የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ

የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

ከእባብ ወደ ዘንዶ

            ማክሰኞ፣ጥቅምት 22 2004
ካወቅክ መበደልክን
ከለየህ ክፋትክን
ከገለፅክ ገመናህን
ካየህ መራቆትክን

ዛሬን ወይም አሁን ነውና የኛ ዕድሜ
ተመለስ ተመለስ ተመለስ ወንድሜ፡፡
አትጨክን በክፋት ዛሬን ለመበደል
የእባብ ልጅ ሆነህ በሚዛን ለመቅለል
ወገኔ ይሁዳ ወንድሜ ዴማስም
ወልድን ፍጡር ያልከው ስጋዬ አርዮስም
ከእባብ ወደ ዘንዶ አይሁን ኩብለላችሁ
ከልብ ተመለሱ
        ዓለምን ምኞትዋን በመስቀል ሰቅላችሁ፡፡
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ
አዳዲስ መጻሕፍትን ይግዙ

ተዛማጅ ጽሑፎች

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ