የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ

የዲያቆን አሸናፊ መኰንን ገጽ 

የእግዚአብሔር ትራፊ

                                               ሰኞ፣ ጥር 21 2004
ከግምት ከበዛው ከማይቆጠረው
ከተትረፈረፈው ጨብጠን ከያዝነው
ከአምስቱ አሳና ከሁለቱ እንጀራ
አለን ከምንለው ከኛ ብዙ ዝና

ይደንቀኛል ይገርመኛል የአምላኬ ሥራ
አዕላፍ መግቦ በብዙ በረከት
በፀጋው ተረፈ አስራ ሁለት ቅርጫት
የእግዚአብሔር  ትራፊ እኛ ካለን በልጧል
ዕልልታ ለስሙ ምስጋናውም በዝቷል
ይልቅ አትመኩ አለን እያላችሁ
ከታላቁ ጌታ እግሩ ስር ወድቃችሁ
የጽድቅ ፍርፋሪ ለምኑ ባካችሁ
ከከነናዊቷ ሕይወት ተምራችሁ
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ
አዳዲስ መጻሕፍትን ይግዙ

ተዛማጅ ጽሑፎች

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ