ከልቤ እንድወድህ ፣
በኑሮ በሞቴ እንዳከብርህ ፣
ለምስጋናህ እንድተጋ፣
በሰጠኸኝ ልክ እንዳገለግልህ ፣
በሰው እጅ እንዳልወድቅ ፣
ለፍርሃት እጅ እንዳልሰጥ ፣
ወዳጄን እንዳልወጋ ፣
አዘመመ ብዬ ሰው እንዳልገፋ ፣
ለሚያልፍ ቀን የማያልፍ ንግግር እንዳልናገር ፣
ልቤ እንዳይከዳኝ ቀልቤ እንዳያመልጠኝ ፣
ምኞቴ እንዳይገዛኝ ፣
በአገሬ ተስፋ እንዳልቆርጥ ፣
እንደ ወጣሁ እንዳልቀር፣
የቀባኸውን እንዳላዋርድ ፣
የሰጠኸኝን ብቻዬን እንዳልበላ ፣
ወዳጄን እንዳላማ ፣
ያፈቀርኩትን እንዳልጠላ ፣
ሞቴን እንዳልረሳ ፣
ብቻዬን ነኝ እንዳልል ፣
ዕድል እንዳያመልጠኝ ፣
የሚያድግ ልጅ እንዳይጠላኝ ፣
የሚሞት ሽማግሌ እንዳይረግመኝ ፣
የሰው ረሀብ እንዳይገጥመኝ ፣
በአፍ ብቻ እንዳልወደህ ፣
ለማያዩ እንቅፋት እንዳላስቀምጥ ፣
በችግረኛ እንዳልጨክን ፣
በክፉ ቀን እንዳልከፋ ፣
ጥጋብን እንድታገሥ ፣
ቂምን እንዳሸነፍ ፣
በቀልን እንድንቅ ፣
የቀረበኝን እንዳልገፋ ፣
ያለኝን ማየት እንዳያቅተኝ …
እባክህ ክርስቶስ ሆይ እርዳኝ!
ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም.