የትምህርቱ ርዕስ | ስብከት ሁለት

ጨለማው ገዥና የክፋት ንጉሥ የሆነው የሰውን ልጅ ምርኮኛ አድርጎ ልክ አንድ ሰው ሌላውን ልብስ እንደሚያለብሰው ነፍሱን በጨለማ ኃይል ከቦ ጨለማ አለበሳት አንድ ልዑል ንጉይሆን ዘንድ ከእግር እስከ ራሱ ንጉዊ ልብስ እንደሚለብስ የክፋት ንጉነፍስን ኃጢአት አለበሳት ይህ የክፋት ንጉነፍስን አረከሳት በመንግቱ ግዛት ምርኮኛ አደረጋት አንዳችም ክፍሏን ነሳያደርግ አሳቧን ፣ ማስተዋሏን ፣ አካሏንአንዳች ሳያስቀር የጨለማ ካባ አለበሰው አንድ ሰው ሲታመም ሙሉ ማንነቱ ታመማል እንጂ ተለይቶ አንድ አካሉ ብቻ ታመመ ንደማይባነፍስ ደስታን በማጣትና በኃጢአት ሁለንተናዋ ታመመ ህ ክፉ እጅግ በጣም አስፈላጊ የሰው አካል የሆነችውን ነፍስ የእርሱ በሆነው ኃጢአት ሲያለብሳት የሰው ግዙፍ አካል (ሥጋ) ለቃይና መበስበስ እጁን ሰጠ
ሐዋርያው ፡- “አሮጌውን ሰው ከሥራው ጋር ገፋችሁታልና” (ቆላ 3:11) ሲል ሙሉ ማንነትን ለመግለነው ይህም አሮጌውን ዓይን በአዲስ ዓይንአሮጌውን ጆሮ በአዲስ ጆሮአሮጌውን እጅ በአዲስ እጅአሮጌውን እግር በአዲስ እግርአሮጌውን ልብ በአዲስ ልብ ሁሉን በአዲስ መተካት ነው የክፋት ንጉሙሉውን የሰው ማንነት ሥጋውንና ነፍሱን በክሎ ከነበረው ክብር በማውረድ በእግአብሔር አምሳል የተፈጠረውን ሰው “አሮጌ ማንነት” የተበከለጹሕ ያልሆነለእግዚአብሔር ግ የማይገዛ ማንነት አለበሰው ይህን ያደረገበት ምክንያት ሰው እግዚአብሔር እንዳቀደለት ማየትን ትቶ በተሳሳተ መንገድ እንዲያይበተሳሳተ መንገድ እንዲሰማወደ ክፋት ሚፋጠኑ እግሮችኃጢአትን የሚሩ እጆችርኩሰትን የሚያመነጭ ልና እንዲኖረው ነው
ስለዚህ ይህን አሮጌ ማንነት ከእኛ ይገፈው ዘንድ እግዚአብሔርን እንለምነው ምክንያቱ እሱ ብቻ ነውና ኃጢአታችንን ማስወገድ የሚችለው እኛን የማረከን በመንግቱም የተቆጣጠረንና ያሰረን የጨለማው ንጉእጅግ ከእኛ የሚልቅ ኃይል አለው ሱን ማሸነፍ በእኛ አቅም የሚሆን አይደለም ነገር ግን እርሱ እግዚአብሔር ከዚህ መራራ ባርነት ነእንደሚያወጣን ቃል ገብቶልናል ይ ከርራ በምትወጣበት ኃይለኛ ነፋስም ሲነፍስ ፀይዋም ነፋሱም የየራሳቸው አካልና ባርይ አላቸው ነገር ግን እግዚአብሔር ካልሆነ በቀር ማንም ነፋሱንና የፀዩን ሙቀት ሊለይ የሚቻለው የለም እግዚአብሔር ብቻ ነው ነፋሱን ከመንፈስ ሊያቆመው የሚችለው ልክ እንደ ፀይና ነፋስ ኃጢአት ከነፍስ ጋር ተዋህዷል ነገር ግን ሁለቱም የየራሳቸው ባርይ አላቸው ነፍስን ከኃጢአት መለየት ፈጽሞ የማይታሰብ ነው እግዚአብሔር ይህንን በነፍስና በሥጋ ላይ ያደረውን ክፉ ነፋስ (ኃጢአት) ካላስቆመውና ካላስቀረው በስተቀር በማንም ይሆናል ተብሎ የማይታሰብ ነው
 
አንድ ሰው ወፍ ስትበር አይቶ መብረርን ቢመኝ አይሆንለትም ምክንያቱም  ክንፍ ስለሌለው መብረር አይችልም ሰውም ከኃጢአት የመላቀቅና የመንያለ ነቀፋ የመሆንያለ መቆሸሽያለ ርግማን የመሆን በተቃራኒው ሁል ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር የመሆን ፈቃድ (ሮሜ 7፡18) እና ፍላጎት አለው ኃይል ግን የለውም ስለዚህ እግዚአብሔር የርግብን ክንፍ (መዝ 54(55)፡6) እንዲሰጠን እንለምነው ወደ እርሱ እንድንበር ወደ ረፍታችንም እንድንደርስ እርሱም ፉውን  ነፋስ ከነፍሳችንና ከሥጋችን ይለየዋል ህም ክፉ ነፋስ በሥጋችንበነፍሳችን ያደረው ኃጢአት ነው ። ይህንንም ኃጢአት ከእኛ መለየት እሱ ብቻ እንጂ ማንም የሚችለው አይደለም ። መጽሐፍ ፡- “እነሆ የለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ” (ዮሐ 1፡29) ይላል ። እሱ ብቻ ለሚያምኑት ምረትን አሳይቷቸዋል ከኃጢአታቸው ዋጅቶ ሁጊዜ ለሚጠብቁትተስፋ ለሚያደርጉትሳያቋርጡ ለሚፈልጉት ድንቅ የሆነውን መዳን ራ።
በሚያስፈራ የጨለማ ምሽት ነፋስ እንደሚነፍስ አትክልቱንና ዛፎቹን እንደሚወዘውዝና እንደሚያውክ የሰው ልጅም በጨለማው ኃይል ሲወድቅ ኃይለኛ ሆኖ በሚነፍሰው የኃጢአት ማዕበል ታውኳል ተንቀጥቅጧል ። በማንነቱ ሁሉ ስጥ ነፍሱ ፣ አሳቡመረዳቱየሰውነቱ ብልቶች ሁሉ ታውከዋል ከነፍሱ አልያም ከአካሉ ከኃጢአት ነየሆነና በኃጢአት ያልተደፈረ ክፍል የለም ። በተመሳሳይም ደስ የሚል የብርሃን ቀን አለ በዚህ ቀን መለኮታዊ የሆነ የመንፈስ ቅዱስ ነፋስ ይነፍሳል ። ይህም ነፋስ በጌታ ቀን (ሥራ 2፡20) በጌታ ቀን ያሉትን ነፍሳት ርታት ይሰጣቸዋል ስም ያደረጋቸዋል ። ይህ ነፋስ የነፍስ ውስጣዊ ማንነቷና ተምኔቷ ባለበት አሳቧ ስጥ  ይሰራጫል ይህ ቅዱስ ነፋስ ነፍስ ውስጥ ብቻ ሳይሆን የግዙፉ የሥጋ ማንነት ውስጥ ዘልቆ በመግባት ሥጋና ነፍስን በማደስ ከቃላት በላይ በሆነው በመለኮታዊ ረፍት ያሳርፋቸዋል ። ሐዋርያው ፡- “ሁላችን የብርሃን ልጆች የቀንም ልጆች ናችሁ። እኛ ከሌሊት ወይም ከጨለማ አይደለንም” (1ኛ ተሰ 5፡5) ሲል እየገለያለው ይህንን ነው
በጨለማው መንግት የነበረው አሮጌው ሰው ሙሉ በሙሉ አሮጌ ማንነት ያለው ነው ይህ አሮጌ ሰው የጨለማውን መንግት ልብስ ለብሷል ይህ ልብስ የእግዚአብሔርን ስም የሚሳደብ ነው ። በተጨማሪ ይህ ልብስ ያለማመንየግድ የለሽነትየግብዝነትየኩራትየንፉግነትየዝሙትጹሕ ያለ መሆን ባጠቃላይ ፀያፍ የሆኑ ማንነቶች ልብስ ነው ። ስለዚህ እዚህ ጋ ከመሬት የሆነው አሮጌውን ሰው ገፈው የጣሉትማለትም ኢየሱስ ክርስቶስ የጨለማውን መንግት ልብስ ያወለቀላቸው ሰዎች አዲሱንና ከሰማይ የሆነውን ሰው ለብሰውታል ሱም ኢየሱስ ክርስቶነው ህም ማለት ከላይ እንዳየነው በተመሳሳይ መልኩ አዲሱን ሰው መልበስ ማለት ዓይንን በአዲስ ዓይንጆሮን በአዲስ ጆሮልብን በአዲስ ልብ በመቀየር ነው ህም ሙሉ በሙሉ ንጹሕ ለመሆንና አዲሱን ሰማያዊ ሰው ለመልበስ ነው
ጌታ እርሱን የሚጠብቁትን ነፍሶች ከቃላት በላይ የሆነውን የመንግቱን ብርሃን ያለብሳቸዋል ። ይህንን ብቻ አይደለም የእምነትየተስፋየልግስናየሰላምየደግነትየርሌሎችንም ሕያው የሆኑትን ልብሶች ያለብሳቸዋል ። እግዚአብሔር በባርይው መገለጫዎች ፍቅርሰላምሐሴትኄ ፣ የዋህነት … እንደ ሆነው አዲሱም ሰው በጋው እንደርሱ ይሆናል ። የጨለማው መንግትና ኃጢአት እስከ ትንኤ ድረስ በኃጢአተኛው ነፍስ ውስጥ ተደብቀው ይኖራሉ ከትንኤው በኋላ የኃጢአተኛው አካል አሁን በነፍስ ውስጥ በተደበቀው ጨለማ ትዋጣለች ። ልክ እንደዚሁ የብርሃን መንግት ሰማያዊ መልክ ኢየሱስ ክርስቶስአሁን ረቂቅ በሆነ መንገድ ለነፍስ አብርሆትን ሰጥቷታል በጻድቁም ነፍስ ይነግነገር ግን ከሰው ዓይን (ከሥጋዊ ዓይን) የተሰወረ ነው ክርስቶስ በነፍስ ዓይን ብቻ ነው የሚታየው ። ይህም የሚሆነው እስከ ትንኤ ድረስ ነው ። ከትንኤ በኋላ ግን የሰው ሰውነት በጌታ ብርሃን ይዋጣልይከብራል (ፊል. 3፡21) ይህም ብርሃን አሁን በጻድቃን ነፍስ ያለ ብርሃን ነው ። ሥጋችንም የክርስቶስን መንግት ከተቀበለችው ዘላለማዊ ብርሃን ከበራላትና በዘላለማዊ ብርሃን ካረፈችው ነፍችን ጋር አብሮ ይነግ። 
በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ

ተዛማጅ ትምህርቶች

የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ

መጻሕፍት

በዲያቆን አሸናፊ መኰንን

በTelegram

ስብከቶችን ይከታተሉ

አዳዲስ መጻሕፍት

ትርጉሙ:- ቀይ ዕንቈ

ለምድራችንና ለአገልግሎታችን በረከት የሆነ መጽሐፍ
የመጀመሪያ እትም ጥቅምት 2016 ዓ.ም

1ኛ ጢሞቴዎስ ትርጓሜ – ክፍል አንድ

የመጀመሪያ እትም ሐምሌ 2013 ዓ.ም

ምክር አዘል መጽሐፍ

የመጀመሪያ እትም