባቸው የተሰጠ ስብከት
1. እኛ የክርስትና ይወትን በጥልቀት ፈጸም የምንፈልግ ሰዎች ከሁሉም ነገር በፊት ባለን አቅም ሁሉ የመለየት አቅም ያለውን የነፍሳችንን ክፍል መንከባከብ አለብን ። በዚህም ጥሩውን ከመጥበእርግጠኝነት የመለየትና ያልተበላሸውን ንጹሕ ተፈጥሮ እንድናገኝ ይረዳናል ይህም ግ ሳናፈርስ ታማኝና ግልጽ ሁነን መልካም ነገርን መፈጸም ያስችለናል ይህንን የመለየት ችሎታ እንደ ዓይን አድርገን ከኃጢአት ሳቦች ጋር ብረት ከማድረግ ነእንወጣለን ። በዚህም ለጌታ የተገባን እንድንሆን የሚያደርጉን ሰማያዊ ስጦታዎች ይሰጡናል ። ከሚታየው ዓለም ማሳያ እንውሰድ ። በነፍስና ሥጋ ፤ በግዙፉ ሥጋ ክፍሎችና በነፍስ ክፍሎች በስሜት ዋሶቻችንና በማይታየው ስሜታን መካከል መመሳሰል አለ
2. ሰውነት የሚመራበት ዓይን አለው ። ዓይን በማየት ሙሉ ሰውነታችንን ቀጥ ብሎ እንዲጓዝ ያደርገዋል ። እስኪ አንድ ረግረግና እሾህ በሞላበት ጫካ ውስጥ የሚጓዝ ሰው አስቡ ። ሰውየው በሚጓዝበት ጊዜ እሳት ተነ፤ በሚረግጠው መሬት ላይም የተሰኩ ጎራዴዎች አሉ ። መንገዱ ላይም ብዙ ኩሬዎችና ገደሎች አሉ ። ፈጣን የሆነው በትኩረትና በፍጥነት የሚሄደው ተጓዥ በዓይኑ መሪነት በጣም አስቸጋሪ የሆኑ ቦታዎች በትኩረት ያልፋቸዋል ። ልብሱ በእሾህና በቆንጥር እንዳይበጨቅ ፤ በረግረጉ እንዳይቆሽሽ በጎራዴውም እንዳይቀደድ በእጁና በእግሩ ይሰበስበዋል። ሁሉንም መንገዶች ዓይኑ ይመራዋል ። የዓይኑ ብርሃን ወደ ገደሉ እንዳይወድቅ ፤ ውሃው ውስጥ እንዳይሰጥም ወይም በሌላ አደጋዎች እንዳይጎዳ ይጠብቀዋል ። ጠንቃቃና ንቁ የሆነው ሰውዬ ልብሱንም በመሰብሰብ በዓይኑ መሪነት ራሱን ከአደጋ ይጠብቃል ። የለበሰውንም ልብስም ከመቀደድና ከመቃጠል ያድናል ። ነገር ግን አንድ ሰው እንዲህ ባለ ቦታ ሲያልፍ ሰነፍ ፤ ግድ የለሽ ገልጃጃና ፈዛዛ ከሆነ ልብሱን ሰብስቦ መያዝ ስለማይችል ልብሱ እየዋለለ በእሾሁና በቁጥቋጦው ይቀደዳል ። አልያም በእሳት ይቃጠላል ። ወይም በየቦታው በተሰኩ ጎራዴዎች ይበጫጨቃል ። በረግረጉም ይቆሽሻል ። በአንድም በሌላም መንገድ ሰውየው ጥሩ ልብሱን በፍጥነት ያበላሸዋል ። በስንናውና በግዴለሽነቱ ዓይኑ የሚያሳየውን በአግባቡ ማድረግ ካልቻለ ራሱ ወደ ገደል ይወድቃል ። ያም ውውስጥ ይሰጥማል
3. ልክ እንደዚሁ በሥጋ ልብነት የምትሸፈነው ነፍስ ራሷን የምትመራበት ነገሮችን የመለየት ችሎታ ያለው ክፍል አላት ። ነፍስ ከግዙፉ ሥጋ ጋር የይወት እሾሆች ፤ ቁጥቋጦዎች፤ ገደሎች፤ ረግረጎች በተባሉት በዚህ ዓለም ምኞቶችና ፍላጎቶች መካከል ስታልፍ ራሷንና ልብስ የሆናትን ሥጋ በሁሉም በኩል በንቃትና በማስተዋል በማክበርና ቅንነት መሰብሰብ አለባት ። ራሷንም እሾህና ቁጥቋጦ ከሆነው ከዓለማዊ ሳብከምድራረብሻና ከምኞት እሳት መጠበቅ አለባት ። በዚህ ሁኔታ ከለበሰ/ከተጠበቀ ዓይንን ክፉ ከማየትጆሮን ሜት ከመስማትእጅና እግርን ከመጥፎ ሥራ ይጠብቃል ። ነፍስ የሰውነትን ክፍሎች ከጥፍር እስከ ፀጉር ክፉና አሳፋሪ ከሆነ ድምፅ ፣ ብልግና ከሆኑ ቃላትዓለማዊና ክፉ ከሆነ ምኞት የመጠበቅና የመከልከል ቃድ አላት።
4. ፍስ ራሷን ከርኩስ የኑሮ ዘይቤ የልብንምሳብ ከዓለማዊነት የኑሮ ዘይቤ እንዲላቀቅ ታደርጋለች ። በዚህም በመጣርና ከቀድሞ በበለጠ በመታገል በታላቅ ማስተዋልም የሰውነት ክፍሎችን በሁሉም አቅጣጫ ከክፉ ነገር በመግታት መልካም የሆነውን ከእግአብሔር የተሰጠውን ልብስ ሳይቀደድሳይቃጠልና ሳይቆሽሽ እንዲኖር ይጠብቀዋል ። ነፍስ ራሷ በማወቅክፉን ከመልካም በሚለይ ቃድዋና በእግዚአብሔር ይል በእርሱም ታላቅነት ባላት ብርታት ሁሉ ራሷን አንድ አድርጋ ከዓለማዊ ምኞት ታሸሻለች በዚህም ምክንያት በጌታ እየታገዘች ከተነገሩት መቅሰፍቶች ትድናለች ። ጌታ ማንኛውንም ሰው ለይወት ምኞትና ሁከትለቁሳዊ ብት ፍላጎትለዓለማዊ ፍቅርበከንቱ ሳብ መዋጥ ላይ በጥንካሬ ጀርባውን አዙሮ ሲያየው የጸጋውን እርዳታ ይሰጠዋል። ያቺ ነፍስም እንዳትወድቅ ይጠብቃታል ። ድንቅ በሆነ ሁኔታ “ክፉ በሆነው በአሁኑ ዓለም” (ገላ 1፥4) ውስጥ በማለፍ  ነፍስ ከእግዚአብሔርና ከመላእክቱ ሰማያዊውን ስጦታ ትቀበላለች ። ምክንያቱም የራሷንና የግዙፉን ሥጋ ልብስ ስለ ጠበቀችበተሰጣት ኃይልም እስካለች ከዓለማዊ ምኞት ስላመለጠችና ጌታ እገዛ የዚህ ዓለም ሩጫዋን በሚደንቅ ሁኔታ ስለፈጸመች ነው
5.  ነገር ግን አንድ ሰው ይወቱን ቸልተኛና ግድ የለሽ ሁኖ ያለ ሥርዓትና ማስተዋል ራሱን ለማስደሰት ከኖረ ከዚህ ዓለም ምኞት ራሱን ሊያርቅ ሆነ ጌታን ብቻ ሊፈልግ አይችልም። በምኞቶቹም ምክንያት በዚህ ዓለም እሾህ ይወጋልከእግዚአብሔር የተሰጠው የአካሉም ልብስ  በምኞት እሳት እዚህም እዚያም ይቦጫጨቃል። እንዲህ ያለችው ነፍስ የተሰጣትን ልብስ በንጽና ስላልጠበቀች ነገር ግን በዚህ ዓለም ማታለል ስላሳደፈችው በፍርድ ቀን በራስ በመተማመን አትቆምም በዚህም ምክንያት ከመንግሰማያት ትጣላለች ። ራሱን በፈቃዱ ለዚህ ዓለም የሰጠውንበምኞቱም የተታለለውንና ከእውነተኛ መንገድ በቁሳዊ ፍቅር የወጣውን ሰው እግዚአብሔር ምን ያደርገዋል ? እግዚአሔር የሚረዳው ራሱን ከቁሳዊ ደስታ ያራቀውንድሮ የነበረውን ጥፋቱን የተወውንሁልጊዜም ሳቡን ወደ ጌታ የሚያደርገውንና ሲፈልግም ሳይፈልግም የፈለገው ወይም ያልፈለገው ሳብ ቢሆንም ራስን ክዶ ጌታን ብቻ የሚፈልግን ሰው ነው። ይህ ጌታ ከእቅፉ ር የሚያደርገው ሰው በሁሉም አቅጣጫ ከቁሳዊ ዓለም ወጥመድና ጥልፍልፍ ራሱን የሚጠብቅ ፣ ደኅንነቱንም በመፍራትና በመንቀጥቀጥ የሚፈጽም (ፊልጵ 2፥12) ፤ የዚህን ዓለም ወጥመዶች መናክሎችንና ምኞቶችን በጥንቃቄ የሚያልፍ በጌታ ቸርነት በጸጋው እንደሚድን ተስፋ የሚያደርግ ነው
6. እነዚያ ልባም የሆኑትን አምስት ደናግላን እስኪ አስቧቸው በልባቸው ማጠራቀሚያ ውስጥ የራሳቸው ተፈጥሮ ያልነበረውን ዘይት ማለትም ከላይ የሆነውን የመንፈስ ቅዱስ ጸጋን ይዘው ከሙሽራው ጋር ወደ ሰማያዊው ሰርግ ቤት መግባት ችለዋል ። ነገር ግን እነዚያ ባላቸው ነገር የረኩራሳቸውን ያላዩትና በሥጋ ሳሉ በልባቸው ማጠራቀሚያ “የደስታ ዘይትን” (መዝ45፥7) ለመቀበል ባተሌ የሆኑትንበስንፍና በቸልተኝነትና በግድ የለሽነት የተኙትንበድንቁርናና በውሸት/ልም ጽድቅ ውስጥ ያሉትንሙሽራውን ማስደሰት ስላልቻሉ ከሰማያዊው የሰርግ አዳራሽ ውጪ የተጣሉትን ሰነፍ የሆኑ አምስት ደናግላን ደግሞ አስቧቸው ። በዚህ ዓለም ስሜትና ፍቅር ተይዘው ሙሉና ጥልቅ የሆነውን ፍቅራቸውን ለሰማያዊው ሙሽራ አልሰጡምና ዘይት አልተሰጣቸውም ። ከራሳቸው የማድረግ አቅም በላይ የሆነውን በመንፈስ ቅዱስ መቀደስ የሚፈልጉ ነፍሳት ያላቸውን ፍቅር ሁሉ ለጌታ ይሰጣሉሲራመዱ ይጸልያሉ ፣ አሳባቸውንና ፊታቸውን ከሁሉም ዓለማዊ ነገር በመመለሳቸው ሰማያዊ የሆነውን ዘይት ለመቀበል የተገቡ ሁነው ተገኝተዋል ሰማያዊውንም ሙሽራ ሳያንቀ በመጠበቅ ፍጹም ደስ አሰኝተውታል ። ባላቸው ነገር ብቻ የሚደሰቱ ነፍሳት ግን በዚህ ዓለም ሳብ ውስጥ ይማቅቃሉ ሳባቸውም ስለዚህ ዓለም ብቻ ነው ። በራሳቸው ግምት በሙራው ሰርግ ቤት ያሉና በሥጋቸውም ያጌጡ ይመስላቸዋል ነገር ግን ከመንፈስ አልተወለዱም የደስታን ዘይትም አልተቀበሉም
 
7. አምስቱ የነፍስ ምክንያታዊ ዋሶች ከላይ ጸጋን ከተቀበሉና በመንፈስ ቅዱስ ከተቀደሱ ከላይ የጥበብን ጸጋ ተቀብለው ልባም ደናግል ይሆናሉ ።  ነገር ግን በተፈጥሮ በተቀበሉት ነገር ብቻ ከረኩ ሰነፎችና የዚህ ዓለም ልጆች ይሆናል። ምንም እንኳን በውጫዊ መልክና በማስመሰል በሃሳባቸውም የዚህን ዓለም መንፈስ ያወለቁ ቢመስላቸውም አውልቀው አልጣሉትም ነገር ግን ራሳቸውን እያታለሉ ለሙሽራው ሙሽሪት አድርገው ያቀርባሉ ። ራሳቸውን ሙሉ በሙሉ ለጌታ የሰጡ ነፍሳትሳባቸውጸሎታቸውእርምጃቸው ሁሉ የጌታን ፍቅር የተከተለ ነው ። ልክ እንደዚሁ ከዚህ ዓለም ፍቅር ጋር የተዛመዱና በዚህ ዓለም ፍቅር የተወሰኑ ፤ ቆይታቸውንም በዚህ ዓለም ለማድረግ የፈቀዱ ነፍሳት ሚኖሩትና ሚራመዱት አእምሮአቸውም የሚኖረው እዚሁ ነው። በዚህም ምክንያት መልካም ከሆነው ከመንፈስ ቅዱስ ጥበብ ጋር መስማማት አይችሉም። ወደ ሰማያዊው የሰርግ አዳራሽ ለመግባትና ላለማዊ ድኅነት ለማግኘት እኛ የሆነው ሰማያዊው ጸጋ ከእኛ ርይ ጋር መዋድና መጣመር  አለበት
8.  ኛ ተፈጥሮ ካልሆኑት ውስጥ አንዱ አደገኛ የሆነውን የኃጢአት ስሜት በአንዱ ሰው አለመታዘዝ በኩል ተቀብለናል ። ይህም ኃጢአት በረዥም ልምድና በተፈጥሮ ዝንባሌ ተፈጥሮአችን መስሏል ። ይህ ከእኛ ተፈጥሮ ውጪ የሆነው ነገር መወገድ ያለበት የቀድሞውም ንጽና መመለስ ያለበት ከእኛ ተፈጥሮ ውጪ በሆነው በሰማያዊ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ነው ። ከሰማይ የሆነውን የመንፈስ ቅዱስ ፍቅር በጸሎትበልመናበምልጃና በእምነት አሁን ካልተቀበልን ለዓለማዊነትም ጀርባችንን ሰጥተን በክፋት የተበከለው ተፈጥሮአችንም ወደ ጌታ ፍቅር ካልተሳበና በመንፈስ ቅዱስ ፍቅርም ካልተቀደሰ ፤ እስከ መጨረሻውም እንዳንወድቅ ተግተን ካልተጋደልን ፣ ግጋቱም መረት ካልተጓዝን ሰማያዊውን መንግሥት መውረስ አንችልም
9.  ባለኝ አቅም ሁሉ ጥልቅና ስውር የሆኑ ቃላትን ልናገር ስለሆነ በንቃት አዳምጡኝ ። የማይወሰነውየማይደረስበት ያልተፈጠረው እግዚአብሔር በማይወሰነውና ከሳባችን በላይ በሆነው ቸርነቱ ሥጋ ለብሶ ወይም እንዲህ ማለት እችላለሁ የሚታዩት ፍጡራኑ ከመለኮታዊ ይወት ተካፋይ እንዲሆኑ እነሱን ከእርሱ ጋር ለማዋድ ራሱን ዝቅ አድርጎ ከማይደረስበት ክብር ራሱን አረደ ። ነፍስ ትን መላእክት አያም ሰይጣን ዓይነታቸው ይለያይ እንጂ አካል አላቸው ። እንደኛ  እንደሚዳሰሰው ግዙፍ አካል ባይሆንም እነዚህ አካላት እንደየ ረቂቅነታቸው የራሳቸው የሆነ ማንነት ፣ ፀባይና መልክ አላቸው ። ከዚህም በተጨማሪ በጣም ረቂቅ የሆነችው ነፍስ የምታይበት ዓይንየምትሰማበት ጆሮየምትናገርበት ምላስየምትዳስስበት እጅና ሁሉም አካላት ያላት ሲሆን የይወት አገልግሎትንም በእነርሱ ትፈማለች
10.  ልክ እንደዚሁ የማይወሰነውና የማይደረስበት ከመታወቅ በላይ በሆነ ክብር የሚኖረው እግዚአብሔር ራሱን ወስኖ ጋን ተዋ። ለሰው ባለው ርና ፍቅር ጋችንን ነቶ ተዋደው ቅዱሳን ከሆኑእምነት ካላቸውና ደስ ከሚያሰኙት ነፍሳት ጋር ራሱን አዋዶ ከእነርሱ ጋር አንድ መንፈስ ሆነ ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው ፡- “ከጌታ ጋር የሚተባበር ግን አንድ መንፈስ ነው” (1ቆሮ 6፥17)። ይህንንም እንዲህ ማስቀመጥ ይቻላል ነፍስ ብቁና ፈቃደኛ ከሆነች አዲስየማትሞትና ከማያልፈውም ክብር ተካፋይ እንድትሆን ሥጋን ተዋሐደ ። እርሱ በሚታየው ዓለም ያሉትን እንደ ምድር፤ ተራሮችና ዛፎች ያሉ ቁሶችን ከምንምነት እንዲፈጠሩ፤ በመላቸውም ወንዞች እንዲፈአስቀድመው ከተፈጠሩት ፍጥረቶች የሰማይ አእዋፍ እንዲፈጠሩ፤ ከዚህም በላይ በዓይን ለማየት ስውር የሆኑ እንደ እሳትና ነፋስ ያሉ ፍጥረታት እንዲፈጠሩ ካደረገ
ይቀጥላል
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ
አዳዲስ መጻሕፍትን ይግዙ

ተዛማጅ ጽሑፎች

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ