የትምህርቱ ርዕስ | ራስህን ስጠኝ

“እግዚአብሔርሰጠ ፥ እግዚአብሔርም ነሣ ፤ የእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁን ።” (ኢዮ 1፥ 21)።
ጌታ ሆይ እነዚህ ውብ ድምፆች ፣ ባሪያህ ኢዮብ መከራ ስቃይ በበዙበት ወቅት እንዲናገራቸው የሰጠኸው ቃላት ናቸው ። እነዚህን ቃላት እንደ እኔ ባለ ኃጢአተኛ አፍና ልብ ላይ እንደገና አስቀመጥህ ። እንዴት ያለህ መልካም ነህ ! አንተ አንድ ወቅት ጤናን ሰጠኸኝ እኔም ረሳሁህ ። አንተም (ጤናዬን) ከእኔ ወሰድህና አሁን ወደ አንተ ተመለስሁ ። እንዴት ያለ እጅግ ታላቅ ስጦታ ነው ! ራስህን ለእኔ ትሰጠኝ ዘንድ ካንተ ይለዩኝ የነበሩትን ያንተን ስጦታዎች ከእኔ አራቅሃቸው ።
ጌታ ሆይ ፣ ካንተ ያልሆነውን በእኔ ያለውን ሁሉንም ነገር ውሰድ ። ሁሉም ነገር ያንተ ነው ። አንተ ጌታ ነህ ። ምድራዊ መልካም ነገሮችን ፣ ክብር፣ ጤና ፣ ሕይወት ሁሉንም ነገር እዘዝ ። በእኔ ውስጥ ያንተን ቦታ የሚወስደውን ሁሉንም ነገር ከሥሩ ቊረጠው።
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ

ተዛማጅ ትምህርቶች

የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ