እግዚአብሔር :-
እያበራ ይቅደምላችሁ ፣
እየከለለ ይምራችሁ ፣
የምትጠሩት ይስጣችሁ ፣
አዛኝ ይዘዝላችሁ ፣
በክፉ ቀን መንገድ ይሁናችሁ ፣
በሩቅ አገር ያሰልጥናችሁ ፣
አንደበት ሁኖ ይርታላችሁ ፣
የባዕድ ወኪል ይዘዝላችሁ ፣
የምትናገሩት ደግ ቃል አያሳጣችሁ ፣
አንደበታችሁን ያጣፍጥላችሁ ፣
የበረሃ ጥላ ይሁናችሁ ፣
በጥቁር ቀን ይደግፋችሁ ፣
የቅርቡን ያስታግሥላችሁ ፣
የረገጣችሁትን ያለምልምላችሁ ፣
ከሕሊና ወቀሳ ፣ ከልጅ ከሰሳ ያድናችሁ !
ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም.