አትሸነጋገሉ
“አቤቱ፣ አድነኝ፣ ደግ ሰው አልቆአልና፣ ከሰው ልጆችም መተማመን ጎድሎአልና፡፡ እርስ በርሳቸው ከንቱ ነገርን ይናገራሉ፤ በሽንገላ ከንፈር ሁለት ልብ ሆነው ይናገራሉ” /መዝ. 11፡1-2/፡፡
“በጣም ነው የምንዋደደው ለአንድ ቀን እንኳ ተጣልተን አናውቅም” የሚሉ ባልና ሚስት ሰው ከሄደ በኋላ ወዳቆሙት ጠብ ይመለሳሉ፡፡ ሰውዬውን ከፊታቸው አድርገው “ይህን ያህል ለምን እንደምወደው አላውቅም በጣም ነው የምወደው” ብለው ዞር ሲል ሐሜት የሚጀምሩ እየበዙ ነው፡፡ ሰው በመድረክ ተውኔት ቢሠራ ሙያ ነው፡፡ በሕይወቱ ተውኔት መሥራት ግን ውርደት ነው፡፡ እጅ እግርን ሊደብቀው አይችልም፣ አካል ነውና፡፡ ክርስቲያኖችም አካል ናቸውና ሊደባበቁ አይገባም፡፡ ሽንገላ አገልግሎትን ሳይቀር እየገዛ ነው፡፡ ፍቅር የሌላቸው አገልጋዮች ፍቅርን ከማምጣት ይልቅ ሲገናኙ እንደሚዋደድ ለመምሰል እንቅስቃሴ ያደርጋሉ፡፡ ሐሜት ያስለመዱት ምእመን ግን እያየ ይታዘባል፡፡ ሽንገላ ፍቅርም ጠብም አይደለም፡፡ ፍቅር ቢሆን አይዋሽም፣ ጠብ ቢሆን አስታራቂ ይገባል፡፡ ሽንገላ እንደ ፍግ እሳት ውስጥ ውስጡን የሚሄድ ጥፋት ነው፡፡ ሽንገላ ተመራጭ ውሸት እየሆነ መጥቶአል፡፡ “ነውም፣ አይደለም አትበለው፣ አዎ አዎ ብለው ሸኘው ለጥቂት ሰዓት ምን ያጣላል” የሚሉ እየበዙ ነው፡፡ ዲፕሎማሲ የተጠና ውሸት ነው፡፡ ዲፕሎማሲ ሕጋዊ ውሸት ነው፡፡ ለአገር ሲባል የሚደረግ እውነትም ውሸትም የማይል ግን ሐሰተኛ የሆነ አካሄድ ነው፡፡ ዲፕሎማሲ ግን ትዳርና ወዳጅት ላይ ሊኖር አይገባውም፡፡ አቅም መጨረስ ነውና፡፡
ነቢዩ ደግ ሰው አልቆልና አድነኝ ሲል እርሱ የፈለገው ደግ ሰው እውነት የሚናገር፣ በእውነት የሚያፈቅር ነው፡፡ ሰዎች በር ዘግተው አልተቀመጡም፡፡ መገናኘት ግድ ሆኖባቸው ይገናኛሉ፡፡ ሲገናኙ ግን እርስ በርስ በመጠባበቅ ነው፡፡ ነቢዩ ይህና ባየ ጊዜ አድነኝ ብሎ ተማጽኖ አቀረበ፡፡ እኛን የሚያይ ጻድቅ ካለም ከእነዚህ አድነኝ ብሎ ጸልዮብን ይሆናል፡፡ ምክንያቱም አፋችን እየመረቀ ልባችን ይራገማልና፡፡ ጅብ ፊትና ኋላ አይሄድም፡፡ ከኋላው ያለው ታፋው ካማረው ሊገምጠው ይችላል፡፡ ስለዚህ ጅብ ፊትና ኋላ አይሄድም፡፡ በመስመር ጎን ለጎን ይጓዛል፡፡ መንገድ ሞልተው ሲሄዱ አይቻለሁ፡፡ የሰው ጉዞ ግን እንደ ጅብ ጉዞ መሆን የለበትም፡፡ ከእርስ በርስ ፍቅራችን በላይ ግንኙነታችን ፈሪሃ እግዚአብሔር ያለው ግንኙነት ካልሆነ አስፈሪ ነው፡፡ ነቢዩ እነዚህን አስብቶ አራጆች አየና አድነኝ አለ፡፡ እርሱ ጋ አልመጡም፡፡ በርቀት ሲያያቸው አድነኝ አለ፡፡
ፍቅር እውነተኛ የሚሆነው በእውነት ላይ ሲመሠረት፣ የሚቀጥለውም መተማመን ሲኖር ነው፡፡ ሽንገላ መተማማት ብቻ አይደለም፡፡ የሌለንን ፍቅር እንዳለን አድርገን ማቅረብም ሽንገላ ነው፡፡ ሽንገላ የጭንብል ኑሮ ነው፡፡ ጭምብሉ ሲወልቅ ትክክለኛው ማንነት ይመጣል፡፡ ሽንገላ አብሮ ለመቆየት እንጂ አብሮ ለመኖር አይሆንም፡፡ ያደክማል፡፡ በሰው ፊት ዝምተኛ መምሰል ሰው ከሄደ በኋላ የነገር መርዝ መውጋት የሸንጋዮች ጠባይ ነው፡፡ ሽንገላ ጻድቅ መባልን እንጂ መሆንን አይፈልግም፡፡ ሸንጋዮች ያደክማሉ፡፡ አብሮአቸው የሚኖር ቁጠኛና ተናጋሪ ስለሚሆን ከሩቅ የሚያየው ሸንጋዩን ቅዱስ፣ ቁጠኛውን ርኩስ አድርጎ ይመለከታል፡፡ ኑሮ ግን በቅርበት እንጂ በሩቅ አይገመገምም፡፡ እግዚአብሔር ሸንጋይና ነፍሰ ገዳይን አንድ አድርጎ ይቆጥራል፡፡ ሸንጋይ ቀስ እያለ የሚገድል ነውና /መዝ. 54፡23/፡፡ የሸንጋዮች ዕድሜአቸው አጭር ነው ይላል፡፡ ለዚህ ይሆን አባቶች፡- “የዛሬ ልጅ ልብሱ ነጭ፣ ነገሩ ምላጭ፣ ከዕድሜው የሚቀጭ” የሚሉት? እግዚአብሔር ከሽንገላ ሕይወት ይፍታን፡፡ ይህን ሰይጣናዊ ጥበብ ከምድራችን ያንሣልን፡፡ የፍቅርና የእውነት ሰው ያድርገን!