መግቢያ » ልዩ ልዩ ሁለት » ኧረ ና እባክህ

የትምህርቱ ርዕስ | ኧረ ና እባክህ

በኔ አገር አፈር ይሸጣል ፣ ለአበባ መትከያ ፤ ዶሮም ዋጋ አውጥታ የአንድ ወር ደመወዝ ይዛ ትሄዳለች። በግ የአራት ወር ደመወዝ አይችለውም። በሬ አይደረስበትምና ማንም አያስበውም። የሬሳ ማጠቢያ ውኃም በልኬት ይሸጣል። ለተራመዱበት መንገድ ፣ ለቆሙበት ስፍራ በሰዓት ይከፈላል ። የውሻ ቡችላም በውድ ዋጋ ይሸመታል። የሰው ልጅ ብቻ መንገድ ላይ ወድቆ የሚያነሣው ጠፍቷል። ድህነት አልጠፋም፣ ድሀው ግን እየጠፋ ነው። ሮም ክርስቲያን እስክትሆን በሰማዕታት ደም ታጠበች። ክርስትናን ስትቀበል ከበደለችው በላይ ካሰች። በኔ አገር በክርስቲያን ምድር ክርስቲያን ይታረዳል። ልጅዋ እየሞተ ስለ ሕንፃ የምትጨነቅ እናት የለችም ፣ ቤተ ክርስቲያን ስለ ልጆችዋ ሞት ፣ እረኞች ስለ መንጋው ማለቅ መደንገጥም አቁመዋል !

ኧረ ና እባክህ ! መድኃኔ ዓለም እናስቸግርህ!

ኅዳር 5 ቀን 2019 ዓ.ም.

በማኅበራዊ ሚዲያ ያጋሩ
ፌስቡክ
ቴሌግራም
ኢሜል
ዋትሳፕ

ተዛማጅ ትምህርቶች

የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ
የትምህርቱ ርዕስ